Skip to main content
x

ገቢዎችና ጉምሩክ በታክስ አስተዳደር ችግሮች እየተፈነ ነው

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የ2011 ዓ.ም. የሩብ ዓመት አፈጻጸሙንና የተቋሙን ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች በማስመልከት ማክሰኞ፣ ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ነፃነት አበራ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡

በሦስት ወራት ሊሰበሰብ ከታቀደው የታክስ ገቢ ውስጥ 10 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ አልተቻለም

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በ2011 ዓ.ም. የመጀመርያ ሩብ ዓመት ለመሰብሰብ ካቀደው ገቢ ውስጥ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ እንዳልቻለ ተመለከተ፡፡ በዚህ ወር ከ23 ቢሊዮን ብር በላይ ይሰበሰባል ተብሏል፡፡  

በታክስ ሥርዓቱ ውስጥ ምላሽ የሚፈልጉ የለውጥ ጥያቄዎች

የታክስ አስተዳደር ጉዳዮችን በተለመከተ የማያባራ ስሞታ የሚቀርብባቸው ችግሮች በተለያዩ የመንግሥት ሥርዓቶች ውስጥ ሲነሱ ቆይተዋል፡፡ የንግድ ማኅበረሰቡ ከታክስ አስተዳደሩ ጋር የተያያዙ ችግሮቹን በጋራና በተናጠል በማቅረብ ሊስተካከሉ ይገባቸዋል ብለው ያመኑባቸውን ሐሳቦች ለመንግሥት በማቅረብ ለዓመታት ዘልቀዋል፡፡

ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የታክስ ወኪልነት የሙያ ሥራን የሚደነግግ መመርያ ሊተገብር ነው

ግብር ከፋዮች ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጋር በታክስ አከፋፈልና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ በወኪሎቻቸው አማካይነት ከባለሥልጣኑ ጋር የሥራ ግንኙነት ማድረግ የሚያስችሉበት አሠራር ሊተገበር ዝግጅት መጀመሩ ይታወቃል፡፡

ለንግዱ ኅብረተሰብ በአንዴ የቀረቡት 21 ረቂቅ የታክስ መመርያዎች

የኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣንና የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣ ባልተለመደ አኳኋን 21 ረቂቅ መመርያዎችን በማሰናዳት ከንግዱ ኅብረተሰብ ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡ ሰኔ 5 እና 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ውይይት ከተደረገባቸው ረቂቅ መመርያዎች መከካል 11ዱ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በኩል የቀረቡ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ረቂቅ መመርያዎችም በባለሥልጣኑ ለውይይት የቀረቡ ነበሩ፡፡

በእነ አቶ መላኩ ፈንታ መዝገብ ክሳቸው ያልተቋረጠላቸው ተከሳሾች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታ አቀረቡ

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተለያዩ ክፍሎች ከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የነበሩና በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ተካተው ክስ የተመሠረተባቸው ስምንት ግለሰቦች፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. አቤቱታ አቀረቡ፡፡

ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ግብር የሚፈለግበት ኪንግናም ንብረቱ ታገደ

በኢትዮጵያ የመንገድ ግንባታ ዘርፍ ለ20 ዓመታት ያህል ሲሳተፍ የቆየው ኪንግናም የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ ኩባንያ፣ ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መክፈል የነበረበትን ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ግብር ባለመክፈሉ፣ የኩባንያው የተለያዩ ንብረቶች ታገዱ፡፡ ኮሪያዊው ሥራ አስኪያጅም ከአገር እንዳይወጡ ታዘዘ፡፡

የታክስና የጉምሩክ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ከ15 በላይ መመርያዎች ይፋ ሊሆኑ ነው

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከ15 በላይ አዳዲስ ረቂቆችና ማሻሻያ የተደረገባቸውን መመርያዎች ለመተግበር ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ከጉምሩክና ከታክስ አስተዳደር ጋር ተግባራዊ ያደርጋቸዋል ተብሎ በሚጠበቁት በእነዚህ አዳዲስ መመርያዎችና ማሻሻያዎች ላይ፣ ከንግድ ኅብረተሰቡ ጋር እንደሚመክርባቸው ተገልጿል፡፡

አነስተኛና መካከለኛ አልባሳት አምራቾች ያልተገባ የጉምሩክ ቀረጥ መጠየቃቸውን ተቃወሙ

በአነስተኛና በመካከለኛ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት አምራችነት ሥራ ላይ እንደተሰማሩ የገለጹ አምራቾች፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከሕግ አግባብ ውጪ ለአምራቾች የተፈቀደውን የቀረጥ ማስከፈያ ሒሳብ ተላልፎ በመጠየቃቸው ያልተገባ ቀረጥን በመቃወም አቤቱታ አቀረቡ፡፡