Skip to main content
x

የመስከረም ወር የዋጋ ግሽበት በ12 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ አደረገ

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ ያደረገው የዋጋ ግሽበት መረጃ እንዳመለከተው፣ በተያዘው ወር የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት በ2010 ዓ.ም. መስከረም ወር ላይ ከተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት አኳያ የ12 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ሲታይ፣ የምግብ ዋጋ ግሽበቱም ካለፈው ዓመት መስከረም ወር ይልቅ በዚህ ዓመት የ13.5 በመቶ ዋጋ ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጀመረው ኦዲት ወደ ባለ ኮከብ ሆቴሎችና ኢንዱስትሪዎች ተሸጋገረ

ለመጀመርያ ጊዜ በተሟላ ደረጃ መሬትና መሬት ነክ ይዞታዎችን ኦዲት በማድረግ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የኦዲት አድማሱን በማስፋት በባለ ኮከብ ሆቴሎችና በኢንዱስትሪዎች ላይ ቆጠራ ሊያካሂድ ነው፡፡

የሚያዝያ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13.7 በመቶ ሆነ

የሚያዝያ ወር 2010 ዓ.ም. አጠቃላይ የአገራዊ የዋጋ ግሽበት ከመጋቢት ወር ከነበረው መሻሻል በማሳየት፣ 13.7 በመቶ ሆኖ ተመዘገበ፡፡ ከወር በፊት የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15.2 በመቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ባወጣው የዋጋ ግሽበት ወርኃዊ ሪፖርት መሠረት በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ላይ መሻሻሎች ቢታይም፣ ምግብ ነክና ምግብ ነክ ባልሆኑት ሸቀጦች ላይ የታየው የዋጋ ግሽበት የተለያየ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በንግድ ተቋማት ላይ ዕርምጃ ቢወሰድም የዋጋ ግሽበት ተባብሶ ቀጥሏል

​​​​​​​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ወራት ያለምንም በቂ ምክንያት የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል ያላቸውን በርካታ የንግድ ተቋማት ቢያሽግም፣ በምግብና ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ግሽበት ተባብሶ ቀጥሏል፡፡

የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በአንድ ዓመት እንዲራዘም ተጠየቀ

ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በየካቲት ወር ሊደረግ የነበረውን አራተኛውን የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ለሚቀጥለው ዓመት እንዲተላለፍለት ጥያቄ አቀረበ፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት በአገሪቱ በተፈጠረው አለመረጋጋት፣ በተለይም በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች  ባጋጠመው ግጭት ምክንያት በርካታ ዜጎች በመፈናቀላቸው ምክንያት ቆጠራውን በዚህ ዓመት ማድረግ እንደማይቻል፣ የኤጀንሲው ኃላፊዎች እምነት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የካርታ ሥራና የታብሌት ኮምፒዩተር ግዥ መዘግየት የሕዝብና ቤት ቆጠራውን እንዳራዘመ ተገለጸ

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የካቲት 4 ቀን 2010 ዓ.ም ለሚደረገው አራተኛው የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ በቅርቡ በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ሥፍራዎች በተፈጠረው ግጭት በሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀል በቆጠራው ላይ ተፅዕኖ እንደማይፈጥር ገለጸ፡፡ የካርታ ሥራ፣ የታብሌት ኮምፒዩተርና የፓወር ባንክ ግዥ መጓተት ለመዘግየቱ በምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ድህነት ቢቀንስም የኑሮ ልዩነት እየጨመረ መምጣቱን የመንግሥት ጥናት ይፋ አደረገ

ሐረሪ ድሬዳዋና አዲስ አበባ ከአገሪቱ ዝቅተኛ የድህነት መጠን የታየባቸው ሆነዋል ባለፈው ዓመት በተካሔደ የድህነት ትንተና ጥናት መሠረት በ2008 ዓ.ም. በአገሪቱ የነበረው አጠቃላይ የድህነት መጠን 23.5 በመቶ (ከ94 ሚሊዮን ሕዝብ ውስጥ በድህነት ውስጥ የሚገኘው) እንደነበር በማሳየት ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረው የ29.6 በመቶ ይልቅ የስድስት በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ተራዘመ

በኅዳር 2010 ዓ.ም. ይደረጋል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው አራተኛው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ባልታወቀ ምክንያት ተራዘመ፡፡ ለቆጠራው አስፈላጊ የሆኑ የሎጂስቲክ ግብዓቶችና አቅርቦቶች በአብዛኛው ወደ አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ቆጠራው መራዘሙ  ታውቋል፡፡