Skip to main content
x

በዓለም ባንክ ድጋፍ 200 ሺሕ አቅመ ደካሞች በምግብ ዋስትና ፕሮግራም ሊታቀፉ ነው

የዓለም ባንክ ከመደበው 450 ሚሊዮን ዶላር በጀት 70 በመቶ ድርሻ የያዘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በተያዘው በጀት ዓመት ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ 200 ሺሕ ነዋሪዎችን በምግብ ዋስትና ፕሮግራም እንደሚያቅፍ አስታወቀ፡፡ አስተዳደሩ ከተያዘው በጀት 32 ሺሕ ለሚጠጉ ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ አቅመ ደካሞች ቀጥታ ወርኃዊ ክፍያ ለመፈጸም፣ 168 ሺሕ የሚሆኑ ነዋሪዎች ደግሞ በማኅበረሰብ አቀፍ ፕሮግራም ታቅፈው የተለያዩ ሥራዎችን ሠርተው ወርኃዊ ክፍያ እንዲያገኙ ዕቅድ አውጥቷል፡፡

የዓለም ባንክ በስድስት ወራት ብቻ የ1.8 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ካሮሊን ተርክ ሐሙስ ታኅሳስ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ጋር የ470 ሚሊዮን ዶላር ብድር ስምምነቶችን ሲፈርሙ እንደገለጹት፣ ባንኩ በተቻለው ፍጥነት የፋይናንስ ድጋፎችን ለማድረግ ካለው ፍላጎት በመነሳት እ.ኤ.አ. በ2017 ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ የ1.8 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡

በመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት መስክ ለውጦችን ያመላከተው የስታትስቲክስ ኤጀንሲ ጥናት በርካታ ጉድለቶች እንዳሉ ጠቆመ

በለጋሾችና በኢትዮጵያ መንግሥት በሚመደብ በጀት ሲተገበሩ በቆዩት የመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ላይ በየጊዜው ለውጦች ቢመዘገቡም፣ በርካታ ጉድለቶች እንደሚታዩ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ጥናት አመላከተ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ረገድ አፋርና ሶማሌ ክልሎችና የድሬዳዋ አስተዳደር ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

የጣሊያን መንግሥት የ15 ሚሊዮን ዩሮ ብድር በዓለም ባንክ በኩል ለሥራ ፈጣሪ ሴቶች አቀረበ

በኢትዮጵያ አነስተኛና ጥቃቅን የሥራ መስኮች ለተሰማሩ ከ20 በላይ ሥራ ፈጣሪ ሴቶች የሚውል የ15 ሚሊዮን ዩሮ (በወቅቱ ምንዛሪ ከ465 ሚሊዮን ብር በላይ) ብድር በዓለም ባንክ በኩል ያቀረበው የጣሊያን መንግሥት፣ በቴክኒክና በሥልጠና መስክም ድጋፍ መስጠት እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጨማሪ 200 ሺሕ ነዋሪዎችን በምግብ ዋስትና ፕሮግራም አካተተ

በፌዴራል ደረጃ ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም 123.9 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸውን ነዋሪዎች ለማቋቋም የጀመረውን ፕሮግራም፣ ቀደም ሲል ከያዘው 123 ሺሕ በተጨማሪ 200 ሺሕ ነዋሪዎችን አካተተ፡፡

በድርቅ የተፈተነው ሴፍቲኔት 600 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ አገኘ

የዓለም ባንክ በሁለት ፕሮግራሞች 1.3 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታና ብድር ሰጥቷል እየተከሰተ ባለው ተከታታይ ድርቅ እየተፈተነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴፍቲኔት ፕሮግራም፣ ከዓለም ባንክ 600 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ አገኘ፡፡ የዓለም ባንክ ዓርብ መስከረም 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በገጠሪቱ ኢትዮጵያ እየተተገበረ ለሚገኘው ሴፍቲኔት ፕሮግራም ከሰጠው ዕርዳታ በተጨማሪ፣ በኢትዮጵያ ፍትሐዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ለተነደፈው ፕሮግራም 700 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጥቷል፡፡