Skip to main content
x

‹‹ጊፋታ›› እና ትውፊቱ

ከሦስት ወራት ክረምት በኋላ የሚከሰተው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ከአደይ አበባ ጋር ተያይዞ መስከረምን መነሻ ያደርጋል፡፡ እንደ የብሔረሰቡ፣ ነገዱ፣ ባህልና ትውፊት የአዲስ ዓመት መባቻው ልዩ ልዩ መጠሪያ አለው፡፡ ዕንቁጣጣሽ፣ አጎሮጎባሽ፣ ዕንግጫ (በዋዜማ) ቅዱስ ዮሐንስ፣ ርዕሰ ዐውደ ዓመት፣ ወዘተ እየተባለ ይጠራል፡፡

የክብረ መስቀል ወጎች ከአዲስ አበባ እስከ ሮም

ከአንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሰባት ዓመታት በፊት እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል የተገኘበት በዓል ከዛሬ መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ፣ በኤርትራና በኮፕቲክ (ግብፅ) ክርስቲኖች እየተከበረ ነው፡፡

የፀሐይና የጨረቃ የዓመት መባቻ የገጠመበት መስከረም 1

ዘመን ከሚሞሸርባት ዓመት ወደሚቀመርባት ወደኛዋ እንቁጣጣሽ ወደ አደይዋ ንስናሽ ተብሎ በመደበኛው ፀሐያዊው የኢትዮጵያ አቆጣጠር መሠረት መስከረም 1 ቀን 2011 ዓ.ም. (የቁጥር ድርደራውም በተመሳሳይ 1111 ሆኗል) አዲሱ ዓመት ገብቶ ሁለተኛው ቀን ላይ እንገኛለን፡፡

ኅብራዊው ክብረ በዓል

በሮም ፍራስካቲ ሠፈር የሚገኘው ትልቁ ባሰሊካ (ካቴድራል) የማያቋርጥ የደወል ድምፅ ይሰማል፡፡ እየቆየም ማስተጋባቱን ቀጥሏል፡፡ በአዘቦቱ ዘወትር ከሚሰማው የተለየውም በሀገረ ጣሊያን በምሥራቅ ኦርቶዶክስና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያናት ረቡዕ  ነሐሴ 9 ቀን 2010 ዓ.ም.

ለአምስቱ ነገሥታት ክብር የሰጠው የአሜሪካው መድረክ

በዳያስፖራ የሚኖሩ በየአገሩ የተበታተኑ ኢትዮጵያውያን ያቋቋሙት ማኅበረ ግዩራን ዘረ ኢትዮጵያ (ኢት ዘር) በእንግሊኛው ምሕፃር ሲድ/SEED (the Society of Ethiopians Established in the Diaspora) ይባላል፡፡ በአሜሪካ ከተመሠረተ ከሁለት አሠርታት በላይ ያስቆጠረው ሲድ በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያለፉትን ነገሥታት መሪዎች በማሰብና በማክበር ያለፈውን አገራዊ ታሪክ ሕያውነት ለማስቀጠል የሚሠራ ተቋም መሆኑ ይገለጻል፡፡

የትንሣኤው ብርሃን

በሔኖክ ያሬድ ‹‹ሽው ሽው ላሌ እሰይ ለዓመት በዓሌ… ታተይ ከቋቱ ላይ ያለው እንቁላል ድመት በላው አንቺ የት ሄደሽ? እኔማ ለገብርዬ ያን እሰጥ ብዬ አግባኝ ሳልለው አግብቶኝ ነጋዴ

በመስቀል በዓል የዩኔስኮ ምዝገባ የተፈጠረው ‹‹ስህተት›› በጥምቀቱም ላለመድገም

መሰንበቻውን የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ከሳቡ በዓላት አንዱ ዓመታዊው የጥምቀት በዓል ነው፡፡ በኢትዮጵያ በአደባባይ ከሚከበሩት በአውራነትም ይጠቀሳል፡፡ ሃይማኖት ከባህል ጋር የነበረውና ያለው የሚኖረው ቁርኝት አሳይነቱም ይጎላል፡፡ ድንበርን አልፎ ባሕርን ተሻግሮ ባዕዶችን ጭምር የማረከ መሆኑም ሌላው ገጽታው ነው፡፡

በዓል እና ገፀ በረከት

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለች፣ ጓደኞቿ ለልደት በዓል ስጦታ መለዋወጥ እንደሚፈልጉ ነገሯት፡፡ የጓደኛሞቹ ስም በወረቀት ይጻፍና ተጠቅልሎ ዕጣ ይወጣል፡፡ ከመካከላቸው ማን የማን ስም የተጻፈበት ወረቅት እንደደረሰው ዕጣው በወጣበት ዕለት አይነጋገሩም፡፡ በሚስጥር ይያዛል፡፡ ወ/ሮ ቤተል ዓባይ እንደምትለው፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አንድ ወይም ሁለት ቀን ሲቀረው ስጦታ ይለዋወጣሉ፡፡

የዋጋ ቅናሽ የሚናፍቀው ሸማች

በዓላት በተቃረቡ ቁጥር ሰውን ሁሉ ራስ ምታት ከሚያሲዙ ጉዳዮች አንዱ የዋጋና የገበያ ጉዳይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከበዓላት አከባበር ልማድ አኳያ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ እንደ በግ፣ ዶሮ፣ ቅቤ፣ እንቁላል ወዘተ. ምርቶች ዋጋቸው ምን ያህል ጨምሮ ይሆን? የሚለው ያሳስባል፡፡ ሁሉም እንደየአቅሙ በዓሉን ለማክበር ተለቅቶና ተበድሮ የቋጠራትን ጥሪት በመያዝ ወደ ገበያ ያቀናል፡፡