Skip to main content
x

የኦጋዴን የጋዝ ልማት ፕሮጀክት ዘግይቷል

በሶማሌ ክልል በኦጋዴን ቤዚን ውስጥ የሚካሄደው የጋዝ ልማት ፕሮጀክት ከተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መዘግየቱ ተጠቆመ፡፡ ፖሊጂሲአል የተሰኘው የቻይና ኩባንያ በኦጋዴን ካሉብ፣ ሒላላና ገናሌ በተባሉ ቦታዎች የሚገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ለማልማትና ተጨማሪ የነዳጅ ክምችቶች አግኝቶ ለማልማት፣ እ.ኤ.አ. በኖቬምበር 2013 ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር ስምምነት መፈጸሙ ይታወሳል፡፡