Skip to main content
x

የቀድሞ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ወደ ግል ተቋማት በማቅናት ባልደረቦቻቸውን ተቀላቅለዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓይብ አህመድ (ዶ/ር) በመንግሥት የፋይናንስ ተቋማት ላይ ከወሰዷቸው ዕርምጃዎች መካከል፣ ባንኮችን ይመሩ የነበሩ የሥራ ኃላፊዎችን በአዲስ የመተካትና የማሸጋሸግ ሥራ አንዱ ነበር፡፡

በሙስና ወንጀል የተከሰሱ የአቢሲኒያ ባንክ ሠራተኞች ጥፋተኛና ነፃ ተባሉ

ትክክለኛውን የስዊፍት መክፈያ መልዕክት መለያ ቁጥር፣ የተቀባይን ስምና አድራሻ በማስተካከል፣ ሌሎችንና ራሳቸውንም ለመጥቀም በአቢሲኒያ ባንክ ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የተከሰሱ አራት ሠራተኞች ጥፋተኛና ነፃ ተባሉ፡፡

የአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንት የብሔራዊ ባንክ የቀድሞ ምክትል ገዥ እንዲተኳቸው አደረጉ

የአቢሲኒያ ባንክን ከአራት ዓመታት በላይ በፕሬዚዳንትነት እየመሩ የሚገኙት አቶ ሙሉጌታ አስማረ ‹‹በቃኝ›› በማለት የሚተካቸውን ኃላፊ ራሳቸው በመፈለግ፣ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ የነበሩትን አቶ በቃሉ ዘለቀን እንዲተኳቸው ያቀረቡትን ሐሳብ ቦርዱ ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፡፡

አቢሲንያ ባንክ በአዲሱ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት ሳቢያ ትርፉ መቀነሱን ገለጸ

ከሰሞኑ የፋይናንስ ተቋማት የ2010 ዓ.ም. አፈጻጸማቸውን የሚያመላክቱ ሪፖርቶችን ለአክሲዮን ባለድርሻዎች ይፋ እያደረጉ ነው፡፡ ከእነዚህ መካከልም ቅዳሜ፣ ኅዳር 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ዓመታዊ ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው አቢሲኒያ ባንክ እንዳስታወቀው በ2009 ዓ.ም.

አቢሲኒያ ባንክ ሒሳቤን በአይኤፍአርኤስ መሥራቴ ትርፌን ቀነሰው አለ

በአዲሱ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃ (አይኤፍአርኤስ/IFRS) በመጠቀም ዓመታዊ ሒሳቡን የሠራው አቢሲኒያ ባንክ የ2010 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 765.7 ሚሊዮን ብር ማትረፍ መቻሉንና አስታወቀ፡፡ ይህ ትርፍ በቀድሞው የሒሳብ ሪፖርት አሠራር ቢሆን 857.5 ሚሊዮን ብር ይሆን እንደነበር አስታውቋል፡፡

አቢሲኒያ ባንክና ንብ ኢንሹራንስ በ9.3 ሚሊዮን ብር ዕዳ ተከሰሱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ፣ ኢቢሲኒያ ባንክንና ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አክሲዮን ማኅበርን በ9.3 ሚሊዮን ብር ዕዳ ከሰሰ፡፡ ኢንተርፕራይዙ በባንኩና በኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ ላይ ክስ የመሠረተው፣ አባስ ኮንስትራክሽን በሚባል ሥራ ተቋራጭ ለሚያስገነባቸው ባለስምንት ፎቅ ሦስት ብሎኮች የሰጡትን ዋስትና ተግባራዊ ባለማድረጋቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

አቢሲንያ ባንክን ለመዝረፍ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ የሚገኘው የኢቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፍ በስለት በማስፈራራት ዘረፋ ለመፈጸም የሞከሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ፡፡ ሪፖርተር በቅርንጫፍ ባንኩ ተገኝቶ ከዓይን እማኞችና ከመርማሪ ፖሊሶች ለመረዳት እንደቻለው፣ ማክሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ገደማ ወደ ባንኩ የገቡ ዘራፊዎች በስለት በማስፈራራት በባለ 50 ኪሎ ግራም ሁለት የማዳበሪያ ከረጢቶች አንደኛው ውስጥ ከ2.7 ሚሊዮን ብር በላይ በማጨቅ ዘርፈው ለመወሰር ሙከራ ቢያደርጉም፣ በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ርብርብና በትራፊክ መጨናነቅ ሳቢያ ሊያዙ መቻላቸው ታውቋል፡፡

አቢሲንያ ባንክ አዲስ ዓርማ ይፋ አደረገ

አቢሲኒያ ባንክ ከ22 ዓመታት በላይ በፋይናንስ ሥራ መስክ የቆየና ከደርግ መንግሥት በኋላ ኢንዱስትሪውን ከተቀላቀሉ ቀዳሚ የግል ባንኮች አንዱ ነው፡፡ ባንኩ ሥራ ሲጀምር መለያው ወይም የኩባንያው ብራንድ በማድረግ እስከ ዛሬ ሲገለገልበት የቆየውን ዓርማ አሻሽሏል፡፡ ከቅዳሜ፣ ግንቦት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በተሻሻለው አዲሱ ዓርማ መጠቀም መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡

አቢሲኒያ ባንክ መለያ አርማውን ቀየረ

አቢሲኒያ ባንክ ላለፉት 22 ዓመታት ሲጠቀምበት የቆየውን መለያ አርማ (ብራንድ) በማሻሻል አዲስ መለያ ሆኖ የሚያገለግለውን አርማ ቅዳሜ ግንቦት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል፡፡

የደርግን ውድቀት ተከትለው የፋይናንስ ኢንዱስትሪውን ከተቀላቀሉት ባንኮች አንዱ የሆነው አቢሲኒያ ባንክ፣ ሲገለገልበት የቆየውን አርማ በአዲስ የተካው ባንኩን ይበልጥ ለመግለጽ የሚያስችል እንዲሆን በማሰብ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ የባንኩን የዕድገት ውጥን ለማሳካት የአርማ ለውጡ ዴሎይት በተባለ ዓለም አቀፍ ኩባንያ በቀረበ ምክረ ሐሳብ መሠረት ተግባራዊ መሆኑን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አስማረ ገልጸዋል፡፡