Skip to main content
x

የክልል አመራሮች ወደ ፌዴራል እንዲመጡ የተደረገው ለውጡን ተሻጋሪ ለማድረግ መሆኑ ተገለጸ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሐሙስ ሚያዝያ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. በካቢኔያቸው ባደረጉት ሹም ሽር ሁለት የክልል መንግሥታት አመራሮች በፌዴራል መንግሥት ኃላፊነቶች ላይ እንዲሾሙ የተደረገው፣ አገራዊ የፖለቲካ ለውጡን ተሻጋሪ ለማድረግ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

እነ አቶ በረከት ስምኦን በፌዴራል ፍርድ ቤት ክስ ተመሠረተባቸው

ከጥረት ኮርፖሬት ኩባንያዎች በተለይ ከዳሸን ቢራ አክሲዮን ማኅበር ጋር በተያያዘ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ፣ በፌዴራል ፍርድ ቤት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ ክሱን የመሠረተው የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ  ሕግ ነው፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ለተጠለሉ ተፈናቃዮች ቤቶቻቸው ሊሠሩላቸው ነው

በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተጠለሉ ተፈናቃዮችን ቤቶች ለመሥራት፣ የክልሉ መንግሥት 155 ሺሕ ቆርቆሮዎችን ገዝቶ ወደ ቀበሌዎች እያስገባ መሆኑ ታወቀ፡፡ በግጭቱ የተቃጠሉ ቤቶችን ለመገንባት ራሱን የቻለ የመሐንዲሶች ቡድንም መቋቋሙን የተናገሩት የዞኑ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንበሩ አውደው፣ መንግሥት ቤታቸው ለተቃጠለባቸው ተፈናቃዮች የቆርቆሮና የሚስማር እንዲሁም የአናጢ ወጪ እንደሚሸፍን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች ለደረሰባቸው ግድያና ዝርፊያ የክልሉንና የፌዴራል መንግሥትን ተጠያቂ አደረጉ

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማና ዙሪያው ከመጋቢት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በታጣቂዎች ለደረሰባቸው ግድያ፣ ዘረፋና መፈናቀል ተጠያቂዎቹ የአማራ ክልል መንግሥትና የፌዴራል መንግሥት መሆናቸውን ተናገሩ፡፡

ፍርድ ቤት የዋስትና ጥያቄ እንዲያቀርቡ የፈቀደላቸው እነ አቶ በረከት ስምዖን ዋስትና ተከለከሉ

የጊዜ ቀጠሮ ምርመራ መዝገባቸው ሲዘጋ የዋስትና መብት መጠየቅ እንደሚችሉ ፍርድ ቤት የነገራቸው አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ፣ ፍርድ ቤቱ በነገራቸው መሠረት የዋስትና ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኙም፡፡

የናይጄሪያ አርብቶ አደሮች ለምዕራብና ለሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የፀጥታ ሥጋት መሆናቸው ተነገረ

ፈላታ በመባል የሚታወቁ የናይጄሪያ አርብቶ አደሮች ለምዕራብና ለሰሜን ምዕራብ የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የፀጥታ ሥጋት መሆናቸው ተገለጸ፡፡ አርብቶ አደሮቹ ከጥቅምት እስከ ታኅሳስ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ የሱዳንና የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው በአማራ፣ በጋምቤላና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በኩል እንደሚገቡ፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉት አቶ ገናናው አግተው ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

በፖሊስ ላይ የቅጣት ውሳኔ በመስጠታቸው የታሰሩት ዳኛ ጉዳይ ዳኞችን ሥጋት ውስጥ ከቷል በአማራ ክልል ዳኞች ያለመከሰስ መብት የላቸውም

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን የሞጣ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ አንድ የፖሊስ አባል በአንድ ወር እስራት እንዲቀጣ በሰጡት ውሳኔ ምክንያት መታሰራቸው፣ ሌሎች በክልሉ የሚገኙ ዳኞችን ሥጋት ውስጥ መጣሉ ተገለጸ፡፡

በእነ አቶ በረከት ስምዖን የዋስትና ጥያቄ ላይ ተቃውሞ ቀረበ

ከጥረት ኮርፖሬት ኩባንያዎች ጋር በተያያዘ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ከበደ ካሳ፣ የዋስትና መብታቸውን ለማስከበር ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችሉ ፍርድ ቤት ነግሯቸው እየተዘጋጁ ቢሆንም፣ የክልሉ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ የመቃወሚያ አቤቱታ አቅርቦባቸዋል፡፡

‹‹አንዳችን ለአንዳችን ጋሻ እንጂ ሥጋት ልንሆን አይገባም›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)

ሥልጣን ከያዙ አንደኛ ዓመታቸውን የያዙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ሁለተኛ የሆነውን ጋዜጣዊ መግለጫ ሐሙስ መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. በታደሰው ጽሕፈት ቤታቸው ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መግለጫ ወቅት ከጋዜጠኞች ከተነሱላቸው ጥያቄዎች ሰፋ ያሉ ማብራሪያዎችን የሰጡ ሲሆን፣ የአዲስ አበባን ጉዳይ፣ የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ፣ የኢሕአዴግን ውህደት በሚመለከት፣ ብሎም ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ዳስሰዋል፡፡