Skip to main content
x

በአገር አቀፍ የውኃ ተቋማት ቆጠራ አራት ሺሕ ሰዎች ይሳተፋሉ

በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ከአራት ሺሕ በላይ ሰዎች የሚሳተፉበት አገር አቀፍ የውኃ አቅርቦት፣ ሳኒቴሽንና ኃይጂን አጠባበቅ ተቋማት ቆጠራ ሊካሄድ ነው፡፡ ቆጠራው በዋናነት በገጠርና በከተማ የውኃ ተቋማት መሠረተ ልማቶችን ከውኃ መገኛ ቦታ እስከ ማከፋፈያ ቦኖና የቤት ለቤት መስመሮችን በማካተት የሚከናወን ሲሆን፣ በዋናነት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የመጠጥ ውኃ አቅርቦትና ሥርጭት፣ እንዲሁም የውኃ ተቋማትን ጥራት ለማወቅ ይረዳል ተብሏል፡፡

ባንኮችና ማይክሮ ፋይናንሶች ለውኃ ዘርፍ እንዲያበድሩ ተጠየቁ

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2030 አሳካለሁ ብላ ከፈረመቻቸው ዘላቂ የልማት ግቦች መካከል ንፁህ ውኃ በየቤቱ ማድረስ አንዱ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ የውሀ ተደራሽነት ጥያቄ ያለባቸው አገሮች ይህንን ግብ እንዲመቱ 114.3 ቢሊዮን ዶላር የሚያስፈልግ ቢሆንም፣ የተመደበው አጠቃላይ በጀት ግን ከተባለው ገንዘብ በሦስት እጥፍ የሚያንስ ነው፡፡

ለአዲስ አበባ ከተማ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የውጭ ምንዛሪ ተፈቀደ

የአዲስ አበባ ከተማን ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ለማሻሻል ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች አንዱ ለሆነው ኖርዝ አያት ፋንታ ጥልቅ ውኃ ፕሮጀክት የሚያስፈልጉ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ግዥ ለመፈጸም የውጭ ምንዛሪ እንዲፈቀድ በተደጋጋሚ ቢሞከርም ምላሽ ሳያገኝ ቆይቶ፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አዲሱ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) እና አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ባካሄዱት ውይይት የውጭ ምንዛሪ መፈቀዱ ታወቀ፡፡

አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገርቢ ግድብ ፕሮጀክትን ታደገ

የቻይና መንግሥት ለኢትዮጵያ የውኃ ፕሮጀክት የሰጠው 146 ሚሊዮን ዶላር የመጠቀሚያ ጊዜው አልፎ ሊቃጠል ሁለት ሳምንታት ብቻ ሲቀረው፣ በቅርቡ የተሾሙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመነጋገር ብድሩን ማትረፍ ቻሉ፡፡

በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር አዲስ አበባ ከባድ የውኃ እጥረት ያጋጥማታል ተባለ

በውጭ ምንዛሪ አቅርቦትና አመዳደብ ችግር ምክንያት አዲስ አበባ ከተማ ከአንድ ዓመት በኋላ ከበድ ያለ የንፁህ ውኃ አቅርቦት ችግር ሊገጥማት ይችላል ተባለ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 46 ሚሊዮን ዶላርና ስድስት ሚሊዮን ዩሮ ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲቀርብለት በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ምላሽ እንዳልተሰጠው አስታውቋል፡፡

ለገርቢ ግድብ ፕሮጀክት መሬት ማስረከብ ባለመቻሉ ከቻይና የተገኘ 146 ሚሊዮን ዶላር ጥቅም ላይ ሳይውል ቀረ

ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ለታሰበው የገርቢ ወንዝ ግድብ ፕሮጀክት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስፈላጊውን መሬት በወቅቱ ባለማቅረቡ ከቻይና መንግሥት የተገኘው ብድር መጠቀሚያ ጊዜ አለፈበት፡፡ ይህ ገንዘብ ከአንድ ዓመት በፊት ሥራ ላይ መዋል የነበረበት ቢሆንም፣ መሬቱን ማግኘት ባለመቻሉ ተመላሽ ሆኗል ተብሏል፡፡

ውኃ አምራቹ ጥቅም ላይ የዋሉ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን እንደሚሰበስብ ገለጸ

በአበበ ድንቁ የታሸገ ውኃና ከአልኮል ነፃ መጠጦች አምራች ፋብሪካ ያስተዋወቀው ቶፕ ውኃ የተባለ አዲስ የውኃ ምርት ይፋ ተደረገ፡፡ ኩባንያው አካባቢን የሚበክሉ የፕላስቲክ ጠርሙሶች የሚያደርሱትን ጫና ለመቀነስ ጥቅም ላይ የዋሉ ጠርሙሶችን ከመሰብሰብ ባሻገር፣ በየዓመቱ ከሚያከናውነው ሽያጭ ውስጥ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ማግኘት ላልቻሉ ማኅበረሰቦች አስተዋፅኦ የሚያደርግበትን አሠራር እንደሚከተል አስታወቀ፡፡

ውኃ የማታውቀው ሉቄ ቀዱሳ ያገኘችው ዕፎይታ

ውኃ በየመንደሩና በየቤቱ በገባበት የከተሜ ኑሮ የአንድ ጀሪካን ውኃ ዋጋ ከአንድ ብር አይበልጥም፡፡ ለገጠር ነዋሪዎች በተለይም የቤት ውስጥ የሥራ ጫና ለሚሸከሙ እናቶችና ልጃገረዶች ግን አንድ ጀሪካን ውኃ ግምት በአንድ ብር የማይገደብ የሞት ሽረት ጉዳይ ነው፡፡ ጢሻ በጥሰው ወጣ ገባውን የገጠር መንደር አቋርጠው ከጎርፍ የማይሻል ድፍርስ ውኃ ለመቅዳት የሚያደርጉት የእግር ጉዞ በትንሹ ግማሽ ቀን ሊሆን ይችላል፡፡

ፈውስን በአጠባ

ባለፈው ሳምንት እሑድ ረፋዱ ላይ እንደ ነገሩ ሆኖ በታጠረው የአሜሪካ ግቢ ውስጥ ግርግር በዝቶበት ነበር፡፡ የመኪና ማቆሚያ ተብሎ በታጠረው ቅጥር መውደቂያ ያጡ ምስኪኖችና የአዕምሮ ሕሙማን ከአንደኛው ጥግ በተደረደሩት ወንበሮች ላይ ተቀምጠው ከፊት ለፊታቸው ያለው ገንዳ ሥራ እስኪጀምር በመጠባበቅ ላይ ነበሩ፡፡ አንዳንዶቹ ከለበሱት ውኃ ነክቶት የማያውቁ አፈር መሳይ ቡትቷቸውን አውልቀው ያደፈ ገላቸውን ለመታጠብ ወረፋ መጠባበቅ ይዘዋል፡፡