Skip to main content
x

አቶ ዳንኤል በቀለ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነርነት መታጨታቸውን እንደተቀበሉ ተሰማ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑት አቶ ዳንኤል በቀለ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር እንዲሆኑ መንግሥት ያቀረበላቸውን ጥያቄ በመስማማት እንደተቀበሉ ታወቀ።

የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በተግባር ለመከላከል የሚረዳ ጥናት መዘጋጀቱ ተገለጸ

ግጭት ከደረሰና የዜጎች ሰብዓዊ መብት ከተጣሰ በኋላ ለመከላከል መሯሯጥ ከንቱ ልፋት መሆኑን በመገንዘብ፣ ችግሩ ከመከሰቱ በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ከጅምሩ መከላከል የሚያስችል ጥናት ተጠንቶ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

በፍትሕ ዕጦት ተማረናል ያሉ የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች አቤቱታ አቀረቡ

በሶማሌ ክልል በመልካም አስተዳደርና በፍትሕ ዕጦት ተማረናል ያሉ የአገር ሽማግሌዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የፖለቲካ መሪዎች፣ ሡልጣኖችና ምሁራን የፌዴራል መንግሥት አቤቱታቸውን ተቀብሎ ምላሽ እንዲሰጣቸው እየጠበቁ እንደሆነ ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡

በኮማንድ ፖስቱ የተፈጸሙ ሰብዓዊ ጥሰቶች እንዲመረመሩ ፓርላማ አዘዘ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሲያስፈጽም በነበረው ኮማንድ ፖስት ተፈጸሙ የተባሉ የሰብዓዊ አያያዝ ጥሰቶች፣ በሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተጣርተው እንዲቀርቡ አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል አስታወቁ፡፡ አፈ ጉባዔዋ ይህንን የተናገሩት ፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማክሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ባነሳበት ወቅት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ወርዶፋ ያቀረቡትን ሪፖርት ካዳመጡ በኋላ ነው፡፡

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ግጭት ላይ የተጠናቀረውን ሪፖርት ለማቅረብ የፓርላማው ጥሪ እየተጠበቀ ነው

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በመስከረም ወር 2010 ዓ.ም. በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል ባጋጠመው የዜጎች መፈናቀል ወቅት የተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አስመልክቶ ያጠናከረውን ሪፖርት ይፋ ለማድረግ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥሪን እየጠበቀ እንደሆነ ዋና ኮሚሽነሩ አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር (ዶ/ር)  አስታወቁ፡፡

በቂሊንጦ ቃጠሎ ምክንያት ተከሰው የነበሩትን ጨምሮ የ62 ተከሳሾች ክስ ተቋረጠ

ነሐሴ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. በቂሊንጦ የእስረኞች ማቆያ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ምክንያት ተጠርጥረው ክስ ተመሥርቶባቸው ከነበሩት ከ100 በላይ ተጠርጣሪዎች መካከል፣ የልብ ሕክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የ62 ተከሳሾች ክስ ዓርብ ግንቦት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ተቋረጠ፡፡ ክሱን ያቋረጠው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሲሆን፣ ክሱ እንዲቋረጥ ትዕዛዝ የሰጡት በቅርቡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሆነው የተሾሙት አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ዴሞክራቲክ ተቋማት በነፃነትና በገለልተኝነት እንዲደራጁ ግፊት ይደረግ!

ኢትዮጵያ ውስጥ ላጋጠሙ ሥር የሰደዱ ችግሮች እንደ መነሻ ተደርጎ የሚወሰደው፣ የዴሞክራቲክ ተቋማት በነፃነትና በገለልተኝነት አለመደራጀትና ሥራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አለመደረጉ ነው፡፡ ዴሞክራቲክ ተቋማት የሚባሉት ምርጫ ቦርድ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ዕንባ ጠባቂ ተቋምና ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ተጠሪነታቸው ለፓርላማው እንደሆነ ተደንግጓል፡፡

በቂሊንጦ ቃጠሎ ተጠርጥረው የተከሰሱ 38 ተጠርጣሪዎች ለብይን ተቀጠሩ

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቂሊንጦ ተከሳሾች ማቆያ ቃጠሎ ጋር በተገናኘ ክስ የተመሠረተባቸው በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ፣ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ 38 ተከሳሾች ለብይን ተቀጠሩ፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን ክስ ሲመለከት የከረመው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ብይኑን የሰጠው ዓርብ ጥር 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ በዕለቱ መዝገቡን ቀጥሮ የነበረው ቀደም ባለው ቀጠሮ መጥሪያ ደርሷቸው ሳይቀርቡ የቀሩ የዓቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮችን ፖሊስ አስሮ እንዲያቀርብና ያልቀረቡበትን ምክንያት አስረድተው ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዲስተካከል እንግሊዝ ጥያቄ አቀረበች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ካለው ቀውስ ጋር ተያይዞ እየተፈጠሩ ያሉ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግሮች እንዲስተካከሉ እንግሊዝ ጠየቀች፡፡   ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ እየተከሰተ ካለው ቀውስ ጋር ተያይዞ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግር እንዳለ፣ ኢትዮጵያም ይህን ችግር እንድታስተካክል እንግሊዝ ምክረ ሐሳብ ማቅረቧ ታውቋል፡፡