Skip to main content
x

የኢትዮ ኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ በኢትዮጵያ በኩል ተጠናቀቀ

ኢትዮጵያ በወር 21 ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝላትን የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታ ስታጠናቅቅ፣ ኬንያ በበኩሏ ፕሮጀክቱን 70 በመቶ ማድረሷ ታወቀ፡፡ በ2008 ዓ.ም. የተጀመረው የኢትዮ ኬንያ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት፣ በኢትዮጵያ በኩል በሦስት ምዕራፎች ተከፋፍሎ እየተካሄደ ነበር፡፡

የኬንያ ትልልቅ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ዝግጅት ጀምረዋል

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አስተዳደር በኢትዮጵያ እንደሚተገብሩ ይፋ ካደረጋቸው ለውጦች መካከል የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ሙሉ በሙሉና በከፊል ወደ ግል እንደሚዛወሩ የሚለው፣ ከአገር ውስጥም ከውጭም ትልቅ ፍላጎት ፈጥሯል፡፡

የሞት ቅጣት ተወስኖባቸው የነበሩ 40 ግለሰቦችን ጨምሮ ለ332 ፍርደኞች ይቅርታ ተደረገ

በነፍስ ግድያና በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች የሞት ቅጣት ውሳኔ ያረፈባቸውን 40 ግለሰቦች ጨምሮ፣ ለ332 ፍርደኞች ዓርብ ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ይቅርታ ተደርጎላቸው ከእስር ተፈቱ፡፡ መንግሥት በፖለቲካና በሌሎች የተለያዩ ወንጀሎች ተከሰውና ቅጣት ተጥሎባቸው የነበሩትን ፍርደኞችና ክሳቸው በመታየት ላይ የነበሩ ተከሳሾችን፣ ከግንቦት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በይቅርታና ክስ በማቋረጥ እየፈታ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ ከዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ አስተናጋጅነት ውጪ ሆነች

ኢትዮጵያ 22ኛውን የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ ለማስተናገድ ከአራት አገሮች ጋር ያደረገችው ውድድር ሳይሳካላት በመቅረቱ ጉባዔውን ለማዘጋጀት ዱባይ መመረጧ ታወቀ፡፡ ጉባዔው በአፍሪካ ይስተናገዳል ቢባልም ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ከሦስት ሺሕ ያላነሱ ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሎ የሚጠበቀውን ይህንን ጉባዔ ለማዘጋጀት ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት አገሮች በተፎካካሪነት ቀርበው ነበር፡፡ ከተፎካካሪዎቹ ውስጥ ዕድሉን ያገኛሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ኢትዮጵያና ኬንያ ነበሩ፡፡

ኬንያ በደረሰው አደጋ የተደናገጠው መንግሥት ግድቦች እንዲጠኑ ትዕዛዝ ሰጠ

በቅርቡ በኬንያ ግድብ ተደርምሶ በደረሰ ጥፋት የተደናገጠው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ግድቦች ያሉበት ነባራዊ ሁኔታ ተጠንቶ እንዲታወቅ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የግድቦች ቆጠራና ደኅንነት ሁኔታ የሚያጠና ኩባንያ ለመምረጥ ያወጣው ጨረታ፣ ረቡዕ ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በይፋ ይከፈታል፡፡

የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ አዘጋጅነት ለተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ተሰጠ

ብዙ ተስፋ የተጣለበትና ኢትዮጵያና ኬንያ ተፋጥጠውበት የነበረው የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔን የማዘጋጀት ዕድል ለተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ተሰጠ፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬንያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች፣ ጆርዳን፣ ኦማንና ኢራን ሲፎካከሩበት የነበረው የንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ ኢትዮጵያ እንዴት ልታሰናዳ እንደተዘጋጀች የሚያመለክተው ሰነድ ለዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ ተልኮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ታሪካዊ መቀራረብ ላይ ያተኮረው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኬንያ ጉዞ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)ዓ.ም. ከጂቡቲና ከሱዳን ቀጥለው ባደረጉት ሦስተኛው የውጭ አገር የሥራ ጉብኝት ከሚያዝያ 28 እስከ 29 ቀን 2010 ወደ ኬንያ በማቅናት፣ በጂቡቲና በሱዳን ከተደረጉት መግባባቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ስምምነቶች ላይ ደርሰው ሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ተመልሰዋል፡፡

ንግድ ምክር ቤት የዓለም ንግድ ምክር ቤቶችን ጉባዔ ለማስተናገድ ከሦስት አገሮች ፉክክር ይጠብቀዋል 

ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር የተፋጠጠችበትንና የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔን የማዘጋጀት አቅም እንዳላት ለማሳየት ያሰናዳችውን ዝርዝር የፕሮጀክት ሰነድ ከተጨማሪ ማብራሪያዎች ጋር በማጀብ በቻይና በሚደረገው ስብሰባ እንደምታቀርብ ታወቀ፡፡

የሕገወጥ መሳሪያዎች ዝውውር በስፋት መታየቱ ተገለጸ

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አሰፋ አቢዮ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የሕገወጥ መሳሪያዎች ዝውውር በስፋት እንደታየ አስታወቁ፡፡ ኮሚሽነሩ ዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ዝውውሩን ለመቆጣጠር ባደረገው ጥረት በርካታ መሳሪያዎችን መያዝ መቻሉን ገልጸው፣ የሕገወጥ የመሳሪያዎች ዝውውር ግን ሙሉ በሙሉ ቆሟል ለማለት እንደማይቻል አስታውቀዋል፡፡

ከሞያሌ ተሰደው ኬንያ የገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር ከስምንት ሺሕ በላይ ሆነ

ከሞያሌ ተሰደው ኬንያ የገቡ ስደተኞች ቁጥር 8,592 መድረሱን የኬንያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስታወቀ፡፡ ማኅበሩ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ ይኼንን አረጋግጧል፡፡

መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በተሳሳተ መረጃ ምክንያት በፀጥታ ኃይሎች በዘጠኝ ግለሰቦች ላይ በተፈጸመው ግድያ፣ ነዋሪዎች መፈናቀል መጀመራቸው ይታወሳል፡፡

ማኅበሩ በአሁኑ ወቅት በስምንት የተለያዩ ማዕከላት ተጠልለው ለሚገኙት ተፈናቃዮች አስፈላጊውን ዕገዛ እያደረገ እንደሆነና የተፈናቃዮቹም ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ገልጿል፡፡