Skip to main content
x

ቅዱስ ሲኖዶስ ግብፅ በዴር ሡልጣን ገዳም እየፈጠረች ላለው ችግር መንግሥት መፍትሔ እንዲያስገኝ ጠየቀ

ግብፅ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታ ላይ እየፈጠረች ያለውን አሳሳቢ ችግር መንግሥት አስፈላጊውን መፍትሔ እንዲያስገኝ ቅዱስ ሲኖዶስ ጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለ11 ቀናት ያካሄደውን ጉባዔ ማጠናቀቁን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ በይዞታችን ላይ አግባብነት የሌለው ሥራን የማደናቀፍና በታሪክም ሆነ በማንኛውም የሰነድ መረጃ የሌለው የባለቤትነት ጥያቄ በማንሳት እየተፈጠረ ያለውን አላስፈላጊ ሁከትና ብጥብጥ ማቆም አለባቸው ብሏል፡፡

በሆቴል ግንባታ ከሚጠቀሱ አሥር የአፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያ ሦስተኛዋ ሆናለች

ዋና መሥሪያ ቤቱን በናይጄሪያ ሌጎስ ያደረገውና፣ በየዓመቱ የየአገሮችን የሆቴል፣ የቱሪዝምና የመዝናኛ አገልግሎቶችን በተመለከተ ሪፖርት የሚያዘጋጀው፣ ደብሊው ሆስፒታሊቲ ግሩፕ፣ በዘንድሮው ሪፖርቱ ኢትዮጵያን በሆቴሎች ግንባታና ኢንቨስትመንት ከአሥር ዋና ዋና አፍሪካ አገሮች ውስጥ ሦስተኛዋ እንደሆነች ይፋ አደረገ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግብፅን በፍፁም አንጎዳም ሲሉ ማሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር በነበራቸው ውይይት፣ ኢትዮጵያ ግብፅን የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት ሲገልጹ በመሃላ የታጀበ ንግግር አሰሙ፡፡ የግብፅ የውኃ ድርሻ እንዲጨምር እናደርጋለን ብለዋል፡፡

የግብፅ የፍርኃት ፖለቲካና ታላቁ የህዳሴ ግድብ

ስቶኮልም ዓለም አቀፍ የውኃ ኢንስቲትዩት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ፣ ለምሥራቅ የዓባይ ወንዝ ተፋሰስ አገሮች ያዘጋጀውን ዓውደ ጥናት እንዲካፈሉ ከተጋበዙ የኢትዮጵያ የሚዲያ ተቋማት መካከል ሪፖርተር አንዱ ነበር፡፡ ለዚህ ዓውደ ጥናት ሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ማለዳ በካይሮ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰው ስድስት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ የጋዜጠኞች ቡድን፣ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ከአውሮፕላን ማረፊያው መውጣት አልቻለም ነበር፡፡

የህዳሴው ግድብ በግብፅ ላይ ጉልህ ጉዳት እንደማያደርስ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ገለጹ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በግብፅም ሆነ በሱዳን ላይ ጉልህ ጉዳት እንደማያደርስ፣ በግድቡ ላይ ጥናት ያደረጉ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ኬቨን ዊል (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ በግድቡ የውኃ ሙሌት ሞዴል ላይ ያደረጉትን ጥናታዊ ምርምር ባለፈው ሳምንት በግብፅ አሌክሳንድርያ ከተማ ለተገኙ የተፋሰሱ የምሥራቅ አፍሪካ ጋዜጠኞች ባረቀቡበት ወቅት ነው፣ ኢትዮጵያ የምትገነባው የህዳሴ ግድብ ጉልህ ጉዳት እንደማያደርስ ተመራማሪው የተናገሩት፡፡

መቋጫ አልባው የህዳሴ ግድብ ውይይት

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምትገነባውን የህዳሴ ግድብና የተፋሰሱ አገሮች በዓባይ ወንዝ ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት አስመልክቶ ድርድር ማድረግ የጀመሩት የህዳሴ ግድቡ መገንባት እንደ ጀመረ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን አቋቁመው ውይይት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገንቢ ያልሆኑ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ወቀሱ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ ከስምምነት ውጭ የሆኑና ገንቢ ያልሆኑ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው ሲሉ ወቀሱ፡፡ ቃል አቀባዩ ይኼንን ያሉት ዛሬ ግንቦት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

ካርቱም ሱዳን መጋቢት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. የተካሄደው ድርድር ውጤታማ ሳይሆን ከቀረ በኋላ፣ ሚኒስቴሩ ለሌላ ውይይት ካይሮ ላይ ሚያዝያ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ሚኒስትሮቹ እንዲሰበሰቡ አሳስበው ነበር፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጥናቶች እንዲቀጥሉ የሦስትዮሽ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሄደ

የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የሦስትዮሽ ብሔራዊ ኮሚቴ አባላት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን የሚመለከቱ ጥናቶች እንዴት እንደሚቀጥሉ በአዲስ አበባ ተገናኝተው ተወያዩ፡፡ በአዲስ አበባ በተካሄደው ስብሰባ የሦስቱም አገሮች የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተገኙ ሲሆን፣ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚደረጉት ሁለት ጥናቶች በሚቀጥሉበትና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ይፋ ባደረገው መረጃ አመልክቷል፡፡  

የኢትዮጵያና የኤርትራ የወደፊት ተስፋና የወቅቱ ፈተና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሰየሙ ባደረጉት ንግግር ከጠቀሷቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታትን ግንኙነት የተመለከተ ነበር፡፡