Skip to main content
x

በምሥራቅ ሐረርጌ በሶማሌ ልዩ ኃይል 40 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን በማዩ ሙሉኬ ወረዳ የሶማሌ ልዩ የፖሊስ ኃይል በትንሹ 40 ያህል የኦሮሞ ተወላጆችን መግደሉ ተገለጸ፡፡ ከ40 በላይ የሚሆኑም ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተጠቁሟል፡፡

ሡልጣን ዓሊሚራህና የአፋር ሕዝብ ፓርቲ አመራሮች ወደ አገር ቤት ተመለሱ

በመንግሥት በተደረገላቸው ግብዣ የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር መሥራች የሆኑት ሡልጣን ሐንፍሬ ዓሊሚራህና የአፋር ሕዝብ ፓርቲ አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ፡፡ ሡልጣን ዓሊሚራህ በሽግግር መንግሥት ጊዜ የክልሉ አስተዳዳሪ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡ ሡልጣኑ ማክሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ ሲገቡ የክልሉ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በጅግጅጋና በሌሎች የሶማሌ ክልል ከተሞች የተቀሰቀሰው ግጭት የፈጠረው ውጥረት

ቅዳሜ ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የተቀሰቀሰው ግጭት በቀብረ ደሃር፣ በጎዴና በደገሃቡር ከተሞችም በመስፋፋት የክልሉ ብሔር አባላት ባልሆኑ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ ጉዳት ደርሷል፡፡

መኢአድ አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ጠየቀ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አገር ለማፍረስ የተቀመጠ ነው ያለውን የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ፓርቲውን ይህን ጥያቄ በይፋ ያቀረበው ሐሙስ ነሐሴ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ‹‹አገር ለማፍረስ የተቀመጠው አንቀጽ 39 የወለደው ችግር የበርካታ ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል፤›› በማለት፣ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው፡፡

በሶማሌ ክልል በተፈጠረው ቀውስ የነዳጅ ኩባንያዎች ሥራ አቋርጠዋል

በሶማሌ ክልል በተፈጠረው የፖለቲካና የፀጥታ ቀውስ ሥጋት የገባቸው በክልሉ የነዳጅ ፍለጋ ሥራ የሚያካሂዱ ኩባንያዎች ሥራ ማቋረጣቸው ታወቀ፡፡ በክልሉ በተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ከሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ ዋና ከተማ ጅግጅጋና ሌሎች አነስተኛ ከተሞች በተፈጠሩ ግጭቶች በርካታ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸው፣ የንግድና የመኖሪያ ቤቶች፣ ባንክና ቤተ ክርስቲያኖች መዘረፋቸውና መቃጠላቸው የሚታወስ ነው፡፡

ለአገር የሚበጀው በሕግ የበላይነት የሚተዳደር ሥርዓት መገንባት ነው!

በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚከሰቱ ግጭቶች ሁሌም የሚጎዱት ንፁኃን ናቸው፡፡ የተለያዩ ዓላማዎችን ለማስፈጸም በደረሱ አደጋዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁኃን ሕይወታቸው ተቀጥፏል፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ለአካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ተዳርገዋል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከሚኖሩበት ቀዬ ተፈናቅለው ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል፡፡

በሶማሌ ክልል የደረሰው ሰብዓዊና ፖለቲካዊ ቀውስ

በሶማሌ ክልል ሕዝቦችና ነዋሪዎች ላይ የሚፈጸም የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በክልሉ የሚስተዋሉ ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት ሐምሌ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በድሬዳዋ የተጀመረውን ጉባዔ ተከትሎ በጅግጅጋ የተቀሰቀሰው ግጭት የበርካታ ሰዎችን ሕይወት በማጥፋት፣ ንብረት በማውደምና ከፍተኛ ሥጋት በክልሉ ከፈጠረ በኋላ ወደ አንፃራዊ መረጋጋት ተመልሷል፡፡

በንፁኃን ሕይወት የሚቆምሩ ለፍርድ ይቅረቡ!

መሰንበቻውን በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል እየተስተዋለ ያለው አሳዛኝ ድርጊት የአገር ህልውናን እየተፈታተነ ነው፡፡ በሶማሌ ክልል በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ ዘረፋና ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ከባድ ጊዜ ውስጥ እንዳለን ያሳያል፡፡

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ከሥልጣናቸው ለቀቁ

ሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶሕዴፓ) ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ከሥልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ እድሪስ እስማኤል ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡