Skip to main content
x

የሕዝብና የመንግሥት ሀብት በመመዝበር በሚጠረጠሩ ላይ ምርመራ መጠናቀቁ ተጠቆመ

በተደራጀና በቅንጅት የሕዝብና የመንግሥት ሀብት መዝብረዋል ተብለው በተጠረጠሩ ላይ፣ ሕጋዊ ዕርምጃ ለመውሰድ ምርመራ መጠናቀቁን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡ የፌዴራል ፖሊስና የምርመራ ቢሮና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት በተለዩ ዘርፎች ላይ ሰፊ ምርመራ ሲያካሄዱ እንደነበር፣ ምርመራውም በአሁኑ ወቅት በመገባደድ ላይ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑት ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የፖለቲካ መብቶችን አፍነዋል የተባሉ ሕጎችንና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ብሔራዊ ምክር ቤት ተቋቋመ

የፖለቲካ መብቶችን አፍነዋል ተብለው የተለዩ ሕጎችን ለማሻሻልና መሠረታዊ የፍትሕ ሥርዓት ለውጥ ለማካሔድ የሚሠራ ብሔራዊ ምክር ቤት ተቋቋመ። ምክር ቤቱ "የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ማሻሻያ ብሔራዊ ምክር ቤት" የሚል መጠሪያ የተሰጠው መሆኑን፣ በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ሰብሳቢነት እንደሚመራ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሪፖርተር ምንጮች ተናግረዋል።

የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት የመልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ላለፉት 20 ወራት በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ጌታሁን ናና፣ ከኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ አቶ ጌታሁን ናና ኃላፊነታቸውን የለቀቁት በፈቃዳቸው ነው፡፡ ሆኖም ባንኩን ለመምራት በተመደቡ በአጭር ጊዜ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ የተገደዱት፣ በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ከፍተኛ ጭቀጭቅ ያስነሳ ስብሰባ ከተካሄደ በኋላ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹም ሽር በማድረግ ለ43 አመራሮች ሹመት ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በ23 በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሥልጣን ሹም ሹር በማድረግ አዳዲስ ሹመቶች ሰጡ፡፡ ከተሰጡት ሹመቶች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳን በማንሳት በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን ደግፌ ቡላ (አምባሳደር) በሚኒስትር ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋቸዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ላለፉት አምስት ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ፍጹም አረጋ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተደርገው ተሾሙ፡፡ አቶ ፍጹም በአዲሱ ሥልጣናቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እንቅስቃሴዎች የመምራትና የማደራጀት ሥራዎችን የመወጣት ኃላፊነት እንደሚይዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የንግዱ ማኅበረሰብ አንገብጋቢ ያላቸውን ችግሮችና ቅሬታዎችን በማሰባሰብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት መላክ ጀመረ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሚያዝያ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ ዋነኛ ችግሮች እንደሆኑ ተለይተው ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ይቻል ዘንድ መመርያና  ማሳሰቢያ ሰጥተው ነበር፡፡ በዚህ መሠረትም እስካሁን ከተሰባሰቡ ጥያቄዎች ውስጥ በርከት ያሉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መላካቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ሄደው የሚሠሩባቸው የዓረብ አገሮች ተለዩ

ወደ ዓረብ አገሮች በብዛት እየሄዱ በቤት ሠራተኝነት በሚቀጠሩ ዜጎች ላይ በ2005 ዓ.ም. መጨረሻና 2006 ዓ.ም. መጀመርያ ላይ በደረሰ የሞት፣ ከባድ የአካል ጉዳትና እንግልት ሳቢያ መንግሥት ጥሎት የነበረውን የጉዞ ዕገዳ ከተነሳ በኋላ፣ በሕጋዊ መንገድ ሄደው መሥራት ለሚፈልጉ ዜጎች መንግሥት አገሮቹን ለይቶ አስታወቀ፡፡ መንግሥት የሁለትዮሽ ድርድርና ስምምነት የተፈራረመባቸው አገሮች ለጊዜው ኩዌት፣ ኳታርና ጆርዳን ብቻ በመሆናቸው ዜጎችም መሄድ የሚችሉት ወደነዚህ አገሮች ብቻ መሆኑ ታውቋል፡፡

መንግሥት በውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ላይ የጣለውን ዕገዳ አነሳ

መንግሥት ለዜጎች ደኅንነት በማሰብ በውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ላይ ለዓመታት ጥሎት የነበረውን ዕገዳ ከማክሰኞ ጥር 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲነሳ ወሰነ። የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ዕገዳው እንዲነሳ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡ የሚታወቅ ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከጥር 22 ቀን ጀምሮ ዕገዳው እንዲነሳ መወሰኑን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

የጥጥ ልማት ባለሥልጣን ሊቋቋም ነው

በተግዳሮቶች የተተበተበውን የጥጥ ልማትን ያሻሽላል የተባለለትና ከሁለት ዓመታት ጥናት በኋላ የተዘጋጀው የጥጥ ልማት ስትራቴጂ ይፋ ሊደረግ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የጥጥ ልማት ባለሥልጣን ይቋቋማል፡፡

በድንበር የሚካሄድ ኮንትሮባንድ የአገር ፈተና ሆኗል

ሕገወጥ የመድኃኒት ዝውውር የጤና ዋስትና ሥጋት መሆኑ ተገለጸ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች ጋር በምትዋሰንባቸው የድንበር ንግድ ቀጣናዎች የሚካሄደው ሕገወጥ ንግድ፣ አገሪቱን ለውጭ ምንዛሪ ኪሳራና ለማኅበራዊ ደኅንነት ችግር እየዳረገ መሆኑ ተመለከተ፡፡