Skip to main content
x

የፍትሕ ሥርዓቱን ቁመና ገልጦ ያሳየው ፍትሕን ፍለጋ ጉዞ

ሕገ መንግሥቱ ያጎናፀፋቸውን ፍትሕ የማግኘት መብት ያጡ ወይም የተነፈጉ የተወሰኑ ግለሰቦች ላለፉት አሥር ዓመታትና አሁንም ባለመታከት እያደረጉት የሚገኘው የፍትሕ ፍለጋ ጉዞ የት ደረሰ? በጉዟቸው መሀል ያገኙዋቸው ምላሾች ተቃርኖ ስለሕግ ተርጓሚው የፍትሕ አካል ቁመና ምን ይናገራል? የሚለው የዚህ ዘገባ ትኩረት ነው። አንቀጽ 37 እንደ መነሻ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ ውሳኔዎች በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተቋማዊ ልዕልና ላይ ያጫሩት ጥያቄ

የፌዴራል ሥርዓትን የሚከተሉ ሁሉም በመላው ዓለም የሚገኙ መንግሥታት የተለያየ ቅርፅና አደረጃጀት ይኑራቸው እንጂ፣ በሁለት መሠረታዊ ባህርያት ያመሳስላቸዋል። እነዚህም በሚመሩበት ሕገ መንግሥት ተደንግጎ የተለየ የሥልጣን ክፍፍል ማድረጋቸው፣ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ሆነው በአንድ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦችን የሚያገለግሉ ከአንድ በላይ የሆኑ ነገር ግን የሚተባበሩና የሚደጋገፉ መንግሥታት መሆናቸው ነው።

አዲሱ የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀትና አዳዲስ ባህርያቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ሁለተኛውን ሹምሽር አድርገውና የአስፈጻሚ አካላትን ብዛትም ቀንሰው ያቀረቡት አዋጅ ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በፓርላማው በሙሉ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን፣ በአስፈጻሚው አካላት ቁጥርና አደረጃጀትንና በካቢኔ አወቃቀሩ ላይ በርካታ አዳዲስ ክስተቶች ተስተውለዋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፓርላማ ሳያፀድቀው አስፈጻሚ አካላትን ማደራጀት የሚያስችለው ሥልጣን ተሰጠው

ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. የተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክት ቤት የ4ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ባፀደቀው የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን ሲያፀድቅ፣ ካሁን በፊት በአዋጅ ይደረግ የነበረው የአስፈጻሚ አካላትን የማደራጀት ሥልጣን በደንብ አማካይነት ማድረግ እንዲችል ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥልጣን ሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ወደ ፌዴራል መንግሥት ተዘዋውረው የነበሩ መሥሪያ ቤቶቹን መሰብሰብ ጀመረ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት አንበሳ አውቶብሳ ድርጅት በድጋሚ ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲመለስ በ2003 ዓ.ም. ቢወስንም ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቶ፣ የምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ካቢኔ ድርጅቱ ደንብና መመርያ ወጥቶለት በቀጥታ ተጠሪነቱ ለከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሆን ወሰነ፡፡

በምሕረት አዋጁ የሚካተቱ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ማመልከት ይጠበቅባቸዋል

ዓርብ ሐምሌ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ለአስቸኳይ ስብሰባ የተጠራው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ለተያዙ፣ ለተፈረደባቸውና ሳይያዙ በውጭ አገር በስደት ለሚኖሩ ግለሰቦችና የሕግ ሰውነት ላላቸው አካላት ምሕረት እንዲደረግላቸው አወጀ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወሰነ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ቅዳሜ ግንቦት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የአገሪቱን የጸጥታ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ረቂቁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተልኮ መጽደቅ ይኖርበታል ሲሉም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃለፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሁለተኛ ጊዜ መታወጁ ይታወሳል፡፡

በፓርቲ ተፅዕኖ ሥር የወደቀውን የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ግንኙነት ተቋማዊ ለማድረግ የተዘጋጀ የፖሊሲ ማዕቀፍ ለፓርላማ ተላከ

በአሁኑ ወቅት በአንድ ፓርቲ ተፅዕኖ ሥር እንደወደቀ በይፋ የታመነበትን የፌዴራልና የክልል የመንግሥታት ግንኙነት ከፓርቲና ከግለሰቦች ተፅዕኖ በማላቀቅ፣ ተቋማዊ መሠረትና ሕጋዊ ሥርዓት እንዲኖረው ለማድረግ የተረቀቀ የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲፀድቅ ለፓርላማ ተላከ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግሥታት ግንኙነት የፖሊሲ ማዕቀፍ›› የሚል መጠሪያ የተሰጠውን ይህንን የፖሊሲ ማዕቀፍ ያረቀቁት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የፌዴራል አርብቶ አደርና ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ናቸው፡፡

የሪል ስቴትና የአከራይ ተከራይ አዋጅ በድጋሚ እንዲስተካከል ታዘዘ

በሪል ስቴት ቤቶች ግብይት፣ በመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩና በኅብረተሰቡ ዘንድ ተጠባቂ የሆኑ ሦስት ረቂቅ አዋጆች በጥቅል ተዘጋጅተው ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከቀረቡ ዓመታት ቢቆጠሩም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሦስቱም ረቂቅ አዋጆች ተነጣጥለው እንዲዘጋጁ በድጋሚ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ፓርላማው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ እንዲወስን በአስቸኳይ ተጠራ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአስቸኳይ አዋጁ ላይ እንዲወስኑ ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠሩ፡፡ ከየካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ወር ዕረፍት የወጡት የፓርላማ አባላት ለአስቸኳይ ስብሰባ በመጠራታቸው ምክንያት፣ ከማክሰኞ የካቲት 20 ቀን 2010 ጠዋት ጀምሮ ሪፖርት ሲያደርጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡