Skip to main content
x

ፌዴራል ፖሊስ በአቶ ኢሳያስ ዳኘው ላይ ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደረገ

የፌዴራል ፖሊስ በአቶ ኢሳያስ ዳኘው ላይ ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውደቅ አደረገው፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ ኢሳያስ ዳኘው የከፍተኛ ፍርድ ቤት አሥረኛ ወንጀል ችሎት በ50 ሺሕ ብር ዋስትናና ከአገር እንዳይወጡ ዕግድ በመጣል ከእስር እንዲፈቱ የሰጠውን ትዕዛዝ አፀና፡፡

ፌዴራል ፖሊስ በአቶ ኢሳያስ ላይ ያቀረበውን የወንጀል ጥርጣሬ መነሻ ሐሳብ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ያደረጉት ለሦስተኛ ጊዜ ነው፡፡

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው በታሰሩት የቀድሞ የማዕከላዊ አሥር መርማሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ

በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) ከ2002 ዓ.ም. እስከ 2010 ዓ.ም. የወንጀል ምርመራ ዳይሬክተር፣ የምርመራ ቡድን መሪና መርማሪ ሆነው ሲሠሩ፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባትና የኦነግ አባል ናቸው ተብለው በተጠረጠሩና በታሰሩ በርካታ ግለሰቦች ላይ ተገቢ ያልሆነ የምርመራ ዘዴ ተጠቅመዋል በተባሉ በአሥር የቀድሞ ማዕከላዊ መርማሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

አቶ ኢሳያስ ዳኘው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በሰባት አባላት በፀደቀ ውሳኔ ሊጠየቁ እንደማይገባ ተናገሩ

የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው፣ ኢዲኤም ለተባለ የአሜሪካ አማካሪ ድርጅት ከተፈጸመ ክፍያ ጋር በተያያዘ በሙስና መጠርጠራቸውን ተቃወሙ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጨምሮ በሰባት አባላት በፀደቀ ውሳኔና በተፈጸመ ክፍያ እሳቸው ሊጠየቁ እንደማይገባም ገልጸዋል፡፡

በእስረኞች ላይ ሽንት በመሽናትና ጥፍር በመንቀል የተጠረጠረችው መርማሪ 11 ክሶች ተመሠረቱባት

በሽብር ወንጀል ተፈርጀው ታስረው በነበሩ የኦነግና አርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት ላይ ሽንት በመሽናት፣ ጥፍር በመንቀልና በሌሎችም ዘግናኝ የተባሉ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥራ የታሰረችው፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ የቀድሞ አባል ዋና ሳጅን እቴነሽ አረፉዓይኔ 11 ክሶች ተመሠረቱባት፡፡

በ100 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ የተፈቀደላቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘው ለተጨማሪ ክርክር ተቀጠሩ

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግና ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው ከ23 ቀናት በፊት በ100 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የተፈቀደላቸው ቢሆንም፣ ከእስር አለመፈታታቸውንና ለተጨማሪ ክርክር ለረቡዕ ጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ተቀጠሩ፡፡

አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ የተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በአዲስ አበባ እንዲታይላቸው ጠየቁ

ከጥረት ኮርፖሬት ኩባንያዎች ገንዘብ ያላግባብ በማባከንና ማጥፋት የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ረቡዕ ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ ከሚገኘው ቤታቸው ተይዘው ወደ አማራ ክልል የተወሰዱትና ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ፣ ካለባቸው የጤና ችግርና የቤተሰብ ሁኔታ አንፃር ጉዳያቸው በፌዴራል ፍርድ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ እንዲታይ ጠየቁ፡፡

ፌዴራል ፖሊስ የ28 ሪል ስቴቶች ዕገዳ ጊዜያዊ መሆኑን አስታወቀ

የፌዴራል ፖሊስ ከወር በፊት የ28 ሪል ስቴት ኩባንያዎች የሽያጭና ተያያዥነት ያላቸው ሥራዎች እንዳይከናወኑ ያገደው በጊዜያዊነት መሆኑን አስታወቀ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ለመሬት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በጻፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው፣ 28ቱ የሪል ስቴት ኩባንያዎች የሽያጭና ተያያዥነት ያላቸው ሥራዎች ለ48 ሰዓታት እንዳይሠሩ የታገዱት የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የሙስና ወንጀል ፈጽመው በምርመራ ላይ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች፣ በሪል ስቴቶቹ ውስጥ የመኖሪያ ቤቶችና የአክሲዮን ድርሻ እንዳላቸው እስኪጣራ ድረስ ነበር፡፡

በሪል ስቴት ኩባንያዎች ላይ የተጣለው ዕግድ እንዲነሳ መመርያ ተሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)፣ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ለሪል ስቴት ኩባንያዎች መስጠት አቁሞ የነበረውን አገልግሎት በድጋሚ መስጠት እንዲጀምር መመርያ ሰጡ፡፡ ፍርድ ቤት እንጂ የፌዴራል ፖሊስ የማገድ ሥልጣን ስለሌለው፣ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ምክትል ከንቲባው ጨምረው መመርያ ሰጥተዋል፡፡

በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንትና ሌሎች ባለሥልጣናት ላይ ምርመራ ተጠናቀቀ

በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማና በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የዞንና የወረዳ ከተሞች በተፈጸመ ወንጀል ተጠርጥረው በምርመራ ላይ በነበሩት፣ የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ በአራት ባለሥልጣናት ላይ ምርመራ መጠናቀቁን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን አስታወቀ፡፡