Skip to main content
x

የአማራ ክልል የወጪና ገቢ ንግድ ማነቆዎች

የአማራ ክልል የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ የክልሉን የወጪና የገቢ ንግድ እንቅስቃሴን የተመለከተ የምክክር መድረክ ቅዳሜ፣ ግንቦት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. አዘጋጅቶ ነበር፡፡ በመድረኩም የክልሉን የገቢና የወጪ ንግድ ዕድሎች፣ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሐሳቦች የቃኘ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቧል፡፡  ጥናታዊ ጽሑፉ በክልሉ የሚታዩትን የወጪና የገቢ ንግድ ችግሮች ያመላከተ ቢሆንም፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አገራዊው ወጪና ገቢ ንግድ የሚታዩበትን ችግሮችም ያመለከተ ነበር፡፡

ሶማሌላንድ በበርበራ ወደብ የምታካሂደውን የማስፋፊያ ግንባታ በመስከረም ወር እንደምትጀምር ታወቀ

ራሷን እንደቻለች ሉዓላዊት አገር ዕውቅና ለማግኘት በመጣጣር ላይ የምትገኘው ሶማሌላንድ፣ ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስን በባለድርሻነት ያካተተውን የበርበራ ወደብ የማስፋፊያ ግንባታ በመጪው መስከረም ወር እንደምትጀምር አስታወቀች፡፡ የበርበራ ወደብ የኦፕሬሽን ሥራዎችን የሚመሩ ኃላፊዎች ሰሞኑን በወደቡ ጉብኝት ላደረጉ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ወቅት እንደታስወቁት፣ በሰኔ ወር የወደብ ግንባታውን ለሚያካሂዱ ኩባንያዎች ሥራው እንደሚሰጣቸውና በመስከረም ወርም  ግንባታ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል፡፡

ሶማሊያ ከመዳረሻ አገሮች አውራ በሆነችበት የወጪ ንግድ አፈጻጸም የ1.35 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተመዘገበ

በዚህ ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ ዘርፉ የ1.35 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ከአሥሩ ዋና ዋና መዳረሻ አገሮች ውስጥ ሶማሊያ በቻይና ተበልጣ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የወጪ ንግድ መዳረሻ አገር ተብላለች፡፡

እየቀነሰ የመጣው የገቢ ንግድ

በአገሪቱ የወጪና የገቢ ንግድ መካከል ያለው ሰፊ ልዩነት አሁንም እንደቀጠለ ቢሆንም፣ አገሪቱ ለገቢ ንግድ የምታውለው ወጪ ቅናሽ እያሳየ መሆኑ ተመለከተ፡፡ የአገሪቱን የወጪና ገቢ ንግድ ዓመታዊ ተከታታይ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በተለይ ባለፉት አሥር ዓመታት የገቢ ንግዱ በአማካይ ከ20 በመቶ እያደገ ቢሆንም፣ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ አገሪቱ ለገቢ ንግድ የምታውለው የውጭ ምንዛሪ በተወሰነ ደረጃ እየቀነሰ ነው፡፡ ሰሞኑን ይፋ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የ2009 ዓመታዊ ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰውም፣ በ2009 በጀት ዓመት ለወጪ ንግድ የወጣው ወጪ ከቀደመው በ5.5 በመቶ ቀንሷል፡፡ 

ብሔራዊ ባንክ ለወጪ ንግድ የሰጠው ትኩረት ተጋኗል እየተባለ ነው

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሰሞኑ ዕርምጃዎች ውስጥ የአገሪቱ ባንኮች ከወጪ ንግድ ባሻገር ላሉት ዘርፎች የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ ገደብ እንደሚያስቀምጥ ማስታወቁ አንዱ ነው፡፡ ይህ አሠራር ባንኮች በዓመት ከምትሰጡት ጠቅላላ ብድር ውስጥ እንደሚወሰነው መጠን ለኢኮኖሚው ዘርፍ እንዲያውሉ የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡

የብር የምንዛሪ ተመን በ15 በመቶ ቀነሰ

ለባንኮች የብድር ጣሪያ ሊቀመጥላቸው ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብር ከሌሎች የውጭ ገንዘቦች በ15 በመቶ ቀንሶ ግብይት እንደሚፈጸምበትና ባንኮች ለተቀማጭ ገንዘብ የሚከፍሉት የወለድ መጠን ወደ ሰባት በመቶ ከፍ ማለቱን አስታወቀ፡፡