Skip to main content
x

በስብሰባ አዳራሾችና በተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረ የሽብር ጥቃት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ

በዓለም ላይ በሽብርተኝነት ከተፈረጁ አሸባሪ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በስብሰባ አዳራሾችና ተቋማት ላይ ሊፈጸም የነበረ የሽብር ጥቃት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

በቡራዩና አካባቢው ሰው በመግደልና ንብረት በማውደም 38 ግለሰቦች በሽብርተኝነት ተጠረጠሩ

ከመስከረም 2 እስከ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ በቡራዩ ከተማና አካባቢው በተፈጸመ ግድያ፣ የንብረት ቃጠሎና ዘረፋ ጋር በተያያዘ ታስረው ከነበሩት በርካታ ተጠርጣሪዎች ውስጥ፣ የ38 ግለሰቦች ድርጊት የሽብር ወንጀል ድርጊት ነው በመባሉ የ28 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡

በሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 63 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የሚያዙ ሰዎችን ወደ መደበኛ እስር ቤት ከመቅረባቸው በፊት በአገሪቱ በተለያዩ ቦታ በሚገኙ ሥውር እስር ቤቶች ውስጥ በማሰር ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል የተባሉ፣ እንደሁም ሕገወጥ ግዥ በመፈጸም በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ዘርፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ 63 ግለሰቦች ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው፣ ሰኞ ኅዳር 3 ቀን 2011 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

በቡራዩና ዙሪያው የወንጀል ድርጊት ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ድርጊት ምርመራ እንዲቀጥል ውሳኔ ተሰጠ

ከአንድ ወር በፊት በቡራዩና ዙሪያው ከተፈጸመ ግድያ፣ አካል ጉዳትና ንብረት ውድመት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ውለው በእስር ላይ የሚገኙ ከ20 በላይ ተጠርጣሪዎች ላይ፣ ምርመራው መቀጠል ያለበት በሽብር ድርጊት ወንጀል መሆን እንዳለበት ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶችን ፍረጃ ለማስነሳትና ምሕረት ለማሰጠት በፓርላማ እንደሚገኙ ታወቀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶች ፍረጃው ተነስቶላቸው በነፃነት መንቀሳቀስ እንዲችሉና ለአገራዊ መግባባት ሲባል በወንጀል ለሚፈለጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ምሕረት እንዲደረግላቸው ባሳለፋቸው ውሳኔዎች ላይ፣ ፓርላማው ሐሙስ ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚወያይና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ታወቀ።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና እነ አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ 771 ሰዎች ከእስር ተፈቱ

በሽብርተኝነት የተፈረጀው የግንቦት ሰባት ድርጅት ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት እነ አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ፣ 771 ተከሳሾችና ፍርደኞች በይቅርታና ክስ በማቋረጥ ከእስር እንዲፈቱ ተደረገ፡፡

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱ በፍርድ ቤት ተቃውሞ አሰሙ

በአርበኞች ግንቦት ሰባትና በኦነግ አባልነት ተጠርጥረው የሽብር ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች ከማረሚያ ቤት ወደ ፍርድ ቤት ከመጡ በኋላ፣ በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲደርሱ ተቃውሞአቸውን አሰሙ፡፡ በእነ ሚፍታህ ሼክ ሰሩር መዝገብ ክስ የተመሠረተባቸው 49 ተከሳሾችን ጨምሮ በእነ ክንዱ ዱቤ፣ በእነ ጎይቶም ርስቃይና በእነ አስቻለው ደሴ የክስ መዝገቦች ተካተው ክስ የተመሠረተባቸው በርካታ እስረኞች፣ ብሶታቸውን በመፈክር አሰምተዋል፡፡

ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ጋር የተጀመረው ድርድር አንድምታ

መንግሥት መቀመጫውን በአሜሪካ ካደረገው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ጋር የፖለቲካ ድርድር መጀመሩ፣ ድርድሩም ኦዴግ አገር ውስጥ ገብቶ እንዲሳተፍ በሚችልበት መርሆዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ኦዴግ የተጀመረውን ድርድር አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ካወጣ በኋላ፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤትም ሰኞ ግንቦት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ድርድሩ መጀመሩን በይፋ አረጋግጧል፡፡

ከአይኤስ የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው በተባሉ 26 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ

በኢትዮጵያ የጅሐድ ጦርነት ለማወጅ ዝግጅት እያደረጉ ነበር ተብሏል አይኤስ ከሚባለው የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉና በአዲስ አበባ፣ በሐረርና በአላባ ከተሞች ውስጥ ቡድን በማደራጀትና በማስተባበር ላይ እያሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የተገለጸ 26 ተጠርጣሪዎች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡