Skip to main content
x

በአካል ጉዳተኞች ስም ሙስና እየተፈጸመ መሆኑ ተነገረ

በኢትዮጵያ በሚገኙ የአካል ጉዳተኞች ስም ከተለያዩ የዓለም አገሮች በርከት ያለ የገንዘብና የቁሳቁስ ዕርዳታ የሚገኝ ቢሆንም፣ እነሱን መነሻ አድርገው ለተቋቋሙ ድርጅቶች መጠቀሚያ የሚውል መሆኑንና ይህም ድርጊት ሙስና እንደሆነ አካል ጉዳተኞች ተናግረዋል፡፡

በመርካቶ በመገንባት ላይ ያለው የአውቶቡስ ተርሚናል በመጪው ዓመት ሥራ ይጀምራል

በመርካቶ በአንድ ሰዓት ውስጥ 6,000 ለሚጠጉ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት የሚችል የአውቶቢስ ተርሚናል ግንባታ ተጀመረ፡፡ ይህ ተርሚናል በከተማው አስተዳደር በ200 ሚሊዮን ብር በጀት ግንባታው የተጀመረ ሲሆን፣ ግንባታው በ2011 በጀት ዓመት ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ የሚገባ ይሆናል፡፡

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ከሰኞ ጀምሮ አድማ እንደሚያደርጉ አስታወቁ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ‹‹ላለፉት ስምንት ዓመታት ላነሳናቸው ፍትሐዊ የሆኑ ከሙያ ዕውቅና፣ ከደመወዝና ከጥቅማ ጥቅም ጋር ለተገናኙ ጥያቄዎች በቂና ወቅታዊ ምላሽ አላገኘንም፤›› በማለት፣ ከሰኞ ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠዋት ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስታወቁ፡፡

ትራንስፖርትን ለገጠር እግረኞች የማድረስ ተልዕኮ

ሐኒ ሰመረ ለንደን በሚገኘው ሆልት ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ስኩል የቢዝነስና ኢንተርፕሩነርሽፕ ፕሮግራም ሁለተኛ ዓመት ተማሪ እንደሆነች ትናገራለች፡፡ ትውልድና ዕድገቷ እዚሁ አዲስ አበባ ሲሆን፣ የአሥረኛ ክፍል ትምህርቷን እንዳጠናቀቀች ነበር ወደ ዱባይ ያቀናችው፡፡

የአዲስ አበባ ፈጣን የትራንዚት አውቶቡስ አገልግሎት ከሦስት ዓመት በኋላ ይጀመራል ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የብዙኃን ትራንስፖርት አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ ያስቻላል ያለውን የፈጣን ትራንዚት አውቶቡስ (ቢአርቲ-ቢ2 ኮሪደር) አገልግሎት፣ በሦስት ዓመታት ውስጥ ሥራ ለማስጀመር እየሠራ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

የፀጥታ አስከባሪዎች መጎዳታቸውንና የመሣሪያ መንጠቅ ድርጊቶች መታየታቸውን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ጊዜ ጀምሮ 17 የፀጥታ አስከባሪዎች መቁሰላቸውንና የተለያዩ ንብረቶች መውደማቸው ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሴክሬታርያት ኃላፊና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በጽሕፈት ቤታቸው ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. አዋጁ ከታወጀ በኋላ የተከናወኑ ተግባራትን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

አቶ ሲራጅ አክለውም በተለያዩ አካባቢዎች የመሣሪያ ንጥቂያና የቀበሌ ጽሕፈት ቤቶችን ማቃጠል መፈጸሙን አስታውቀዋል፡፡ አንድ ፋብሪካ መቃጠሉንና አሥር የሕዝብ አውቶቡሶች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

የጋምቤላ ከተማ የባጃጅ ሾፌሮች አገልግሎት አቆሙ

በጋምቤላ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባጃጆች ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠዋት ጀምሮ አገልግሎት ማቆማቸውን የሪፖርተር ምንጮች ከስፍራው አስታውቀዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የአካባቢው ነዋሪዎች በትራንስፖርት እጦት እንደተቸገሩ ተናግረዋል፡፡

የባጃጅ ሾፌሮቹ ሥራ ያቆሙት አላግባብ ከፍተኛ ግብር እንድንከፍል ተጥሎብናል በማለት ሲሆን፣ የከተማው አስተዳደር ከሾፌሮቹ ጋር ውይይት ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል፡፡

ለወል ትራንስፖርት የሚውሉ 1,000 ታክሲዎች ሊገቡ ነው

በኪሎ ሜትር ሁለት ብር ከሃምሳ ሳንቲም ያስከፍላሉ ፒክ ፒክ ታክሲና ዮኪዳ ኮንሰልት የተባሉ ኩባንያዎች ከበላይ አብ ሞተርስ ጋር በመተባበር ለሰባት ተሳፋሪዎች የወል ትራንስፖርት አገልግሎት በስምሪት የሚሰጡ   አንድ ሺሕ ታክሲዎችን ለአዲስ አበባ ከተማ ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን አስታወቁ፡፡

የአዳማ መናኸሪያ በዘጠኝ ሚሊዮን ብር የማስፋፊያ ግንባታ ሊደረግለት ነው

ግንባታው ከሁለት ወር በኋላ ይጀመራል ከተቋቋመ ከ30 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የአዳማ መናኸሪያ በዘጠኝ ሚሊዮን ብር የማስፋፊያ ግንባታ ሊደረግለት ነው፡፡ አዲስ መናኸሪያም ተዘጋጅቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው፡፡