Skip to main content
x

በአገር አቀፍ የውኃ ተቋማት ቆጠራ አራት ሺሕ ሰዎች ይሳተፋሉ

በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ከአራት ሺሕ በላይ ሰዎች የሚሳተፉበት አገር አቀፍ የውኃ አቅርቦት፣ ሳኒቴሽንና ኃይጂን አጠባበቅ ተቋማት ቆጠራ ሊካሄድ ነው፡፡ ቆጠራው በዋናነት በገጠርና በከተማ የውኃ ተቋማት መሠረተ ልማቶችን ከውኃ መገኛ ቦታ እስከ ማከፋፈያ ቦኖና የቤት ለቤት መስመሮችን በማካተት የሚከናወን ሲሆን፣ በዋናነት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የመጠጥ ውኃ አቅርቦትና ሥርጭት፣ እንዲሁም የውኃ ተቋማትን ጥራት ለማወቅ ይረዳል ተብሏል፡፡