Skip to main content
x

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቻይና ጉብኝት በርካታ ስምምነቶች እንደሚደረጉበት ይጠበቃል

ለሁለተኛ ጊዜ በሚካሄደው ከ40 በላይ የሚሆኑ አገሮች መሪዎች በሚታደሙበት የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ቻይና ገቡ፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ሌሎች የፌዴራል የሥራ ኃላፊዎችን ያቀፈው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የልዑካን ቡድን፣ በቻይና ቆይታው የብድር መክፈያ ጊዜ ማራዘምን ጨምሮ የተለያዩ ስምምነቶችን እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

የኢሕአዴግ ምክር ቤት በለሆሳስ ያለፈው የውህደት ጉዳይ

የአራት ብሔራዊ ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ)፣ ከግንባርነት ወደ አንድ አገራዊ ፓርቲ ሽግግር እንደሚያደርግ ሲነገር ከቆየ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ከቀድሞው የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ አመራር ጊዜ ጀምሮ በፓርቲው አጀንዳነት ውይይት ሲደረግበትና ጥናት ሲካሄድበት የቆየው ይኼ አጀንዳ ረዥም ዓመታትን አስቆጥሮ፣ አሁንም የግንባሩ አጀንዳና የሌሎችም የመወያያ ርዕስ እንደሆነ ዘልቋል፡፡

የክልል አመራሮች ወደ ፌዴራል እንዲመጡ የተደረገው ለውጡን ተሻጋሪ ለማድረግ መሆኑ ተገለጸ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሐሙስ ሚያዝያ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. በካቢኔያቸው ባደረጉት ሹም ሽር ሁለት የክልል መንግሥታት አመራሮች በፌዴራል መንግሥት ኃላፊነቶች ላይ እንዲሾሙ የተደረገው፣ አገራዊ የፖለቲካ ለውጡን ተሻጋሪ ለማድረግ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ኢትዮጵያ በሚዲያ ነፃነት ከፍተኛ መሻሻል ያሳየችበትን ውጤት እንዳስመዘገበች ዓለም አቀፉ ተቋም ይፋ አደረገ

የፈረንሣይ ድንበር የለሽ የጋጤኞች ቡድን (ሪፖርተርስ ሳንስ ፍሮንቲየርስ) ባወጣው የዘንድሮ በዓለም የፕሬስ ነፃነት መመዘኛ መሠረት፣ ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ ከፍተኛ የሚዲያ ነፃነት መሻሻል ያሳየችበትን ውጤት እንዳስመዘገበች ይፋ አደረገ፡፡

ፓርላማው የሚኒስትሮችን ሹመት አፀደቀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በካቢኔያቸው ላይ ያደረጉትን ሹም ሽር ፓርላማው አፀደቀ፡፡ በዚህ መሠረት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ ወ/ሮ አይሻ መሐመድ (ኢንጂነር) በመተካት የመከላከያ ሚኒስትር ሆነዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከማቋቋም ባሻገር

ታላቅ ተስፋ አጭሮ የነበረው ምርጫ 97 የአገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሒደት አንድ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል በማለት ብዙዎች የጠበቁት ጅማሮው መልካም ስለነበረ ነው፡፡ ነገር ግን ፍፃሜው በእስርና በግድያ ከመጠናቀቁም በላይ፣ አጠቃላይ የአገሪቱን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሒደት ጭራሹን ቁልቁል የሰደደና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴን ቅርቃር ውስጥ የከተተ በመሆን አልፏል፡፡

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት በህዳሴ ግድብ ላይ የተለየ አቋም የለኝም አለ

ሱዳንን ለ30 ዓመታት ከመሩት ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር ላይ ሰሞኑን  ሥልጣን የተረከበው ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት፣ ከዚህ ቀደም የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያደረጋቸውን ስምምነቶች እንደሚያከብር በማስታወቅ በተለይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የተለየ አቋም እንደሌለው ተገልጿል፡፡

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ተነሱ

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣንን ለስምንት ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት የመሩት አቶ ዮናስ ደስታ ከሥልጣናቸው መነሳታቸው ታወቀ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለአቶ ዮናስ በጻፉት ደብዳቤ፣ ከሐምሌ 13 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ለአገር ላበረከቱት አስተዋጽኦ በማመስገን፣ ከሚያዝያ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ከኃላፊነታቸው እንዳነሷቸው አስታውቀዋቸዋል፡፡

የአገራዊ ደኅንነት ሥጋት የሆነው የብሔር ፖለቲካ

በመጋቢት 2010 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ሲመጡ የነበረው ከልክ ያለፈ ደስታና ፌሽታ ቀስ በቀስ እየረገበ የመጣ ይመስላል፡፡ እርሳቸው ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት አገሪቱን ሲንጣት የነበረው ግጭት፣ ሁከት፣ ብጥብጥና አመፅ ከመጋቢት 2010 ዓ.ም.

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ አዳዲስ የቦርድ አባላት ሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብን በተመለከቱ ጉዳዮችና በዚሁ ዘርፍ ቁጥጥር ለማድረግ ሥልጣን ለተሰጠው የኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ አዲስ ቦርድ ሰብሳቢና የቦርድ አባላትን ሰየሙ፡፡