Skip to main content
x

ኢትዮጵያ በዘረመል የተለወጡ ህያው የጥጥ ዝርያዎች እንዲመረቱ ፈቀደች

ከሁለት ዓመታት ጥብቅ የመስክ ላይ ሙከራ በኋላ መንግሥት በዘረመል የተለወጡ ህያው የጥጥ ዝርያዎች እንዲመረቱ የሚያስችል ፈቃድ፣ ለኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት መሰጠቱ ታወቀ፡፡ ኢንስቲትዩቱ ፈቃድ ለሚሰጠው ለአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ሚኒስቴር ያቀረበውን የምርምር ውጤት መነሻ በማድረግ ለቀረበለት የጽሑፍ ማመልከቻ፣ ሚኒስቴሩ ፈቃድ መስጠቱን በሚኒስቴሩ የደኅንነተ ሕይወት ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አሰፋ ጉዲና ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የጥጥ ልማት ባለሥልጣን ሊቋቋም ነው

በተግዳሮቶች የተተበተበውን የጥጥ ልማትን ያሻሽላል የተባለለትና ከሁለት ዓመታት ጥናት በኋላ የተዘጋጀው የጥጥ ልማት ስትራቴጂ ይፋ ሊደረግ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የጥጥ ልማት ባለሥልጣን ይቋቋማል፡፡