Skip to main content
x

አጉል ጀብደኝነት የአገር ችግር አይፈታም!

በበርካታ ችግሮች የተተበተበችው ኢትዮጵያ አሁንም ለበለጠ ችግር የሚዳርጋት ፈተና ከፊቷ ተጋርጧል፡፡ በማንነት፣ በአስተዳደራዊ ወሰንና በመሬት ይገባኛል እሰጥ አገባዎች ምክንያት በተለያዩ ክልሎች መካከል በሚከሰቱ አለመግባባቶች ግጭቶች በተደጋጋሚ አጋጥመዋል፡፡ አሁንም ደም ለማፋሰስ የሚያደርሱ እሰጥ አገባዎች እየተሰሙ ነው፡፡

የተሽመደመዱ ተቋማት በተመሰከረላቸው አመራሮች ነፍስ ይዘራባቸው!

ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኞቹ መንግሥታዊ ተቋማት በደመነፍስ የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ በአዋጅ ተቋቁመው ሥልጣንና ኃላፊነታቸው በግልጽ ቢደነገግም፣ ብዙዎቹ በመፈክሮች ከማጌጥ ውጪ እዚህ ግባ የሚባል አፈጻጸም የላቸውም፡፡ በፓርቲ ፖለቲካ መሥፈርት ብቻ ተሹመው የሚመሯቸው ግለሰቦችም በአንድ በኩል ከፍተኛ በሆነ የአቅም ማነስ፣ በሌላ በኩል የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ሲያባርሩ ስለሚውሉ ተቋማቱ ውርጭ እንደመታው የስንዴ ቡቃያ ጠውልገዋል፡፡

ታላቅ አገር ለመገንባት ታላቅ አስተሳሰብ ያስፈልጋል!

ታዋቂዋ ዲፕሎማት ሳህለወርቅ ዘውዴ የመጀመርያዋ ኢትዮጵያዊ የሴት ፕሬዚዳንት ተደርገው ሐሙስ ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሾሙ ባደረጉት ንግግር፣ ‹‹ታላቅ አገር የመገንባት ህልምን ዕውን ለማድረግ ከሰላም ውጪ ምንም አቋራጭም ሆነ አማራጭ የለም፡፡

መርህ አልባ እሰጥ አገባ ፋይዳ የለውም!

በመርህ መመራት ሚዛናዊና ምክንያታዊ ለመሆን ከመርዳቱም በላይ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ችግሮችን ተቋቁሞ አሸናፊ ለመሆን ያስችላል፡፡ መርህ አልባነት ግን መቅዘፊያ እንደሌለው ጀልባ ከመዋለል ውጪ ምንም አይፈይድም፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለዓመታት የዘለቀው ‹‹የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው›› ዓይነት መርህ አልባነት በተለያዩ ገጽታዎች እየተከሰተ፣ አሁንም ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸውን ወገኖች አቅጣጫ አልባ እያደረጋቸው ነው፡፡

የሐሳብና የተግባር አንድነት የሚረጋገጠው የሕግ የበላይነት ሲከበር ብቻ ነው!

ኢሕአዴግ በሐዋሳ ከተማ ያካሄደው 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የሐሳብና የተግባር አንድነት ተረጋግጦ በነፃነት፣ በግልጽነትና በአሳታፊነት በተደረገ ውይይት ውሳኔ ላይ ተደርሶ እንዲጠናቀቅ የብዙዎች ጉጉት ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ በሕዝብ ከፍተኛ ግፊት ተደርጎበት ከውስጥ ባሉ የለውጥ ኃይሎች የበላይነት ቢጀመርም፣ በተለያዩ መንገዶች ይደረጉ የነበሩ ችግር ፈጣሪ እንቅስቃሴዎች ለሰላምና ለመረጋጋት  ጠንቅ ሆነው ቆይተዋል፡፡

አገር ፀንታ የምትቆመው ቅንነትና ሰፋ ያለ ዕይታ ሲኖር ነው!

በአሁኑ ጊዜ ውስብስቡን የኢትዮጵያ ችግር ለመፍታት የአገር ፍቅር፣ ዕውቀት፣ ብስለት፣ ቅንነትና ሰፋ ያለ ዕይታ ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ጫፍ ድረስ በታሪኩ የሚታወቀው ለአገሩ ባለው ጥልቅ ፍቅርና ተወዳዳሪ በሌለው አስተዋይነቱ ነው፡፡

የሕዝብን ቀልብ የሚገዛው የላቀ ሐሳብ ብቻ ነው!

መልካም አጋጣሚዎችን በማምከን የሚታወቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ በመስዋዕትነት የተገኘውን ለውጥ ለመቀልበስ ለሚያግዝ ከንቱ ትንቅንቅ መደላድል እየፈጠረ ነው፡፡ ሕዝብ የዴሞክራሲ ጭላንጭል እያየ ተስፋ ሰንቆ አዲሱን ዓመት በተቀበለ ማግሥት፣ የተጀመረውን ለውጥ መቀመቅ የሚከት ሰቅጣጭ ጥቃት በወገኖቻችን ላይ ተፈጽሟል፡፡

ነውጠኛ ባህሪያት ለአገር አይጠቅሙም!

ኢትዮጵያን ከአምባገነናዊ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር የሚቻለው፣ ነውጠኛ ባህሪያትን አስወግዶ ዴሞክራሲያዊነትን በመላበስ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚገነባው ደግሞ ልዩነቶችን ማክበርና መቀበል ሲቻል ነው፡፡ ዴሞክራሲ አፋኝነትን፣ ጉልበተኝነትንና ጥጋበኝነትን ማስተናገድ አይችልም፡፡