Skip to main content
x

የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ የማምጣት ፈተናና የተደቀነው ማኅበራዊ ቀውስ ሥጋት

የ2011 ዓ.ም. የፌዴራል መንግሥት ረቂቅ በጀት ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ይዘው የቀረቡት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ያደረጉት የበጀት መግለጫ ንግግርን የአገሪቱን ኢኮኖሚ ጠፍረው ያሰሩ ችግሮችንና ለችግሮቹ ፈጣን መፍትሔ ካልተገኘ ሊፈጠር የሚችለውን ማኅበራዊ ቀውስ ያመላከተ ነበር፡፡

ሜቴክ ከፍተኛ የሀብት ብክነት እንዳለበት አመነ

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከፍተኛ የሀብት ብክነትና የውጤታማነት ችግር እንዳለበት አመነ። ኮርፖሬሽኑ ይህንን ያስታወቀው ረቡዕ ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለፓርላማ የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት፣ ለተሰነዘረበት ከፍተኛ የሀብት ብክነት ወቀሳ ምላሽ ሲሰጥ ነው።

ኢሕአዴግ ባድመ ለኤርትራ እንድትሰጥ የወሰነውን የአልጀርስ ስምምነት ሙሉ በሙሉ መቀበሉን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማክሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፣ ባድመ ለኤርትራ እንድትሰጥ የወሰነው የአልጀርሱን ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ እንደወሰነ አስታወቀ፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አመሻሸ ላይ ባወጣው መግለጫ ከ20 ዓመታት ውዝግብና እሰጥ አገባ በኋላ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የድንበር ማካለል ኮሚሽን የወሰነውንና በሁለቱ መንግሥታት በአልጀርስ የተፈረመውን ስምምነት እንደሚቀበል ይፋ ሲያደርግ ምክንያቱ ምን እንደሆነ አሥፍሯል፡፡

ቻይናዊው የኦሞ ኩራዝ አምስት ስኳር ፕሮጀክት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሳቸው በገለልተኛ አካል እንዲታይ ጥያቄ አቀረቡ  

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው እ.ኤ.አ. ጁላይ 25 ቀን 2017 በቁጥጥር ሥር የዋሉትና ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት የኦሞ ኩራዝ አምስት ስኳር ፕሮጀክት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚኒተር ዩዋን ጂያሊን፣ የተመሠረተባቸው ክስ በገለልተኛ አካል እንዲታይላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በደብዳቤ ጥያቄ አቀረቡ፡፡

ከውጭ የተገዙ ምርቶች በተመሳሳይ ወቅት ጂቡቲ በመድረሳቸው የትራንስፖርት መጨናነቅ ተፈጠረ

መንግሥት ከውጭ በገፍ የገዛቸው ምርቶች በተመሳሳይ ወቅት ጂቡቲ ወደብ በመድረሳቸው፣ በተለይ ከወደብ እስከ ጋላፊ ያለው መንገድ ክፉኛ በመበላሸቱ የትራንስፖርት መጨናነቅ እንደተፈጠረ ተመለከተ፡፡ መንግሥት ለ2010/2011 ዓ.ም. ምርት ዘመን የሚያስፈልግ 1.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በ600 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ግዥ እየፈጸመ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ገበያ ለማረጋጋት 200 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ በ1.6 ቢሊዮን ብር በሚሆን ወጪ፣ እንዲሁም 400 ሜትሪክ ቶን ስኳር በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡

ሜቴክ በያዛቸው የስኳርና የማዳበሪያ ፋብሪካዎች ላይ መንግሥት የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በተደጋጋሚ ጊዜ ቢራዘምለትም ሊያጠናቅቅ ያልቻላቸውን አንድ የስኳርና አንድ የአፈር ማዳበሪያ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ፣ መንግሥት ውሳኔ እንዲሰጥበት ጥያቄ መቅረቡ ተገለጸ፡፡ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ግርማ አመነቴ (ዶ/ር) ሐሙስ ሚያዝያ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለፓርላማ ሲያቀርቡ እንደተናገሩት፣ የጣና በለስ ቁጥር ሁለት የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ከሜቴክ ተነጥቆ በአዲስ ኮንትራክተር ሥራውን ለማስቀጠል እየተመከረ ነው፡፡

2.5 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የሚያመርተው ኦሞ ኩራዝ ሁለት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

ከ6.67 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት የተገለጸው የኦሞ ኩራዝ ሁለት ስኳር ፋብሪካ የምርት ሥራ መጀመሩ ተገለጸ፡፡ ባለፈው ዓመት ፋብሪካው የምርት ሙከራ ጀምሮ ነበር፡፡ ሆኖም በድንገተኛ ዝናብ ምክንያት ሙከራው ቢቋረጥም፣ ከታኅሳስ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ማምረት እንደጀመረ የስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጋሻው አይችሉህም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ፋብሪካው መጋቢት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. የሙከራ ምርት መጀመሩ ይታወሳል፡፡

የለስላሳ መጠጦች አምራች ኩባንያ ኦሮሚያ ውስጥ 720 ኩንታል ስኳር ተወረሰበት

በኢትዮጵያ ሦስት ከተሞች ኮካ ኮላና ሌሎች ለስላሳ መጠጦችን የሚያመርተው ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ኩባንያ፣ ለባህር ዳር ፋብሪካው ሲያጓጉዘው የነበረው 720 ኩንታል ስኳር በኦሮሚያ ክልል ጎሃፅዮን ከተማ ተወረሰበት፡፡

ግልብ ገበያ

በአንድ ሳምንት ውስጥ ሦስት ገጠመኞች አስተናግጃለሁ፡፡ ገጠመኝ አንድ! በአውሮፓውያን አቆጣጠር ተሠልታ፣ የመንግሥት ታክስና ሌሎች ክፍያዎች ተቀናንሰውላት ከምትደርሰኝ ደመወዜ አስቤዛ ለመግዛት ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. (ኦክቶበር 29) በከተማችን ከሚታወቁ ሱፐር ማርኬቶች ወደ አንዱ ጎራ አልኩ፡፡ የምፈልጋቸውን ዕቃ መራርጬ ወደ ገንዘብ ተቀባይዋ አመራሁ፡፡