Skip to main content
x

የሕክምናው ውጋጅ

ከየመኖሪያ ቤቱና ከየተቋማቱ ተጠርጎ የሚወጣ ቆሻሻ ኑሮ ፊቷን ላዞረችባቸው የቆሼ ቃራሚዎች የህልውናቸው መሠረት ነው፡፡ የምግብ ትርፍራፊ፣ የውኃ ኮዳ፣ ሞዴስ፣ ፋሻ፣ ቤት ያፈራው ነገር ሁሉ በሚከማችበት የቆሻሻ ክምር ፌስታላቸውን አንጠልጥለው የሚርመሰመሱ ምስኪኖች ብዙ ናቸው፡፡

ለኩላሊት ሕሙማን የገና ሥጦታ

የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ደም ግፊትና ስኳር ሕመም ቢያጋጥማቸውም ትኩረት ሰጥተው አለመታከማቸው ለኩላሊታቸው ከጥቅም ውጪ መሆን ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በወቅቱ ባይዘናጉ ኖሮም ‹‹ዝብርቅርቅ ያለ ሕይወት›› ለሚሉት ኑሮ ባልተዳረጉም እንደነበር ይገምታሉ፡፡

ለዓይን ባንክ ገቢ የተደረገው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ብሌን

‹‹ከሞትኩ በኋላ የዓይኔን ብሌን የምለግሰው፣ አንዱ ለሌላው እያስተላለፈ ማየት የተሳናቸው ካለባቸው ችግር እንዲላቀቅ ለማድረግ ነው፡፡›› ይኼንን ዐረፍተ ነገር ከዓመታት በፊት የተናገሩት ቅዳሜ ታኅሣሥ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ለ12 ዓመታት ያገለገሉት አቶ ግርማ፣ ከኢትዮጵያ የዓይን ብሌን በመለገስ የመጀመርያው ሰው ናቸው፡፡

ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ያስተናግዳል የተባለው ሆስፒታል ተመረቀ

በሰባት መቶ ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ጅማ የሕክምና ማዕከል ተመረቀ፡፡ ማዕከሉ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚኖሩ ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች የሚጠቀሙበት ነው ተብሏል፡፡

በኤችአይቪ የመያዝ ምጣኔው ባለበት ቆሟል ተባለ

ኢትዮጵያ ውስጥ ከ17 ዓመታት በፊት በኤችአይቪ ኤድስ የመያዝ ምጣኔ በየዓመቱ 81 ሺሕ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ምጣኔው በዓመት ወደ 15 ሺሕ፣ አጠቃላይ ሥርጭቱም ከ15 ዓመት በፊት ከነበረው 5.8 በመቶ ወደ 0.9 በመቶ መውረዱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አሚር አማን (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

የማያመልጡት ጭስ

ለመጀመርያ ጊዜ ትምባሆ መጠቀም የጀመሩት ሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ነባር ነዋሪዎች ወይም ቀይ ህንዶች ናቸው፡፡ ክርስቶፈር ኮሎምቦስ የተባለው አሳሽ ሰሜን አሜሪካ ‹ጭስ የሚበሉ ሰዎች አየሁ ወይም አገኘሁ ብሏል፡፡

የአዕምሮ ሕሙማንን የመፈወሱ ትግል በጌርጌሴኖን

በአዲስ አበባ ራስጌ ከሚገኘው የእንጦጦ አቀበታማ ቦታ ላይ ካረፈው ቅጥር ግቢ የሚወጡና የሚገቡ ይታያሉ፡፡ ቅጥሩ ከመንገድ ዳር የዕርምጃ ያህል የሚያስገባ ቢሆንም፣ ከመሀል ከተማ የራቀ መሆኑና አቀማመጡ ለኑሮ የማያመች አድርጎታል፡፡ ሞቅ ያለ ፀሐይ ወጥቶ ሳለ አጥንት ድረስ የሚዘልቀው ቅዝቃዜ ቆፈን ያስይዛል፡፡

ጥያቄ ውስጥ የወደቀው የኮንዶም ሥርጭት

በአንድ ወቅት የዓለም ሁሉ አንገብጋቢ ጉዳይ ነበር፡፡ መንግሥት፣ ማኅበረሰቡ፣ ቀበሌዎችና የወጣት አደረጃጀቶች እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃኑ፣ የኪነ ጥበብ ዘርፉ ሁሉ በአንድ ድምፅ አንድ ሆነው የዘመቱበትም ነበር፡፡ የሁሉም አጀንዳ ለነበረው ኤችአይቪ ዳጎስ ያለ በጀት ተሰፍሮ በየመንደሩ ይጣል ለነበረው ድንኳን ኤችአይቪ ምክንያት እንዳይሆን፣ ሁሉም የበኩሉን እንዲያደርግ ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡

ማጨስ በተከለከለባቸው ከሚተን ጭስ ከአራት ሺሕ በላይ ጎጂ ቅንጣቶች መገኘታቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ ትንባሆ ማጨስ በተከለከለባቸው 15 ቦታዎች ከተነነው የሽሻና ትንባሆ ጭስ ውስጥ ደባል አጫሾችን (የማያጨሱ ሰዎችን) ለከፋ የጤና ጉዳት የሚዳርጉ 4,189 እጅግ በጣም ደቃቅ ቅንጣቶች መገኘታቸው በጥናት ተመለከተ፡፡

በሕፃናት ላይ የበረታው የአየር ብክለት

በቀድሞው ንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ ሥርዓት ነበር፡፡ ባልና ሚስቱ በወቅቱ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወረድ ብሎ በሚገኘው በዛብህ ሆቴል አልጋ ይዘዋል፡፡ ወቅቱ ክረምት ነበርና ክፍላቸው የተቀጣጠለ ከሰል እንዲገባ ጠይቀው ከሰሉ ይገባል፡፡