Skip to main content
x

አራት ክልሎች  የተመደበላቸውን 5.3 ቢሊዮን ብር ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርኮች ግንባታ እንዲያውሉ ተወሰነ

 መንግሥት ከውጭ የልማት አጋሮች ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ በዘንድሮ የበጀት ዓመት ካገኘው ስድስት ቢሊዮን ብር ውስጥ 5.3 ቢሊዮን ብር የሚከፋፈሉት አራት ክልሎች፣ ሙሉ በጀቱን ለተቀናጀ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ እንዲጠቀሙበት ወሰነ። ክልሎቹ አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ናቸው፡፡

አገሪቱን ሰቅዘው የያዙት ሁከቶችና ግጭቶች

ባለፉት ሦስት ዓመታት አገሪቱን ወጥሮ የቆየው የግጭትና የአመፅ አዙሪት በተወሰነ ደረጃ ጋብ ያለ ቢሆንም፣ በሌላ ወገን ደግሞ ግጭቶች እንደ አዲስ የሚፈጠሩባቸውና ሁከቶች የሚስተናገዱባቸው ሥፍራዎች አልጠፉም፡፡ ይህም ቀድሞ የነበረው አመፅ ሥፍራ ቀየረ እንጂ አልረገበም ለሚሉ ወገኖች ሁነኛ መከራከሪያ ምክንያት ሆኗል፡፡

በደቡብ ክልል ካፋ ዞን ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ

በደቡብ ክልል በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸው ታወቀ፡፡ በዞኑ ከሚገኙ አሥር ወረዳዎች አንዱ የሆነው የዴቻ ወረዳ ከቤንች ማጂና ከደቡብ ኦሞ ዞኖች ጋር የሚዋሰኑ ሲሆን፣ በአካባቢው ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሄዱ ነዋሪዎች ያሉበት የሠፈራ ጣቢያ ይገኛል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው በዚሁ የሠፈራ ጣቢያ ውስጥ መሆኑን፣ የሪፖርተር ምንጮች ከሥፍራው አስታውቀዋል፡፡

ክልሎች የፓልም ዘይት እንዲያስገቡ የመለመሏቸውን ነጋዴዎች ለፌዴራል መንግሥት እያቀረቡ ነው

ክልሎች የፓልም ምግብ ዘይት ከውጭ አገር እንዲያስገቡ የመለመሏቸውን ድርጅቶች ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ማቅረብ ጀመሩ፡፡ ነገር ግን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያስቀመጠውን መሥፈርት ብናሟላም ተመራጭ አልሆንም ያሉ ነጋዴዎች ቅሬታ ማሰማት ጀምረዋል፡፡ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ክልሎች የመለመሏቸው ነጋዴዎች እያስገቡ ቢሆንም፣ ሁሉም አጠናቀው አላስገቡም፡፡

ደኢሕዴን ከጠቅላላ ጉባዔ አቅጣጫ በማፈንገጥ ዞኖች ክልልነትን እያፀደቁ ነው አለ

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) በደቡብ ክልል የሚስተዋለው የዞኖች የክልልነት ጥያቄን በዞን ምክር ቤቶች የማፅደቅ ተግባር ሕገ መንግሥታዊ ቢሆንም፣ ድርጅቱ በአሥረኛ ጉባዔው ካስቀመጠው አቅጣጫ ውጪ ነው አለ፡፡

ከ48 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የመስቃንና ማረቆ ተፈናቃዮች ዕርዳታ እንዲቀርብ ተጠየቀ

ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን፣ በመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት 24 ዜጎች ሞተው 167 ሰዎች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው፣ ከ48 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች የዕለት ደራሽ የምግብና ምግብ ነክ ዕርዳታ እንዲደረግላቸው ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ መቅረቡ ታውቋል፡፡