Skip to main content
x

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሚያደርጉት ውይይት የሚሰክኑት መቼ ነው?

ከወራት በፊት ወደ አሜሪካን ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ በጉብኝታች ወቅት እዚያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከተናገሩት ንግግር መካከል የሚጠቀሰው፣ የሥልጣን ዘመናቸው የመጨረሻ ግብ በአገሪቱ ነፃ፣ ፍትሐዊና ገለልተኛ ምርጫ ማድረግ እንደሆነ ነበር፡፡

የአገር ጉዳይ የልጆች ጨዋታ አይደለም!

በዚህ ዘመን ምራቃቸውን የዋጡ ሰዎች የወጣቶች መካሪ፣ የአገር ሽማግሌ፣ የትውልድ አርዓያና የተጣመመውን የሚያቀና መሆን ሲገባቸው፣ እንደ ሠፈር ጎረምሳ የብጥብጥና የሁከት ምንጭ ሲሆኑ ያሳዝናል፡፡ በፖለቲካው መስክ ከ40 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩ ፖለቲከኞችና የሚመሩዋቸው ድርጅቶች አድረው ቃሪያ ሲሆኑ ያሳፍራል፡፡ ለዓመታት በመሣሪያ ያልተሳካላቸውንና በሰላማዊ ጥሪ ያገኙትን መልካም አጋጣሚ የሚያበላሹ ያሳቅቃሉ፡፡

ከ500 በላይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ወታደሮች ካምፕ ሊገቡ ነው

ለረዥም ጊዜ በበረሃ በመቆየታቸው ቤት ንብረታቸው በመፍረሱና መሄጃ በማጣታቸው የትም መሄድ የማይችሉ 550 ያህል የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ካምፕ እንዲገቡ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን፣ የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አስታወቁ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሎ ከፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር

ማክሰኞ ኅዳር 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር በአገሪቱ ስለተጀመረው ለውጥ፣ እንዲሁም በመጪው ዓመት ስለሚደረገው ምርጫ አስመልክቶ ተወያዩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተወያዩት ጥሪ ከተደረገላቸው የ80 ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ነው፡፡

መጪው ምርጫና የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሸክም

በ1993 ዓ.ም. የተፈጠረው የሕወሓት የመሰንጠቅ አደጋና አሸንፎ የመውጣት ፖለቲካዊ ትግል በወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የፖለቲካ ሕይወት ላይ ትልቅ አሻራ ነበረው። የሚቀርቧቸው እንደሚናገሩት ደግሞ ከአሻራነት በላይ የሕይወት መስመራቸው የተቀየረበት እንደሆነ ይናገራሉ።

በቀጣዩ ምርጫ ላይ ለመነጋገር በአስተማማኝ ቁመና ላይ መገኘት ያስፈልጋል!

ለሚቀጥለው ምርጫ ከወዲሁ ለመነጋገር እንደ መንደርደሪያ የሚሆን ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አገር ውስጥ ካሉና በቅርቡ ከውጭ ከገቡ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ለመወያየት፣ ለማክሰኞ ኅዳር 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንደ አዲስ ለሚደራጀው የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም አመራርነት መታጨታቸው ተሰማ

መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ በስደት ይኖሩ ከነበረበት አሜሪካ የተመለሱት የቀድሞ ፖለቲከኛና የፖለቲካ ፓርቲ አመራር የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ አዲስ ለሚደራጀው ብሔራዊ ምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ኃላፊ እንዲሆኑ ታጩ።

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ነገ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ

ከአንዴም ሁለት ጊዜ ለእስር ከተዳረጉ በኋላ የተፈቱትና መቀመጫቸውን አሜሪካ ያደረጉት የሕግ ባለሙያዋና የቀድሞ የቅንጅት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ሐሙስ ጥቅምት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ማለዳ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ፡፡