Skip to main content
x

የኢጋድ ስብሰባ አሁንም ያለ ስምምነት ተበተነ

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) የደቡብ ሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ቡድን ለኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት፣ ሁለቱ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች ሥልጣን መጋራትና ወታደራዊ ኃይል አወቃቀር ላይ መስማማት እንዳልቻሉ አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎችን የአስተዳደር ወሰን ለማካለል የክልሎቹ ፕሬዚዳንቶች ልዩ ትብብር ተጠየቀ

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የአስተዳደር ወሰን ውዝግብን ለመፍታትና አስተዳደራዊ ወሰኖችን ለማካለል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና የማካለል ሥራውን በሰላማዊ ሁኔታ ለማከናወን የሁለቱም ክልሎች ፕሬዚዳንቶች ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲተባበሩና እንዲከታተሉ፣ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትሩ ጠየቁ፡፡

የወላይታ ዞን ባለሥልጣናት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ከኃላፊነት ለቀቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ግጭት በተከሰተባቸው የደቡብ ክልል የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የወልቂጤና የቀቤና የዞንና የወረዳ አስተዳዳዎች ከኃላፊነታቸው እንዲለቁና ለደረሱ ጥፋቶች ኃላፊነት እንዲወስዱ ማሳሰቢያ ከሰጡ በኋላ፣ የወላይታ ዞን አምስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡

‹‹ይህ ሙሉ በሙሉ አዎንታዊና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚደረጉ ለውጦችን ለመደገፍ የሚረዳ ነው፤›› ብለው እንደሚያምኑ የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ጌታሁን ጋረደው (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁከት የተነሳባቸው አካባቢዎች የሥራ ኃላፊዎች እንዲለቁ አሳሰቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በደቡብ ክልል ግጭት የተከሰተባቸው አካባቢዎች የሥራ ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው እንዲለቁ አሳሰቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት፣ በቅርቡ ግጭት ተከስቶባቸው በነበሩ  በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶና በወልቂጤ ከተሞች ከኅብረተሰቡ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌና የቀቤና የዞንና የወረዳ አስተዳደር ኃላፊዎች ሥራቸውን በአስቸኳይ እንዲለቁ ማሳሰባቸውን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ሁከት ተከስቶባቸው የነበሩ አካባቢዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የክልልነት ጥያቄ አነሱ

ከሳምንት በፊት በተቀሰቀሰ ሁከት የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ተከስቶባቸው የነበሩት የደቡብ ክልል ነዋሪዎች፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በነበራቸው ውይይት የክልልነት ጥያቄ አጉልተው አነሱ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በፓርላማ ሪፖርታቸውን ካቀረቡና የአባላትን ጥያቄ ከመለሱ በኋላ በቀጥታ ወደ ሐዋሳ ከተማ በማቅናት፣ በነጋታው ማክሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ከሲዳማ ዞን ከፍተኛ አመራሮችና ከነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

እንደማመጥ!

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል ውስጥ ትልቁ ችግር አለመደማመጥ ነው፡፡ ባለመደማመጥ ምክንያት የደረሱት ችግሮች ምን ያህል ከባድ እንደሆኑም ይታወቃል፡፡ የፖለቲካው የጥበብ መጀመርያ መደማመጥ መሆን ሲገባው፣ መደማመጥ ባለመኖሩ ብቻ አገሪቱና ሕዝብ በርካታ መከራዎችን ዓይተዋል፡፡

በደቡብና ኦሮሚያ አዋሳኝ ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ደረሰ

በምዕራብ ጉጂና ጌዴኦ ዞኖች ተከስቶ በነበረው ግጭት የተፈናቃዮች ቁጥር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ ከቀናት በፊት ባወጣው ሳምንታዊ ሪፖርት እስካሁን ባለው አኃዝ መሠረት 527,263 ከምዕራብ ጉጂ ዞን ሲፈናቀሉ፣ 170 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ከጌዴኦ ዞን መፈናቀላቸው ተገልጿል፡፡

በደቡብ ክልል በተቀሰቀሰ ግጭት ከአሥር በላይ ሰዎች ሞቱ

በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት ከአሥር በላይ ሰዎች መሞታቸውን፣ ዘጠኝ ሰዎች ከባድ፣ ከ80 በላይ ሰዎች ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና ከ3,000 በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኃይሉ ተናግረዋል፡፡

እያገረሹ ያሉ ግጭቶች መላ ይፈለግላቸው!

ለሦስት ዓመታት ያህል የዘለቀው ደም አፋሳሽ ግጭት በሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ረገብ ቢልም፣ በተለያዩ ምክንያቶች የሚቀሰቀስ ግጭት ግን ገጽታውንና አድማሱን እያሰፋ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በፓርላማ ከተሰየሙበት ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ቢታይም፣ ከእግር ኳስ ሜዳዎች እስከ ክብረ በዓላት ሥነ ሥርዓቶች ድረስ ምክንያታቸው በውል ያልታወቀ ግጭቶች በብዙ ሥፍራዎች አጋጥመዋል፡፡