ቁርጥ ግብር፣ ለማስገበር አስቸጋሪ የሆኑ ገቢ ላይ ይተገበራል፡፡ በቁርጥ የሚጣል ግብር መጠን በተጠና ግምት ይሰላል፡፡ ግብር ተማኙና ሰብሳቢው ባለሥልጣን ትክክል ነው ብሎ የሚያስበውን ግብር በግምትም ቢሆን ለማወቅ የተለያዩ መረጃዎች ላይ ይመሠረታል፡፡ 

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ፣ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም ለመወሰን የሚያስችለውን አዋጅ አጽድቆ  ረቂቁን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ 

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ በዚህ ዓመት የሚጸድቁ ዋና ዋና አዋጆችን የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች የ2009 ዓ.ም. የሥራ ዘመናቸውን ሲጀምሩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ወቅት አሳውቀዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የምርጫ ሕጉና የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ የሚኖረውን ልዩ ጥቅም የሚመለከቱት ከሚወጡት ውስጥ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡

Pages