Skip to main content
x

የአገራዊ ደኅንነት ሥጋት የሆነው የብሔር ፖለቲካ

በመጋቢት 2010 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ሲመጡ የነበረው ከልክ ያለፈ ደስታና ፌሽታ ቀስ በቀስ እየረገበ የመጣ ይመስላል፡፡ እርሳቸው ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት አገሪቱን ሲንጣት የነበረው ግጭት፣ ሁከት፣ ብጥብጥና አመፅ ከመጋቢት 2010 ዓ.ም.

የፍትሕ ሥርዓቱን ቁመና ገልጦ ያሳየው ፍትሕን ፍለጋ ጉዞ

ሕገ መንግሥቱ ያጎናፀፋቸውን ፍትሕ የማግኘት መብት ያጡ ወይም የተነፈጉ የተወሰኑ ግለሰቦች ላለፉት አሥር ዓመታትና አሁንም ባለመታከት እያደረጉት የሚገኘው የፍትሕ ፍለጋ ጉዞ የት ደረሰ? በጉዟቸው መሀል ያገኙዋቸው ምላሾች ተቃርኖ ስለሕግ ተርጓሚው የፍትሕ አካል ቁመና ምን ይናገራል? የሚለው የዚህ ዘገባ ትኩረት ነው። አንቀጽ 37 እንደ መነሻ

ሕገ መንግሥቱን እንደጣሰ እየታወቀ ሲሠራበት የነበረ ደንብ ለሕገ መንግሥት ትርጉም ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ተላከ

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኞችን በሕግ የመዳኘት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ገፎ የነበረና ባለሥልጣኑ ከአሥር ዓመታት በላይ ሲጠቀምበትና ሲያስፈራራበት የነበረው ደንብ ቁጥር 155/2000፣ ሕገ መንግሥቱን ተቃርኖ እንዳገኘው የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔ አስታወቀ፡፡

የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አዋጅ ከፀደቀ በኋላ የቀጠለው ፖለቲካዊ ውዝግብ

ሕገ መንግሥቱን ይጣረሳል የሚል ተቃውሞ የቀረበበት የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጫ ድምፅ ቢፀድቅም፣ በሕገ መንግሥታዊነቱ ላይ የቀጠለው ክርክር ሌላ የሕገ መንግሥታዊነት ጥያቄና ክርክር ጭሮ ወቅታዊውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ አየር ተቀላቅሏል።

የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነትና ደኅንነት ፖሊሲ ማሻሻል ለምንና እንዴት?

ሁለት አሠርት ዓመታት ለመሙላት ጥቂት ጊዜ የቀረውንና በሥራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና አገራዊ ደኅንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ለማሻሻል እየተሠራ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የአገራዊ ደኅንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር ከገባ 17 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ይኼንን ፖሊሲና ስትራቴጂ በፊታውራሪነት ያረቀቁት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነበሩ፡፡

የሕገ መንግሥት ትርጓሜ ጉዳይ

በኢሕአዴግ ውስጥ ከተፈጠረው የአመራር ለውጥ ወዲህ፣ አገሪቱ የተለያዩ አወዛጋቢ ጉዳዮችን እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ ከእነዚህ አወዛጋቢ ጉዳዮች ውስጥ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግዘፍ ነስቶ ግለሰቦችን፣ ፖለቲከኞችን፣ እንዲሁም የሕገ መንግሥትና የመንግሥት አስተዳደር ምሁራንን በከፍተኛ ሁኔታ እያወዛገበና እያወያየ የሚገኘው ደግሞ ሕገ መንግሥቱ ነው፡፡

የአስተዳደራዊ ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ የፀደቀበት መንገድ ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ?

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኅዳር 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባው ሁለት ኮሚሽኖችን ለማቋቋም በተረቀቁ የሕግ ሰነዶች ላይ ተወያይቶ በማፅደቅ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጆቹን እንዲያፀድቃቸው በላከው መሠረት ኅዳር 20 ቀን ረቂቆቹ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ ውሳኔዎች በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተቋማዊ ልዕልና ላይ ያጫሩት ጥያቄ

የፌዴራል ሥርዓትን የሚከተሉ ሁሉም በመላው ዓለም የሚገኙ መንግሥታት የተለያየ ቅርፅና አደረጃጀት ይኑራቸው እንጂ፣ በሁለት መሠረታዊ ባህርያት ያመሳስላቸዋል። እነዚህም በሚመሩበት ሕገ መንግሥት ተደንግጎ የተለየ የሥልጣን ክፍፍል ማድረጋቸው፣ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ሆነው በአንድ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦችን የሚያገለግሉ ከአንድ በላይ የሆኑ ነገር ግን የሚተባበሩና የሚደጋገፉ መንግሥታት መሆናቸው ነው።