Skip to main content
x

የአዲስ አበባ ከተማ ቁልፍ ቦታዎችን ይዘው የቆዩ ሁለት ባለሥልጣናት ተነሱ

ላለፉት አሥር ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁልፍ ቦታዎችን ይዘው ሲመሩ የቆዩት አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃንና አቶ ኃይሌ ፍሰሐ ከሥልጣናቸው ተነሱ፡፡ አቶ ተወልደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ዋና አማካሪ፣ እንዲሁም በከተማው ሙሉ ሥልጣን ያለው የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡

አምስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አገር አቀፍ የዕርቅና የመግባባት ኮንፈረንስ ሊጠሩ ነው

አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመጀመርያ ጊዜ ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚሳተፉበት፣ አገራዊ የዕርቅና የመግባባት ኮንፈረንስ በነሐሴ ወር መጨረሻ ለመጥራት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ታወቀ፡፡

የባሌ ጎባና የደምቢዶሎ ግጭቶች

ባለፉት ሦስት ዓመታት በተለያዩ ክፍሎች የተከሰቱ ተቃውሞዎችና አመፆች፣ በአገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ያስከተሉ ነበሩ፡፡ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ጊንጪ ተነስቶ ክልሉን ያዳረሰው አመፅና ተቃውሞ፣ በአማራ ክልል በሰፊው የታየው ሕዝባዊ ተቃውሞና አመፅ የበርካቶች ሕይወት እንዲያልፍ፣ የአካል ጉዳቶች እንዲደርሱ፣ በርካቶች ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉና የአገሪቱ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጎዳ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

ብአዴን አገራዊ የለውጥ ሒደቱን ሊያደናቅፉ ይችላሉ የሚላቸውን ከፍተኛ አመራሮች ለማጥራት ማቀዱ ተሰማ

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) አዲስ የለውጥ ንቅናቄ በመላ አገሪቱ እንዲቀጣጠል በኢሕአዴግ ውስጥ ካሉ እህት ድርጅቶችና ለውጥ ፈላጊ ሕዝብ ጋር በመሆን ከፍተኛ ሚና ቢጫወትም፣ በውስጡ ያሉ አንዳንድ አመራሮቹ ለውጡን ከማስቀጠል ይልቅ ዳተኝነትና መደናገር የሚታይባቸው በመሆኑ በማጥራት ለመለየት ዕቅድ መንደፉ ታወቀ፡፡

የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሦስት ቀናት በአዲስ አበባ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በፓርላማ ሲሰየሙ ባሰሙት ንግግር፣ ከኤርትራ መንግሥት ጋር ሰላም ለመፍጠርና በሁለቱ ወንድማማች አገሮች መካከል የነበረውን የጦርነት ታሪክ ምዕራፍ ለመዝጋት ቁርጠኛ መሆናቸውን፣ የኤርትራ መንግሥትም ተመሳሳይ ዕርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አስተላልፈው ነበር፡፡

የብሔራዊ መግባባትና የዕርቅ ጉባዔ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው

የኢትዮጵያውያን ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባት ዓለም አቀፍ አስተባባሪ ኮሚቴ፣ የነሐሴ ወር ከማለቁ በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ሁሉን አቀፍ የብሔራዊ መግባባትና የዕርቅ ጉባዔ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ተነፍገናል ያሉ የሸኮ ብሔረሰብ ተወካዮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታ አቀረቡ

ላለፉት 27 ዓመታት ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ተነፍገናል ያሉ የሸኮ ብሔረሰብ አባላት በግፍ አጥተነዋል ያሉት መብት እንዲከበርላቸው፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አቤቱታ አቀረቡ፡፡