Skip to main content
x

አገሪቱን ሰቅዘው የያዙት ሁከቶችና ግጭቶች

ባለፉት ሦስት ዓመታት አገሪቱን ወጥሮ የቆየው የግጭትና የአመፅ አዙሪት በተወሰነ ደረጃ ጋብ ያለ ቢሆንም፣ በሌላ ወገን ደግሞ ግጭቶች እንደ አዲስ የሚፈጠሩባቸውና ሁከቶች የሚስተናገዱባቸው ሥፍራዎች አልጠፉም፡፡ ይህም ቀድሞ የነበረው አመፅ ሥፍራ ቀየረ እንጂ አልረገበም ለሚሉ ወገኖች ሁነኛ መከራከሪያ ምክንያት ሆኗል፡፡

መዋሀድ የከበዳቸው የመድረክ አባል ፓርቲዎች

አወዛጋቢው ምርጫ 97 በፖለቲከኞች፣ በሲቪክ ማኅበራት አመራሮች፣ እንዲሁም በጋዜጠኞች እስር መቋጨቱን ተከትሎ የአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ጭርታና ድብታ ወሮት ነበር፡፡ ይህንን ድብታ ለመስበር በሚመስል ሁኔታ የፖለቲካ ምኅዳሩን የተቀላቀለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ በመሆን ለመሥራት እንቅስቃሴውን በ2000 ዓ.ም. ጀመረ፡፡

‹‹ዛሬ ነገ እየተባለ የጠፋው ጊዜ ከባድ ጉዳት አድርሷል›› የአገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ

በተደረገለት የሰላም ጥሪ መሠረት አገር ቤት ገብቶ በሰላም ለመንቀሳቀስ ከኤርትራ የተመለሰው በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ‹‹ሸኔ›› የተባለው የኦነግ ቡድን፣ ከኤርትራ ይዞት ከመጣው ውጪ ሠራዊቱን ካምፕ ባለማስገባቱና ዛሬ ነገ እየተባለ በባከነው ጊዜ ምክንያት ከባድ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ፡፡

ኦነግ ተከፈተብኝ ያለው ጦርነት እንዲቆም የኦሮሞ ሕዝብ ጫና እንዲያደርግ ጠየቀ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ተከፈተብኝ ያለው ጦርነት እንዲቆም፣ የኦሮሞ ሕዝብና ሰላም ወዳዶች ሁሉ በመንግሥት ላይ ጫና እንዲያደርጉ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ። ኦነግ ሰኞ ታኅሳስ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው፣ "ኦነግ በመራው የኦሮሞ ሕዝብ የነፃነት ትግልና ሕዝባችን (በተለይም ቄሮ) በከፈለው ውድ መስዋዕትነት ኢሕአዴግ ተገዶ ለሰላም ጥሪ መልስ እንዲሰጥ በመደረጉ፣ ላለፉት ስምንት ወራት ለሁሉም የሚጠቅም የሰላም መስኮት ዕድል የተከፈተ ወይም የተፈጠረ መስሎ ነበር።

ዓቃቤ ሕግ በ49 ሰዎች ሞት በተጠረጠሩ 68 ግለሰቦች ላይ ክስ መሠረተ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች መስከረም 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ፣ በመስቀል አደባባይ አቀባበል ለማድረግ ወደ ‹‹አዲስ አበባ እንዳንገባ ተከልክለናል›› ባሉ ግለሰቦች በተፈጠረ ረብሻ ለ49 ሰዎች ሞት ምክንያት በመሆን ተጠርጥረዋል በተባሉ 68 ግለሰቦች ላይ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሠረተ፡፡

የኦነግና የኦዴፓ ውዝግብ አገራዊ አንድምታ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡበት መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ ርቀው በውጭ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ ጥሪዎች ሲያደርጉ ተደምጠዋል፡፡

ከስህተቱ የማይማር የትውልድ መሳቂያ ይሆናል!

‹‹ብልህ ከሌሎች ስህተት ሲማር ሞኝ ግን ከራሱም አይማርም›› የሚለው ዕድሜ ጠገብ አባባል ትልቅ መልዕክት አለው፡፡ የሰው ልጅ በሥራ ላይ ሲሆን ስህተት ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ ‹‹ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋም›› የሚል የዛገ ተረት እየተረተ መኖር ግን አይችልም፡፡

ከሴራ ፖለቲካ ማንም አያተርፍም!

የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምኅዳር ካበላሹት በርካታ ከንቱ ነገሮች መካከል አንዱ ሴረኝነት ነው፡፡ ሴረኝነት የኢትዮጵያን መልካም አጋጣሚዎች ከማበላሸት አልፎ የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፈ፣ ያሰቃየ፣ ለስደት የዳረገና ተስፋ ያስቆረጠ ነው፡፡

በኦሮሚያ ከተካሄዱ ሰላማዊ ሠልፎች መልዕክት የወሰዱት ፓርቲዎች የትብብር ጉዞ ጅማሮ

‹‹ኦሮሞ እንኳን ሌላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስተዳደር ይቅርና ራሱን እንደማያስተዳድር ተደርጎ ይታሰብ የነበረውን የመቶ ዓመት ጥያቄ አልፈን፣ ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ኦሮሞ ያስተዳድረናል የሚሉበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡