Skip to main content
x

ኢትዮጵያ ከዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ አስተናጋጅነት ውጪ ሆነች

ኢትዮጵያ 22ኛውን የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ ለማስተናገድ ከአራት አገሮች ጋር ያደረገችው ውድድር ሳይሳካላት በመቅረቱ ጉባዔውን ለማዘጋጀት ዱባይ መመረጧ ታወቀ፡፡ ጉባዔው በአፍሪካ ይስተናገዳል ቢባልም ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ከሦስት ሺሕ ያላነሱ ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሎ የሚጠበቀውን ይህንን ጉባዔ ለማዘጋጀት ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት አገሮች በተፎካካሪነት ቀርበው ነበር፡፡ ከተፎካካሪዎቹ ውስጥ ዕድሉን ያገኛሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ኢትዮጵያና ኬንያ ነበሩ፡፡

የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ አዘጋጅነት ለተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ተሰጠ

ብዙ ተስፋ የተጣለበትና ኢትዮጵያና ኬንያ ተፋጥጠውበት የነበረው የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔን የማዘጋጀት ዕድል ለተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ተሰጠ፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬንያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች፣ ጆርዳን፣ ኦማንና ኢራን ሲፎካከሩበት የነበረው የንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ ኢትዮጵያ እንዴት ልታሰናዳ እንደተዘጋጀች የሚያመለክተው ሰነድ ለዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ ተልኮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የአማራ ንግድ ምክር ቤት ለወጪና ገቢ ንግድ የሱዳን ወደብን ለመጠቀም የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሊመክር ነው

ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በክልሉ የሚደረገውን የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ የሚቃኝ የምክክር መድረክ በመጪው ቅዳሜ ግንቦት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚያካሄድ አስታወቀ፡፡ ‹‹ገቢና ወጪ ንግድ በአማራ ክልል ዕድሎች፣ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሐሳቦች›› በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚቀርብና በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ከክልሉ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

የንግዱ ማኅበረሰብ አንገብጋቢ ያላቸውን ችግሮችና ቅሬታዎችን በማሰባሰብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት መላክ ጀመረ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሚያዝያ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ ዋነኛ ችግሮች እንደሆኑ ተለይተው ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ይቻል ዘንድ መመርያና  ማሳሰቢያ ሰጥተው ነበር፡፡ በዚህ መሠረትም እስካሁን ከተሰባሰቡ ጥያቄዎች ውስጥ በርከት ያሉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መላካቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙስናን ተጠይፈው የመንግሥትን ነጋዴነት እንደሚያስቀጥሉ ያስታወቁበት የምክክር መድረክ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከንግዱ ማኅበረሰብ የመተዋወቂያ የምክክር መድረክ ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2010 ዓ.ም. አካሂደዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነጋዴዎቹን በተዋወቁበት የመጀመርያው ንግግራቸው ‹‹ከሀብታሞች ጋር ትገናኛለህ ስላሉኝና ደሃ መንግሥት እንዳልሆንኩ እንድታውቁ በማለት ሽክ ብዬ ነው የመጣሁት፤›› በማለት ለፈገግታና ለተግባቦት እንዲያዋዛላቸው በማድረግ መድረኩን አስጀምረዋል፡፡

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት መልካም ዕድልና ሥጋት

አፍሪካውያን በታሪካቸው ለመጀመርያ ጊዜ ሊባል በሚችል ደረጃ በርከት ብለው ፊርማቸውን ያኖሩበት ትልቅ ሰነድ እንደሆነ የተገለጸለት የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ባለፈው ሳምንት በሩዋንዳ ርዕሰ ከተማ ኪጋሊ ላይ ተፈርሟል፡፡

የንግድ ምክር ቤት አባልነት በውዴታ ወይስ በግዴታ?

የንግድ ምክር ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 341/1995 ለማሻሻል ከተለያዩ አካላት የመነሻ ሐሳቦች ቀርበው እየተመከረባቸው ናቸው፡፡ ከ70 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያላቸው ንግድ ምክር ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 314/1995 መሠረት እንደ አዲስ ሲደራጁ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት የሚል መጠሪያ ይዘው እንዲቋቋሙ ተደርጓል፡፡ ይሁንና በዚህ አዋጅ መሠረት ከተደራጁ በኋላ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ሲብላሉ ቆይተው አዋጁን ለማሻሻል ወደሚያስችሉ ተግባሮች እየገባ ነው፡፡

የንግድ ምክር ቤቶች መቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል የቀረቡ ሁለት ሐሳቦች እየተፋጩ ነው

በመላ አገሪቱ የሚገኙትን የንግድ ኅብረተሰብ ይወክላሉ የተባሉ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ከግማሽ ሚሊዮን ያላነሱ አባላትን እንደያዙ ይነገራል፡፡ እነዚህ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ቀድሞ በንግድ ምክር ቤት አሁን ደግሞ በንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች የሚል መጠሪያ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ይሁንና እነዚህን ተቋማት ከ12 ዓመታት በፊት እንደ አዲስ እንዲዋቀር ያደረገው አዋጅ ቁጥር 341/95 ከወጣበት ጊዜ አንስቶ አዋጁ በርካታ ክፍተቶች እንዳሉት ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡ በተለይም ዘርፍ ምክር ቤቶች ከታች ጀምሮ በራሳቸው መዋቅር እንዲደራጁና በየደረጃው ከንግድ ምክር ቤቶች ጋር ተጣምረው እንዲደራጁ መደረጉ፣ የንግድ ምክር ቤቶችን እንቅስቃሴ በተፈለገው ደረጃ አላራመደም በሚል የተለያዩ መከራከሪያዎች ሲቀርቡ እንደነበር ይታወሳል፡፡