Skip to main content
x

የኢሕአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶች ስብሰባና የሚጠበቁ ውሳኔዎች

ኢትዮጵያ አንድ መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ያላት አገር እንደሆነች መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በቆዳ ስፋትም ሆነ በሕዝብ ብዛት በግንባር ቀደምትነት ከሚጠሩ የአፍሪካ አገሮች መካከል አንዷ ነች፡፡ የአገሪቱ የሕዝብ ቁጥር ባለፉት 50 ዓመታት በእጥፍ እንዳደገ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የአገሪቱ የሕዝብ ቁጥር እያደገ ከመምጣቱ ጋር በተያያዘ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲስፋፉና ሲገነቡ ይታያል፡፡ በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዓመት በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ወጣቶች ከከፍተኛ ትምህርት እንደሚመረቁ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡ መንግሥት በየዓመቱ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎችን እያስመረቀ ቢገኝም፣ ተመርቀው በግላቸውም ሆነ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተቀጥረው ወደ ሥራ የሚገቡ ወጣቶች ቁጥር እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ አገሪቱም ካላት የሕዝብ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች እንዳልሆነ ይነገራል፡፡

የኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የዶ/ር ነጋሶን የሕክምና ወጪ ለመሸፈን ወሰነ

የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት የነበሩት ነጋሶ ጊዳዳ (ዶ/ር)፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የሕክምና ወጪያቸውን ሲሸፍንላቸውና መኪና ሊገዛላቸው እንደሆነ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ ‹‹የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ድጋፍ እንዲሆነኝ የተወሰነ ገንዘብ ሰጥቶኛል፡፡ በተረፈ መኪና ይገዛልሀል ተብዬ እርሱን እየጠበቅኩ ሲሆን፣ የሕክምና ወጪዬን በተመለከተ ደግሞ በምፈልግበት ጊዜ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ወጪው እንደሚሽፈን ተገልጾልኛል፤›› ብለዋል፡፡

በሕወሓት ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች ሚና የነበራቸው አመራሮች ኃላፊነት እንደሚወስዱ ተገለጸ

ከጥር 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በመቀሌ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የከፍተኛ አመራሮች ኮንፈረንስ፣ በማዕከላዊ ኮሚቴው ግምገማ ወቅት እንደተደረገው ሁሉ እስከ ታችኛው ድረስ ባሉ የድርጅቱ መዋቅሮች ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች ሚና የነበራቸው አመራሮች ኃላፊነት እንደሚወስዱ፣ የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ለሪፖርተር ገለጹ።

የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

ሰባተኛው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከፍተኛ አመራሮች ድርጅታዊ ኮንፈረንስ በመቐለ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተወሰኑ ውሳኔዎችን እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ለማስረፅ የሚረዳ አቅጣጫ የሚቀመጥበት እንደሆነ ተጠቁሟል።

ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት እንደሚሆኑ ተጠቆመ

ላለፉት በርካታ ዓመታት የፌዴራል መንግሥት ካቢኔ አባልና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር)፣ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ የክልሉ ፓርቲ ሕወሓት መወሰኑን አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሪፖርተር ገለጹ። 

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በአገሪቱ የፀጥታ ጉዳይ ላይ እየመከረ ነው

ሰላሳ ስድስት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሰባ፣ በአገሪቱ የፀጥታ ጉዳይ ላይ እየመከረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደጠቆሙት የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ማክሰኞ ታኅሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ የተጀመረ ሲሆን፣ በዋናነት አገሪቱ ባጋጠማት የፀጥታ ጉዳይ ላይ እየመከረ መሆኑ ታውቋል፡፡

ልማታዊ መንግሥትና የገጠመው የጥገኛ ገዥ መደብ ምሥረታ ጣጣ

የአፍሪካ አኅጉርን እንዴት ከድህነት አዘቅጥ አውጥቶ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትና መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግርር ማረጋገጥ ይቻላል በሚል ንድፈ ሐሳብ ላይ ያተኮረ፣ የዶክትሬት ማሟያ ጥናታዊ ምርመራቸውን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ እያሰናዱ እንደበር ይታወሳል፡፡

የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ራሱን ያየበት መነጽር

የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ለ35 ቀናት የግምገማ ስብሰባ ላይ ከርሟል፡፡ በግምገማውም የድርጅቱ ስትራቴጂካዊ አመራር ክልላዊና አገራዊ ተልዕኮውን ከመወጣት አንፃር ያለበትን ቁመና ለማየት የሚያስችል ሥር ነቀል ግምገማ ማካሄዱን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ለ35 ቀናት ግምገማ ላይ የቆየው የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዋቀረ

ለ35 ቀናት በግምገማ ላይ የከረመው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት (ትግራይ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴውን እንደገና በማዋቀር ተጠናቀቀ፡፡ ሐሙስ ኅዳር 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ከአንድ ወር በላይ የፈጀ ስብሰባውን ያጠናቀቀው የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ዘጠኝ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል፡፡ ባወጣው የአቋም መግለጫም ራሱ ላይ አካሂጃለሁ ያለውን ሥር ነቀል ግምገማ በዝርዝር አስታውቋል፡፡

ቃልና ተግባር ሳይጣጣሙ መንግሥት የሕዝብ አመኔታ እንደማያገኝ ማመን አለበት!

የገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ መሥራችና ዋነኛ አባል የሆነው የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ለ35 ቀናት ያካሄደውን የግምገማ ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ባወጣው መግለጫ፣ በራሱ ላይ የሰላ ሒስ በማካሄድ የእርምት ዕርምጃና የአመራር ሽግሽግ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ሕወሓት ሕዝባዊ ወገንተኝነቱ አስተማማኝ መሆኑን፣ ፈተናዎች በገጠሙት ቁጥር ራሱን በሚገባ እየፈተሸና ወቅቱን የጠበቀ ማንኛውም ዓይነት ዕርምጃ በመውሰድ ጥንካሬዎቹን የሚያጎለብት፣ ድክመቶቹን ያለምሕረት በማስወገድ በመስዋዕትነት የደመቀ ታሪክ መሥራት የቻለ አመራር ባለቤት መሆኑን፣ ከእህትና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በተከፈለ እጅግ ከባድ መስዋዕትነት አዲሲቷን ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ዕውን ለማድረግ መቻሉን አስታውቋል፡፡ በአገሪቱም ታሪክ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና የህዳሴ ምዕራፍ መከፈቱን በአፅንኦት ገልጿል፡፡