Skip to main content
x

ጃፓን ለአዲስ አበባ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ሰጠ

የጃፓን መንግሥት በአዲስ አበባ ለሚተገበረው የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ፕሮጀክት ሁለት ሚሊዮን ዶላር ሰጠ፡፡ ‹‹ፋኩዎካ ሜተድ›› ተብሎ የሚጠራው ፕሮጀክት በከተሞች አካባቢ የሚያጋጥምን የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ችግር ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ፕሮጀክት ነው፡፡

የግል ትምህርት ቤቶች የጥራት መቆጣጠሪያ ሥልቶች ላይ ቅሬታቸውን አሰሙ

የአዲስ አበባ አጠቃላይ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ሬጉላቶሪ ኤጀንሲ በቅርቡ ጠርቶት በነበረው ስብሰባ የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶችን በተለይም የግል አገልግሎት ሰጪዎችን ለማነጋገርና በአገሪቱ የትምህርት ጥራት ላይ በተቀመጠው ደረጃ መሠረት ያዘጋጀውን የመቆጣጠሪያ ሰነድ ወይም ‹‹ቼክ ሊስት›› ይፋ ባደረገበት ወቅት ቅሬታ ቀረበበት፡፡

የመንግሥት ቁጥጥር በመዳከሙ በልኬት መሣሪያዎች የሚፈጸም ብዝብዛ ተባብሷል

በግብይት ሥርዓት ውስጥ ሚና ካላቸው አሠራሮች መካከል የልኬት መሣሪያ ወይም ሚዛን ይጠቀሳል፡፡ የልኬት መሣሪያዎች በሻጭና በገዥ መካከል የሚደረገውን  ግብይት የመዳኘት ድርሻ አላቸው፡፡ እነዚህ የልኬት መሣሪያዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ  የሚያገለግሉ የጋራ ቋንቋ ለመናገር የሚያስችሉ ናቸው፡፡ ዳኝነታቸው አወንታዊ የሚሆነው ግን መሣሪያዎቹ በአግባቡ ጥቅም ላይ ሲውሉ ነው፡፡

በአደጋ የተከበበው የአዲስ አበባ ‹‹ሳንባ››

የባህል አልባሳት፣ ጌጣጌጥና መገልገያዎች የሚሸጡበትን ሽሮ ሜዳ ስናልፍ የመኖሪያ ቤቶች ቁጥር እየቀነሰ፣ የዕፀዋት ብዛት እየጨመረ ሄደ፡፡ ታሪካዊውን የእንጦጦ ተራራ ጠመዝመዛ መንገድ ተከትለን ወደ ላይ አቀናን፡፡ ከተራራው ወደ ታች ሲቃኝ፣ በአገር በቀል ዕፀዋት የተሸፈነው እንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ አብዛኞቹ አረጋውያን የምግብ እጥረት ይገጥማቸዋል

በአዲስ አበባ ከተማ 74 ከመቶ የሚሆኑት አረጋውያን ለከፍተኛ፣ እንዲሁም 97 ከመቶ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ መዳረሻ የምግብ እጥረት እንደሚገጥማቸው ተነገረ፡፡ ‹‹የመገናኛ ብዙኃን ትኩረት ለአረጋውያን›› በሚል ርዕስ ታኅሣሥ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ጡረተኛና አረጋውያን ብሔራዊ ማኅበር ባካሄደው ዓውደ ጥናት ላይ  እንደተመለከተው፣ ለምግብ እጥረቱ የቤተሰብና የማኅበረሰብ ድጋፍ አናሳ መሆን እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡

ለ100 ሺዎች የሥራ ዕድል የመፍጠር ጅማሮ በአዲስ አበባ

በአዲስ አበባ ከመሬት አቅርቦት፣ ከግንባታ ፈቃድ፣ ከገንዘብ እጥረትና ከቴክኖሎጂ ኋላቀርነት ጋር የተያያዙ ችግሮች ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እንዳይፈጠር ምክንያት ሆነዋል፡፡ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎችም ቢሆኑ የከተማዋን ነዋሪ ጨምሮ በየዕለቱ ከየክልሉ እየፈለሱ ከተማዋን መኖሪያቸው ያደረጉ ወጣቶችና ሴቶችን ማስተናገድ አልቻሉም፡፡ በመሆኑም እንደ አንድ ማስተንፈሻ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች መደበኛ ባልሆኑ ንግዶች ተጨናንቀው ይታያሉ፡፡

አዲስ አበባን ማፅዳት ወይስ ፅዱ አዲስ አበባን መፍጠር?

ዕለተ ቅዳሜ ጠዋት የዕረፍት ቀኔ እንደመሆኑ፣ የልማዴን ቡና ለማድረስ ከመኖሪያ ቤቴ 200 ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ካፌ ታኅሣሥ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ተገኝቻለሁ፡፡ ከለመድኩት የጠዋት ቡና ጎን ለጎን የአዲስ አበባን ሳምንታዊ ጋዜጣና መጽሔቶች ይዘት ጎብኘት አድርጌ ወደ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ስመለስ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አዲስ ፎቶ መነጋገሪያ ሆኖ አገኘሁት፡፡

ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ሦስት ሆቴሎችን እየገነባ ነው

በአምስት ዓመት ሆቴሎችን ብዛት 20 ለማድረስ አቅዷል ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በአርባ ምንጭ፣ አዲስ አበባና በአዳማ ሦስት ዘመናዊ ሆቴሎችን በመገንባት ላይ ነው፡፡ ከስምንት ዓመት በፊት ኃይሌና ዓለም ኢንተርናሽናል የኢንቨስትመንት ኩባንያው የሐዋሳ ኃይሌ ሪዞርትን በመገንባት ወደ ሆቴልና ቱሪዝም መስክ የተቀላቀለ ሲሆን፣ በዝዋይና በሻሸመኔ ሁለት ሪዞርት ሆቴሎችን ከፍቷል፡፡ በሱሉልታ ከተማ ያያ ቪሌጅን ገንብቶ አገልግሎት ላይ ማዋሉ ይታወሳል፡፡

ክልሎችን ከአጎራባች ክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች የሚያቀናጅ አገር አቀፍ የከተማ ፕላን ሊዘጋጅ ነው

የአዲስ አበባና የአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን በገጠመው ተቃውሞ ከተሰረዘ በኋላ፣ የፌዴራል መንግሥት በመላ አገሪቱ የተቀናጀ የከተማ ፕላን ለመፍጠር ያረቀቀው አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡