Skip to main content
x

የሞት ቅጣት ተወስኖባቸው የነበሩ 40 ግለሰቦችን ጨምሮ ለ332 ፍርደኞች ይቅርታ ተደረገ

በነፍስ ግድያና በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች የሞት ቅጣት ውሳኔ ያረፈባቸውን 40 ግለሰቦች ጨምሮ፣ ለ332 ፍርደኞች ዓርብ ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ይቅርታ ተደርጎላቸው ከእስር ተፈቱ፡፡ መንግሥት በፖለቲካና በሌሎች የተለያዩ ወንጀሎች ተከሰውና ቅጣት ተጥሎባቸው የነበሩትን ፍርደኞችና ክሳቸው በመታየት ላይ የነበሩ ተከሳሾችን፣ ከግንቦት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በይቅርታና ክስ በማቋረጥ እየፈታ መሆኑ ይታወሳል፡፡

የመንግሥትን የፖሊሲ ለውጥ የሚያመላክቱ ሁለቱ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔዎች

ኢትዮጵያ ለለፉት ሦስት ዓመታት የፖለቲካ ውጥረት፣ ከፍተኛ የሆነ የሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመትን ያስከተሉ ተቃውሞዎችና አመፆች ውስጥ ቆይታለች፡፡ ይሁንና በአገሪቱ ያጋጠመው የሰላም መደፍረስ እንዲጠራና የተሻለ የፖለቲካ መረጋጋት እንዲኖር በማሰብ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሥልጣናቸውን ለቀው፣ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል፡፡

በትግራይና በኦሮሚያ ክልሎች ታስረው የነበሩ ከዘጠኝ ሺሕ በላይ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው

ግድያና ኢሰብዓዊ የወንጀል ተግባር ከፈጸሙ ተከሳሾችና ፍርደኞች በስተቀር፣ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተከሰውና ፍርድ አርፎባቸው ለነበሩ 9,817 ተከሳሾች የትግራይና ኦሮሚያ ክልሎች መንግሥታት ይቅርታ አደረጉ፡፡ በትግራይ ክልል መንግሥት ይቅርታ የተደረገላቸው 2,206 ታራሚዎች ሲሆኑ፣ 45 ሴቶች መሆናቸውን የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋና የክልሉ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረ መስቀል ታረቀ ተናግረዋል፡፡

ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔውን አሰናብቶ በምትካቸው መረጠ

ላለፉት ሦስት ዓመታት በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ያለው አባተ ያቀረቡትን መልቀቂያ የተቀበለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ በምትካቸው ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኞ ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ባካሄደው መደበኛ ጉባዔው፣ ላለፉት ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩት አፈ ጉባዔ ያለው አባተ፣ ከአፈ ጉባዔነታቸው መነሳት እንደሚፈልጉ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሏል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሳምንት ክራሞት

ከተመረጡ ሁለት ሳምንታት ያስቆጠሩት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሥልጣናቸውን በተረከቡ በቀናት ውስጥ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሥራ ጉብኝት በማድረግ፣ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በመገናኘት ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

‹‹ትግራይ ያለ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያም ያለ ትግራይ ትርጉም የላቸውም›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እያደረጉ የሚገኘውን ጉዞ ዓርብ ሚያዝያ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በመቀጠል መቐለ ከተማ ተገኝተው ለከተማው ነዋሪዎች ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸው በዚህም ትግራይና ኢትዮጵያ የተሳሰሩ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ ‹‹ትግራይ ያለ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያም ያለ ትግራይ ትርጉም የላቸውም፤›› ብለዋል፡፡

ፍርደኞችና ክሳቸው የተቋረጠ እስረኞች የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው እንዲፈቱ ተወሰነ

በተከሰሱበት ወንጀል የተፈረደባቸውና ክሳቸው ተቋርጦ እንዲፈቱ በመንግሥት የተወሰነላቸው 746 እስረኞች የሚፈቱት፣ ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ቀርቦ ከፀና በኋላ የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው ነው፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሐሙስ የካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዳስታወቀው፣ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው ከተፈረደባቸው ውስጥ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 417 ፍርደኞች ይቅርታ እንዲደረግላቸው በፌዴራል ይቅርታ ቦርድ ተወስኖ ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ቀርቧል፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረትም ጉዳያቸው በመታየት ላይ የነበረ የ329 ተጠርጣሪዎችን ክስ ይቋረጣል፡፡

በሕወሓት ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች ሚና የነበራቸው አመራሮች ኃላፊነት እንደሚወስዱ ተገለጸ

ከጥር 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በመቀሌ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የከፍተኛ አመራሮች ኮንፈረንስ፣ በማዕከላዊ ኮሚቴው ግምገማ ወቅት እንደተደረገው ሁሉ እስከ ታችኛው ድረስ ባሉ የድርጅቱ መዋቅሮች ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች ሚና የነበራቸው አመራሮች ኃላፊነት እንደሚወስዱ፣ የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ለሪፖርተር ገለጹ።