Skip to main content
x

በዱር ሰደድ እሳት የሚፈተኑ ፓርኮች

ሲያሻው ምድር ለምድር፣ ሲለው ከቋጥኝ ቋጥኝ፣ አሊያም ሣርና ዛፎችን እያያያዘ የመንቀልቀል ባህሪ ያለውን ሰደድ እሳት እንኳንስ በባህላዊ መንገድ በሠለጠነውም ቢሆን መመከቱ ቀናትን የሚፈጅ ነው፡፡ እሳቱ ተረትቶ እጅ እስከሚሰጥም ያገኘውን ሁሉ አመድ ያደርጋል፡፡