Skip to main content
x

​​​​​​​ጤፍ የኢትዮጵያ ፀጋ

ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትጵያውያን በቋሚነት የሚመገቡትን ጤፍ፣  ከምግብነትም ባለፈ ከአምላክ የተሰጠ ፀጋ ነው ብለው ይገልጹታል፡፡ እስከ 2008 ዓ.ም. ድረስ የተሻሻሉና አሁንም ድረስ ምርት ላይ ያሉ 42 ዓይነት የጤፍ ዝርያ ፀጋ ያላት ኢትዮጵያም ጤፍን በየዓመቱ በሦስት ሚሊዮን ሔክታር መሬት ላይ ታበቅላለች፡፡

ሥርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ግብርና

ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ በግብርና እንደሚተዳደር በሚነገርላት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና አሁንም ድረስ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ የአገሪቱ የጀርባ አጥንት ነው የሚባለው ግብርና ዜጎቿን እንኳ መመገብ አልቻለም፡፡

በ200 ሚሊዮን ብር የተቋቋመው ብሔራዊ የሩዝ ምርምር ማዕከል ተመረቀ

በጃፓን መንግሥት የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ በአማራ ክልል የተገነባው ብሔራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል ተመረቀ፡፡ ፎገራ ብሔራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል፣ በአገሪቱ ለሩዝ እርሻ ተስማሚነቱ ለሚነገርለት 30 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ለማልማት ብሎም ከውጭ ለሚገባውና ከ300 ሺሕ ቶን በላይ ከውጭ የሚገባ ሩዝ ምርትን ለመተካት ተስፋ የተጣለበት ብሔራዊ የሩዝ ማዕከል የአገሪቱ 18ኛው የግብርና ምርምር ማዕከል ሆኖ ሐሙስ፣ ኅዳር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ተመርቋል።

አብዮት የሚያስፈልገው ግብርና

በኢትዮጵያ ሊታረስ የሚችለው መሬት ከኢትዮጵያ አልፎ ዓለምን ለመመገብ የሚችል ቢሆንም፣ አገሪቷ ያላትን አቅም አሟጣ አልተጠቀመችም፡፡ ከግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስቴር የሰብል ልማት ዳይሬክተር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በኢትዮጵያ ከ50 ሚሊዮን እስከ 72 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ሊታረስ የሚችል ነው፡፡

ማብራሪያ የሚያስፈልገው የፕሬዚዳንቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ አቅጣጫ

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) በሳምንቱ መጀመርያ ላይ ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ላይ የ2011 ዓ.ም. የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ የሚጠቁም ንግግር አድርገዋል፡፡ በዚህ ንግግራቸው ውስጥ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ሊያስቀጥሉ የሚችሉ የተለያዩ ነጥቦችን አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ግራና ቀኞች

የኢትዮጵያ ግብርና ላይ የተመሠረቱ የኢንዱስትሪ ልማት ግቦችን ለዘመናት ስትተገብር ቆይታለች፡፡ ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥትም ሆነ የቀደሙቱ መንግሥታት ለግብርና የሰጡት ትኩረት ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ያለውን ሚናና አስተዋፅኦ የተገነዘበ ቢመስልም፣ እንደየመንግሥታቱ ፖሊሲና ስትራቴጂ የተለያየ አካሄድ ይታይ ነበር፡፡

አንዲትን ላም በመቶ ሺሕ ጥጆች የመመንዘር ቀመር

ተሽሎ የተገኘውን ዝርያ መርጦ ከብቶችን የማዳቀልና የማባዛት ታሪክ የበረዶ ዘመን ማብቂያ ላይ ከዛሬ 10,000 ዓመታት በፊት ጀምሮ የተመዘገበ ነው፡፡ ለጅምሩ ዋነኛ ምክንያቶች የነበሩትም የሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሄድና የአየር ንብረት ለውጥ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዚህ መነሻነት የተጀመረው እንስሳትን የማዳቀል ሳይንስ ለዘመናዊው ውስብስብ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች መሠረት ሆኗል፡፡

ከ18 አገሮች የተውጣጡ ኩባንያዎች የሚታደሙበት ዓውደ ርዕይ

ፌርትሬድ የተሰኘው የጀርመኑ ኩባንያ ከአገር በቀሉ ፕራና ኤቨንትስ ኩባንያ ጋር በመተባበር በቋሚነት ማዘጋጀት በጀመረው የግብርና፣ የምግብና መጠጥ ማቀነባበሪያ እንዲሁም የፕላስቲክ ኅትመትና ምርት ማሸጊያዎች የንግድ ዓውደ ርዕይ ላይ ከ18 አገሮች የተውጣጡ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ተገለጸ፡፡

ተማሪዎቹ በገበሬው ማሳ

በላይነሽ ቀለሜ የአሥረኛ ክፍል ትምህርቷን ያጠናቀቀችው በ2008 ዓ.ም. ነበር፡፡ በጊዜው ያመጣችው ውጤት ወደ መሰናዶ ትምህርት የሚያስገባት ባለመሆኑ በአቅራቢያዋ በሚገኝ ቀበሌ በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች ድጋፍ እንድታደርግ ተመርጣ መሥራት ጀመረች፡፡