Skip to main content
x

የኦሮሚያ ክልል አዲስ የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች አደረጃጀት ፀደቀ

የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ) አራት መሥሪያ ቤቶችን በማጠፍ የክልሉን የአስፈጻሚ አካላት ብዛት ከ42 ወደ 38 ዝቅ እንዲል፣ ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም. በተጠራው የምክር ቤቱ አራተኛ ዓመት አምስተኛ የሥራ ዘመን ሦስተኛ አስቸኳይ ጉባዔ ወሰነ፡፡

ባለመንታ ገጽታው ተሰናባቹ ዓመት

ኢትዮጵያውያን ዓምና ብለው ሊጠሩት የተቃረቡትን 2010 ዓ.ም. በመስከረም ወር የተቀበሉት በአገሪቱ በበርካታ አካባቢዎች ይከሰቱ በነበሩ አሰቃቂ የእርስ በእርስ ግድያዎች፣ በጎጠኝነት ምክንያት ብቻ ዜጎች ከትውልድ ቀዬዎቻቸው ያፈሩትን ጥሪት ተነጥቀው እንዲፈናቀሉና አሰቃቂ ሕይወትን በመጠለያ ካምፖች መግፋት በጀመሩበት፣ የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታና ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ባልታወቀበት ጨለማ ውስጥ ሆነው ነበር። በዚህ አስከፊ ሁኔታ የጀመረው 2010 ዓ.ም.

የወልዲያና የፍኖተ ሰላም ማረሚያ ቤቶች ተቃጠሉ

በአማራ ክልል በወልዲያና በፍኖተ ሰላም ማረሚያ ቤቶች በተነሳ ‹‹ግርግር›› ማረሚያ ቤቶቹ መቃጠላቸውንና ሌሎች ጉዳቶችም መድረሳቸውን፣ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስታወቁ፡፡

በማረሚያ ቤቶቹ ለተነሳው ግርግር ምክንያቱ በቅርቡ በፓርላማ የፀደቀው የምሕረት አዋጅ፣ እኛን ተጠቃሚ አያደርገንም በማለት የተቃወሙ እስረኞች ያስነሱት እንደሆነ አቶ ንጉሡ ገልጸዋል፡፡

በምሕረት አዋጁ አሳዛኙ የታሪክ ምዕራፍ ይዘጋ!

ዓርብ ሐምሌ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የምሕረት አዋጁን አፅድቋል፡፡ አዋጁ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ለተሳተፉ፣ የፖለቲካ መብታቸውን ለመጠቀም እንቅስቃሴ በማድረጋቸው መንግሥት ሲፈልጋቸው ከአገር ሸሽተው በተለያዩ አገሮች በስደት ለሚኖሩ ምሕረት ለመስጠት፣ በተጨማሪም የእርስ በርስ ጥላቻንና ጥርጣሬን በማስወገድ በብሔራዊ መግባባት አብሮ ለመሥራት ሲባል መውጣቱ ተገልጿል፡፡

በምሕረት አዋጁ የሚካተቱ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ማመልከት ይጠበቅባቸዋል

ዓርብ ሐምሌ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ለአስቸኳይ ስብሰባ የተጠራው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ለተያዙ፣ ለተፈረደባቸውና ሳይያዙ በውጭ አገር በስደት ለሚኖሩ ግለሰቦችና የሕግ ሰውነት ላላቸው አካላት ምሕረት እንዲደረግላቸው አወጀ፡፡

የኦሮሚያ የቀድሞ ሹም አዲስ አበባን በምክትል ከንቲባነት ይመራሉ

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉት አቶ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)፣ በምክትል ከንቲባነት አዲስ አበባን እንዲያስተዳድሩ ተሾሙ፡፡ በቅርቡ በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ያልሆነ ምክትል ከንቲባ መሆን ችለዋል፡፡

አዲስ አበባ በምክትል ከንቲባ ልትመራ ነው

በቅርቡ በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር መሠረት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ያልሆኑ ምክትል ከንቲባ ተሾሙ፡፡ በምክትል ከንቲባነት የተሾሙት አቶ ታከለ ኩማ (ኢንጂነር) ሲሆኑ፣ እሳቸው የከተማውን ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማን በተመተካት ኃላፊነቱን ማክሰኞ ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ተረክበዋል፡፡

አቶ ታከለ የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የነበሩ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የሱሉልታ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅና የሆለታ ከተማ ከንቲባም ነበሩ፡፡ የሰበታ ከተማ ኢንዱስትሪና ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የኦሮሚያ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሠርተዋል፡፡

የዘንድሮው ፓርላማ

አምስተኛው የምርጫ ዘመን ሦስተኛ ዓመት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዓመቱን ሥራ የጀመረው በመደናገር ውስጥ ሆኖ ነበር፡፡ የመደናገሩ ምክንያትም የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ የአገሪቱ ከፍተኛ የሆነውን ሥልጣን አልፈልግም በማለት መልቀቂያ በማቅረባቸው ነው፡፡