Skip to main content
x

ያገለገሉ መኪኖችን የሚያስመጡ ነጋዴዎች ‹‹ፍትሕ አጓደለብን›› በማለት ገቢዎችን ወቀሱ

ለዓመታት ያገለገሉ መኪኖችን ከውጭ በማስመጣት ሲተዳደሩ የቆዩ ነጋዴዎች፣ ‹‹የገቢዎች ሚኒስቴር ፍትሕ አጓደለብን›› በማለት ወቀሱ፡፡ ገቢዎችና ነጋዴዎች በኤክሳይስ ታክስ አወሳሰን ላይ ሳይግባቡ ለወራት ቆይተዋል፡፡

ግጭቶችን የሚያቀነባብሩት በኮንትሮባንድና በሕገወጥ ንግድ ገንዘብ ያከማቹ መሆናቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ የተጀመረውን የዴሞክራሲ፣ የሰላም፣ የልማትና የዕድገት ለውጥ ለማደናቀፍና በተለያዩ አካባቢዎች በወንድማማች ሕዝቦች መካከል ግጭቶችን በማቀነባበር ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ላይ ያሉት፣ በኮንትሮባንድና በሕገወጥ ንግድ ኪሳቸውን ያደለቡ ጥቂት ግለሰቦች መሆናቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከግጭት ወደ ግጭት የሚደረገው ሽግግር ይብቃ!

በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች አሁንም ግጭቶች አሉ፡፡ ከግጭት ወደ ግጭት የሚደረገው ሽግግር መቋጫ ባለማግኘቱ፣ በተለያዩ ሥፍራዎች ግጭቶች እየተቀሰቀሱ የንፁኃን ደም እየፈሰሰ ነው፡፡ በሰላም ወጥቶ መግባት ከባድ በሆነባቸው ቦታዎች ንፁኃን ሕይወታቸውን በከንቱ እየገበሩ ነው፡፡

በሐሰተኛ ደረሰኝ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ፈጽመዋል የተባሉ 124 ድርጅቶች እየተመረመሩ ነው

በቅርቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ ካቢኔ አባል ሆኖ የተዋቀረው የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ሕገወጥና ሐሰተኛ ደረሰኞችን ሲሸጡ የነበሩና በሐሰተኛ ሰነዶች ሲያጭበረብሩ የቆዩ 124 ድርጅቶችና ግለሰቦችን ዝርዝር ይፋ በማድረግ፣ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ሕገወጥ ግብይት በመፈጸማቸው የወንጀል ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኙ አስታወቀ፡፡

ሐሰተኛ ደረሰኝ አትመው በመሸጥ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት የፈጸሙ 124 ድርጅቶች ይፋ ተደረጉ

ትክክለኛ ማንነታቸውና አድራሻቸውን ሆነ ብለው በሐሰተኛ ሰነዶች በመሰወርና ደረሰኝ አትመው በመሸጥ ተግባር እጅ ከፍንጅ የተያዙትን ጨምሮ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ሲፈጽሙ የነበሩ 124 ሐሰተኛ ድርጅቶች መያዛቸውን አዲሱ የገቢዎች ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።