Skip to main content
x

ንግድ ባንክ አስተዳደራዊ የመዋቅር ለውጥ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስካሁን ሲሠራበት የነበረው አስተዳደራዊ መዋቅር ላይ ለውጥ አደረገ፡፡ በዚህም መሠረት የባንኩ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት መዋቅሮች ላይ ማሻሻያ አድርጓል፡፡ በማሻሻያውም የባንኩን ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉን ዘለቀ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሎ የሰየመ ሲሆን፣ በሥራቸውም ስምንት ሥራ አስፈጻሚዎችን አስቀምጧል፡፡

ንብ ባንክ አሴት ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጓል

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ቋሚ ሀብት ለማፍራት ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በጀመረው እንቅስቃሴ ከ2.8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ አምስት የሕንፃ ግንባታዎችን እያካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ባንኩ ከአዲስ አበባ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዱከም ከተማ ያስገነባውን ለሁለገብ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ ግንቦት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ባስመረቀበት ወቅት እንደተገለጸው፣ ባንኩ ቋሚ ሀብት ለማፍራት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በማሳደግ ላይ ነው፡፡

ተሰናባቹ የእናት ባንክ ቦርድና አዲሱ አመራር ርክክብ ፈጸሙ

እናት ባንክን ለማቋቋም መንቀሳቀስ የጀመሩት መሥራቾች ውጥናቸው የተጀመረው ከአሥር ዓመታት በፊት ነበር፡፡ በአሥር እንስቶች ዋና አደራጅነትም ባንኩን የማቋቋም ሥራ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ለባንኩ ምሥረታ የሚያስፈልገው 75 ሚሊዮን ብር በአክሲዮን ሽያጭ አማካይነት ከተሟላ በኋላ፣ ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝቶ ባንኩ ሥራ ከጀመረ ስድስተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡

ብሔራዊ ባንክ አዲስ የውጭ ምንዛሪ አሰጣጥ ሥርዓትን በባንኮች ላይ ሊተገብር ነው

በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ መሠረታዊ ችግር ስለመሆኑ በይፋ የተነገረለትና ችግሩም ሥር ሰድዶ የሚታየው የውጭ ምንዛሪ እጥረትና አጠቃቀም ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ኃላፊነታቸውን በተረከቡ ማግሥት ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በመከሩበት ወቅት፣ የቀረበላቸው የውጭ ምንዛሪ እጥረትና ችግሮቹ ላይ ያጠነጠነ ጥያቄ ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽም የውጭ ምንዛሪ እጥረት የሚገኝበትን ሁኔታና የችግሩን ስፋትም አመላክቷል፡፡

ብሔራዊ ባንክ የወጋገን ባንክን ሕንፃ ለቢሮ አገልግሎት መከራየቱ ታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወጋገን ባንክ አዲሱ ሕንፃ ላይ ቢሮዎች መከራየቱ ተሰማ፡፡ ብሔራዊ ባንክ ስቴዲየም አካባቢ ከተገነባው የወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ የተከራየው ሦስት ወለሎች እንደሆነ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ብሔራዊ ባንክ በወጋገን ባንክ ሕንፃ ላይ የተከራያቸው ወለሎች ለቢሮ አገልግሎት እንዲውሉ በማሰብ ሲሆን፣ የተወሰኑ የብሔራዊ ባንክ የሥራ ክፍሎችን ወደዚህ ሕንፃ እንደሚያዘዋውር ታውቋል፡፡

ዳሸን ባንክ ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ላስገኙ ደንበኞቹ ዕውቅና ሰጠ

ዳሸን ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገቢ አስገኝተዋል ላላቸው 168 የንግድ ተቋማት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች ዕውቅና ሰጠ፡፡ ባንኩ በ2009 ዓ.ም. ከ530 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ እንዳገኘም ይፋ አድርጓል፡፡

ባንኮች ለብሔራዊ ባንክ ቦንድ ግዥ ከ65 ቢሊዮን ብር በላይ ማዋላቸው ታወቀ

የግል ባንኮች ከሚያበድሩት እያንዳንዱ ገንዘብ ውስጥ የ27 በመቶ ተቀናሽ አስልተው ለብሔራዊ ባንክ ቦንድ ግዥ እንዲያውሉ በሚያስገድደው መመርያ መሠረት እስካሁን ከ65 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማድረጋቸው ተጠቆመ፡፡

ሕብረት ባንክ የ12 ዓመታት የስትራቴጂክ ዕቅድ እንዲያዘጋጅለት ድሎይት የተባለውን የውጭ አማካሪ ቀጠረ

የአገሪቱ የግል ባንኮች ለተወዳዳሪነት የሚያበቋቸውን የተለያዩ ስትራቴጂዎች በመቅረጽ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ የውጭ ተወዳዳሪ የሌለባቸው የኢትዮጵያ ባንኮች የእርስ በርስ መወዳደሪያ ሥልቶቻቸው ጠንካራ እንዳልሆኑ ይነገራል፡፡

ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የ45 ነጋዴዎችን የባንክ ሒሳብ ማገዱ ተቃውሞ አስነሳ

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በንግድና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ 45 ኩባንያዎች በ18 ባንኮች የሚያንቀሳቀሱትን ሒሳብ በሙሉ ማገዱ ተቃውሞ አስነሳ፡፡ ባለሥልጣኑ የባንክ ሒሳባቸውን ያገደው ሕግን ባልተከተለ መንገድ መሆኑን የገለጹ ኩባንያዎች ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የ40/60 ሱቅ ለመግዛት ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ አቀረበ

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የአዲስ አበባ ከተማ የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ የንግድ ቤቶችን ለመሸጥ ባወጣው ጨረታ፣ 156 ካሬ ሜትር የ40/60 ሱቅ ለመግዛት 26.6 ሚሊዮን ብር የመጫረቻ ዋጋ አቀረበ፡፡ ባንኩ የሰጠው ዋጋ ለሁሉም ሱቆች ከተሰጡት ዋጋዎች በከፍተኛነት ተመዝግቧል፡፡