Skip to main content
x

መጪው ምርጫና የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሸክም

በ1993 ዓ.ም. የተፈጠረው የሕወሓት የመሰንጠቅ አደጋና አሸንፎ የመውጣት ፖለቲካዊ ትግል በወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የፖለቲካ ሕይወት ላይ ትልቅ አሻራ ነበረው። የሚቀርቧቸው እንደሚናገሩት ደግሞ ከአሻራነት በላይ የሕይወት መስመራቸው የተቀየረበት እንደሆነ ይናገራሉ።

በቀጣዩ ምርጫ ላይ ለመነጋገር በአስተማማኝ ቁመና ላይ መገኘት ያስፈልጋል!

ለሚቀጥለው ምርጫ ከወዲሁ ለመነጋገር እንደ መንደርደሪያ የሚሆን ውይይት ሊደረግ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አገር ውስጥ ካሉና በቅርቡ ከውጭ ከገቡ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ለመወያየት፣ ለማክሰኞ ኅዳር 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንደ አዲስ ለሚደራጀው የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም አመራርነት መታጨታቸው ተሰማ

መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ በስደት ይኖሩ ከነበረበት አሜሪካ የተመለሱት የቀድሞ ፖለቲከኛና የፖለቲካ ፓርቲ አመራር የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ አዲስ ለሚደራጀው ብሔራዊ ምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ኃላፊ እንዲሆኑ ታጩ።

ከውጭ ከገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ ጥያቄ እንዳልቀረበለት ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሥልጣን ከያዙ ወዲህ በተለያዩ መንገዶች የትግል እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ አገር ቤት ገብተው እንቅስቃሴያቸውን ማድረግ እንደሚችሉ ጥሪ ካቀረቡ በኋላ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ቤት ቢመለሱም፣ አንዳቸውም ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀርበው በይፋ የምዝገባ ጥያቄ አለማቅረባቸውን የቦርዱ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ተስፋ ዓለም ዓባይ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ኢሃን ኢትዮጵያን ከአገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት ለመቀየር የሽግግር ጊዜ ያስፈልጋል አለ

የተለየ ሐሳብ ይዞ መቅረቡን የሚናገረው የኢትዮጵያውያን አገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) የፖለቲካ ፓርቲ፣ ኢትዮጵያ ላለፉት 50 ዓመታት ከቆየችበት የአገዛዝ ሥርዓት ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት ለማሸጋገር፣ የሽግግር ጊዜና ተቋማት ያስፈልጓታል አለ፡፡

ኢዴፓ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

ላለፈው አንድ ዓመት ያህል በአመራሮች መካከል በተፈጠረ ልዩነት ችግር ውስጥ ገብቶ የነበረው የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ ለአገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እስከ ዛሬ ሲያደርገው የነበረውን ገንቢ ሚና በመቀጠል፣ ከዚህ ቀደሙ አደራጃጀት በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ በመውጣት የሚያደርገውን ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

የኢዴፓ ፕሬዚዳንት የፓርቲውን ማኅተምና ቼክ እንዲረከቡ በፍርድ ቤት ተወሰነላቸው

የቂርቆስ ምድብ አንደኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ግንቦት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የኢትጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ዋና ጸሐፊ አቶ ሳህሉ ባዩ በእጃቸው የሚገኘውን ማኅተምና ቼክ ለፕሬዚዳንቱ ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) እንዲያስረክቡ ወሰነ፡፡ በኢዴፓ አመራሮች መካከል ከገዥው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ጋር እየተካሄደ በነበረው ድርድር ምክንያት፣ በፓርቲው አመራር ማንነት ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡