Skip to main content
x

የተጓተተውን የንብ ኢንሹራንስ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ የቻይና ተቋራጭ በ812 ሚሊዮን ብር ተረከበው

በጨረታ ሒደቱ ላይ ጥያቄ ሲነሳበት የቆየውና የግንባታ ሒደቱ የተጓተተው የንብ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር፣ የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ግንባታ የቻይና ተቋራጭ እንዲገነባው የግንባታ ውል ተፈረመ፡፡

ለተጓተተው የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታ ብድር እንዲፋጠን ተጠየቀ

ለኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታ ፕሮጀክት የሚያስፈልገው የኃይድሮና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ግዥ መዘግየት አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ በመሆኑ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ከቻይና መንግሥት ጋር በመነጋገር በፍጥነት የኮንሴሽናል ብድር እንዲያመቻች ተጠየቀ፡፡

ኢትዮጵያ ከቻይና ከምታገኘው ጥቅል ብድር ውስጥ የዕርዳታ ምጣኔው ከፍ ተደረገ

በከፍተኛ የዕዳ ጫና ውስጥ ለምትገኘው ኢትዮጵያ ከቻይና መንግሥት ከሚገኝ ጥቅል ኮንሴሽናል ብድር ውስጥ የዕርዳታ ምጣኔው ከፍ ተደረገላት፡፡ ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ አገሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ አዲስ የኮንሴሽናል ብድር ሥሌት ተግባራዊ ማድረጓ ታውቋል፡፡

የንግድ ጦርነት ሥጋት ያጠላበት የኢትዮጵያ ወጪ ንግድ ሥጋቶች

ከሰሞኑ የንግድ ጦርነትን ያህል በዓለም ኢኮኖሚ ረገድ ትልቅ መነጋገሪያ ርዕስ ስለመኖሩ ያጠራጥራል፡፡ በቻይናና በአሜሪካ መካከል የከረረው የሸቀጦች ታሪፍ እንኪያ ሰላንቲያ፣ ቀስ በቀስ ሌሎች አገሮችንም እያስከተለ ወደለየለት የንግድ ጦርነት እንዳያመራ አሥግቷል፡፡

የዕዳ መክፈያ ጊዜ የተራዘመላት ኢትዮጵያ ከቻይና ድጋፍ ቀዳሚዋ ሆናለች

በየሦስት ዓመቱ በአፍሪካና በቻይና መካከል የሚካሄደው የቻይና አፍሪካ  የትብብር ፎረም፣ ዘንድሮ  በቤጂንግ ተስነናግዷል፡፡ በፎረሙ ከታዩና ከሚጠበቁ ጉዳዮች መካከል ለአፍሪካ የተዘረጋው የ60 ቢሊዮን ዶላር የቻይና ድጋፍ ትልቁን ቦታ ይይዛል፡፡

ኢትዮጵያና ቻይና ምንና ምን ናቸው?

የኢትዮጵያና የቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ረዥም ጊዜ በማስቆጠር፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለያዩ ዕድገቶችን እያስመዘገበ ወደ ኢኮኖሚያዊና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ደረጃ ደርሷል፡፡ ቻይና አፍሪካን ማማተር ስትጀምር ኢትዮጵያን እንደ መግቢያ ነበር የመረጠችው፡፡

የቻይና መንግሥት የኢትዮጵያን የዕዳ ጫና ለማቃለል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሁንታ ሰጠ

በቻይና አፍሪካ የልማት ፎረም ላይ ለመሳተፍ በአገሪቱ ዋና ከተማ ቤጂንግ ለቀናት ቆይታ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያን የሚጠቅሙ በርከት ያሉ ስምምነቶችን ማድረግ መቻላቸው ታወቀ፡፡ የቻይና መንግሥት የኢትዮጵያን የዕዳ ጫና ለማቃለል ይሁንታ እንደሰጣቸው ተሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደንበኞቹን ችግር መፍታት ያልቻለው በማስፈጸም አቅምና በግብዓት አቅርቦት ችግር ነው አለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደንበኞቹን ችግር መፍታት ያልቻለው፣ የሰው ኃይል የማስፈጸም አቅም ውስን በመሆኑና በግብዓት አቅርቦት ችግር እንደሆነ አስታወቀ፡፡

በሶማሌ ክልል በተፈጠረው ቀውስ የነዳጅ ኩባንያዎች ሥራ አቋርጠዋል

በሶማሌ ክልል በተፈጠረው የፖለቲካና የፀጥታ ቀውስ ሥጋት የገባቸው በክልሉ የነዳጅ ፍለጋ ሥራ የሚያካሂዱ ኩባንያዎች ሥራ ማቋረጣቸው ታወቀ፡፡ በክልሉ በተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ከሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ ዋና ከተማ ጅግጅጋና ሌሎች አነስተኛ ከተሞች በተፈጠሩ ግጭቶች በርካታ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸው፣ የንግድና የመኖሪያ ቤቶች፣ ባንክና ቤተ ክርስቲያኖች መዘረፋቸውና መቃጠላቸው የሚታወስ ነው፡፡