Skip to main content
x

‹‹በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ በጣም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ግቡን እንዲመታ ነው የተመለስነው›› አቶ ዳውድ ኢብሳ፣ የኦነግ ሊቀመንበር

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራር አባላት ቅዳሜ መስከረም 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡10 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከደረሱ በኋላ፣ በእንግዳ መቀበያ ሳሎን መግለጫ የሰጡት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከ26 ዓመታት በኋላ ወደ አገር ቤት የተመለሱት፣ በአገሪቱ የተጀመረው ለውጥ በጣም በሰላማዊ መንገድ ግቡን እንዲመታ ለማድረግ ነው አሉ፡፡

በሕገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 199 ቤቶች ለቤት አልባዎች ተሰጡ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ በሚሠሩ ኃላፊዎችና ግለሰቦች ተይዘው የነበሩ 199 ቤቶችን ቁልፍ፣ ለቤት አልባ ችግረኞች ዓርብ ጳጉሜን 2 ቀን 2010 ዓ.ም. አስረከቡ፡፡

አዲሱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መታወቂያ ይዘትና ንድፍ ለውሳኔ ቀረበ

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የሚሰጠው የመታወቂያ ካርድ ይዘትና ንድፍ ለካቢኔ ቀረበ፡፡ በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ፣ በቀረቡለት ሁለት አማራጮች ላይ ከመከረ በኋላ አንዱን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊሰጥ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ የአመራር ለውጥ አካሂዶ ሲጨርስ፣ ተሳስሮ የቆመውን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ለሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በመስጠት በድጋሚ ሊያሸጋግር መሆኑ ታወቀ፡፡