Skip to main content
x

የአገራዊ ደኅንነት ሥጋት የሆነው የብሔር ፖለቲካ

በመጋቢት 2010 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ሲመጡ የነበረው ከልክ ያለፈ ደስታና ፌሽታ ቀስ በቀስ እየረገበ የመጣ ይመስላል፡፡ እርሳቸው ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት አገሪቱን ሲንጣት የነበረው ግጭት፣ ሁከት፣ ብጥብጥና አመፅ ከመጋቢት 2010 ዓ.ም.

የሕገ መንግሥት ትርጓሜ ጉዳይ

በኢሕአዴግ ውስጥ ከተፈጠረው የአመራር ለውጥ ወዲህ፣ አገሪቱ የተለያዩ አወዛጋቢ ጉዳዮችን እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ ከእነዚህ አወዛጋቢ ጉዳዮች ውስጥ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግዘፍ ነስቶ ግለሰቦችን፣ ፖለቲከኞችን፣ እንዲሁም የሕገ መንግሥትና የመንግሥት አስተዳደር ምሁራንን በከፍተኛ ሁኔታ እያወዛገበና እያወያየ የሚገኘው ደግሞ ሕገ መንግሥቱ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ ውሳኔዎች በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተቋማዊ ልዕልና ላይ ያጫሩት ጥያቄ

የፌዴራል ሥርዓትን የሚከተሉ ሁሉም በመላው ዓለም የሚገኙ መንግሥታት የተለያየ ቅርፅና አደረጃጀት ይኑራቸው እንጂ፣ በሁለት መሠረታዊ ባህርያት ያመሳስላቸዋል። እነዚህም በሚመሩበት ሕገ መንግሥት ተደንግጎ የተለየ የሥልጣን ክፍፍል ማድረጋቸው፣ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ሆነው በአንድ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦችን የሚያገለግሉ ከአንድ በላይ የሆኑ ነገር ግን የሚተባበሩና የሚደጋገፉ መንግሥታት መሆናቸው ነው።

የሲዳማ የክልልነት ጥያቄና አንድምታው

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ባካሄደው ጉባዔ ከተወያየባቸው አጀንዳዎች መካከል፣ የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ትኩረትን ስቦ ቆይቷል፡፡ ምክር ቤቱ ባደረገው ጉባዔ የቀረበለትን የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ እንደተቀበለም ተገልጿል፡፡

ለብሔራዊ መግባባት የማይጠቅሙ አፍራሽ ድርጊቶች ይምከኑ!

ኢሕአዴግ የደርግ መንግሥትን በትጥቅ ትግል አስወግዶ ሥልጣን ከያዘ 27 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ እነዚህ 27 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ክስተቶችን አስተናግደዋል፡፡ ከአሀዳዊ ወደ ፌዴራላዊ ሥርዓት በመሸጋገር በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ መስኮች በርካታ ጉዳዮች ተከናውነዋል፡፡

ከፖለቲካዊ ውይይቶች መሻገር ያልቻለው ብሔራዊ ማንነትና አገራዊ መግባባት

ሐሙስ ግንቦት 9 ቀን 2010 ዓ.ም. የሸራተን ሆቴል ላሊበላ አዳራሽ በመንግሥት ባለሥልጣናት፣ በምሁሩን፣ በፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ በአገር ሽማግሌዎችና በተለያዩ ግለሰቦች ተሞልቷል፡፡ በዕለቱ ያተሰበሰቡት እነዚህ ታዳሚዎች የሰባሰባቸው ዓላማ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሥር የሚገኘው ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከልና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት (UNDP) በጋራ ባዘጋጁት ‹‹ብሔራዊ ማንነትና አገራዊ አንድነት›› የሚል ርዕስ የተሰጠው ሕዝባዊ የምክክር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ነው፡፡

ኢሕአዴግ ርዕዮተ አለማዊ ለውጥ እያመጣ ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ በሚያደርጓቸው ንግግሮች የተነሳ፣ አብዛኞቹ የንግግራቸው ይዘት እስካሁን ከተለመደው ኢሕአዴጋዊ የአነጋገር ያፈነገጠና አዲስ አስተሳሰቦችን ያዘለ እንደሆነ ይገልጻል፡፡

ስለአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ዜጎች ምን ይላሉ?

ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ጤና ስለመታወኩ ጥርጣሬ ያላቸው ጥቂቶች ናቸው፡፡ መጀመርያ አካባቢ የተነሱትን ሕዝባዊ ተቃውሞዎችና አመፆች መነሻን ከራሱ አርቆ በውጭ በሚገኙና ውጫዊ በሆኑ ኃይሎች ላይ ጥሎ የነበረው ገዥው ፓርቲም፣ አሁን ጤናማ ላልሆኑት አዝማሚያዎችና ችግሮች ዋነኛ መነሻ ራሱ መሆኑን፣ በውስጡ ያሉ አጥፊ ኃይሎችን በመታገል በድጋሚ ራሱን አድሶ ወደ ቀደመው ማንነቱ እንደሚመለስ እየተናገረ ነው፡፡

ኢዴፓ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኅበረሰቡ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቀረበ

በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎች፣ መምህራንና ሠራተኞች አንድነታቸውን ከምንጊዜውም በላይ በማጠናከር አብሮነትን፣ መከባበርንና መቻቻልን የሚንዱ እኩይ ድርጊቶችን በጋራ እንዲከላከሉ የኢትዮጵያውያን  ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ጥሪውን አስተላለፈ፡፡