Skip to main content
x

በግማሽ ዓመት ከ8,700 በላይ ሰዎች በተሽከርካሪ አደጋ የሞትና የአካል ጉዳት ሰለባ ሆነዋል

በስድስት ወራት ውስጥ በደረሱ የተሽከርካሪ አደጋዎች ሳቢያ 8,764 ሰዎች ለሞት፣ ለከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ያስታወቀው የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ፣ በተለይ ገጭተው በሚያመልጡ አሽከርካሪዎች ሳቢያ የሚደርሰው ጉዳት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን አስታወቀ፡፡

በመድን ዘርፉ የተደራሽነትና የአዳዲስ አገልግሎቶች ጥያቄ

የኢትዮጵያ የገንዘብ ተቋማት አጠቃላይ አቅም ከሰሃራ በታች አገሮች አንፃር ሲታይ ብዙ እንደሚቀረው ሲነገር ሲተነተን ቆይቷል፡፡ ዘርፉ ለአገር በቀል ኩባንያዎች ብቻ ክፍት በመደረጉ፣ ከውጭ ለሚመጣበት ውድድር ያልተገባ ከለላ እንደተሰጠው የሚከራከሩ አካላት፣ በተደራሽነቱ ረገድም ዝቅተኛ አፈጻጸም የሚታይበት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ንብ ኢንሹራንስ በድጋሚ ያካሄደው የቦርድ አመራሮች ምርጫ ውጤት አልፀደቀለትም

የንብ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ባለአክሲዮኖች ያካሄዱትን የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ዓመት በመሻሩ በድጋሚ እንዲካሄድ በወሰነው መሠረት ዳምግም ምርጫ ቢካሄድም፣ የአዳዲስ አመራሮችን ውጤት እስካሁን እንዳላፀደቀው ተሰማ፡፡

ፀሐይ ኢንሹራንስ የገበያ ድርሻውን በ13 በመቶ በማሻሻል የ280 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

ፀሐይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ባለፈው ዓመት በነበረው ውጤታማ እንቅስቃሴ ሳቢያ ገቢውን በማጠናከር በኢንዱስትሪው ውስጥ የያዘውን የገበያ ድርሻ በ13 በመቶ ማሳደግ እንደቻለ አስታወቀ፡፡ ከ280 ሚሊዮን በላይ ዓረቦን ሰብስቧል፡፡

ቡና ኢንሹራንስ ካፒታሉን ወደ 200 ሚሊዮን ብር አሳደገ

የቡና ኢንሹራንስ ባለአክሲዮኖች የኩባንያውን ካፒታል በእጥፍ ለማሳደግና የሕይወት መድን መስጠት የሚጀምርበትን ውሳኔ አሳለፉ፡፡ ኩባንያው የ2010 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸሙን ይፋ ባደረገበት ጉባዔ ላይ የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ ባቀረበው ሐሳብ መሠረት ካፒታሉ በእጥፍ ጨምሮ 200 ሚሊዮን ብር እንዲሆን ተወስኗል፡፡

አፍሪካ ኢንሹራንስ ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዘግቧል

በመድን ኢንዱስትሪው ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ ከዘለቁ አምስት የግል ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው አፍሪካ ኢንሹራንስ፣ በ2010 ዓ.ም. ከታክስ በፊት 71.5 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡ ጠቅላላ ሀብቱም ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ተሻግሯል፡፡  

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ከ81 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዘገበ

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ በ2010 ዓ.ም. ከታክስ በፊት 81.4 ሚሊዮን ብር ማትረፉ ተገለጸ፡፡ ያስመዘገው ትርፍ በ141 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ ኩባንያው የሥራ አፈጻጸሙን በሚያመለክተው ሪፖርት ይፋ እንዳደረገው፣  ዓምና ያገኘው የትርፍ መጠን በኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ የትርፍ ዕድገት ካስመዘገቡ መካከል እንደሚያሠልፈው ተመልክቷል፡፡

መድን ድርጅቶች ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ አስመዘገቡ

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በ2010 ዓ.ም. 1.33 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገባቸው ተመለከተ፡፡ 3.7 ቢሊዮን ብር ለካሳ ክፍያ አውለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይህንኑ አመላክቷል፡፡ ከሰሞኑ ሪፖርቶቻቸውን ይፋ ካደረጉ ኩባንያዎች የተገኘው መረጃም 17ቱ መድን ድርጅቶች በ2010 ዓ.ም. ከታክስ ተቀናሽ በኋላ ያስመዘገቡት ትርፍ ከ2009 ዓ.ም. አኳያ በ22.5 በመቶ ብልጫ አለው፡፡