Skip to main content
x

ኑሮ ከተባለ…

በአጭር የተከረከሙት ፀጉራቸው ብዙም ሽበት አይታይበትም፡፡ ጎስቋሏ ፊታቸው ግን እርጅና የተጫጫናቸው አስመስሏቸዋል፡፡ ከወለሉ የመስኮት ያህል ከፍታ ያለውን በር እንደተደገፉ ውጭ ውጭውን ያያሉ፡፡ ዕይታው የደከመው ዓይናቸው ግን ወዳጆቻቸውን እንኳን አይለይም፡፡ በስማቸው እየጠሯቸው ለሰላምታ እጃቸውን ለዘረጉላቸው ሰዎች አፀፋውን ቢመልሱም ማን መሆናቸውን አላወቁም፡፡

በኢትዮጵያ ድህነት ቢቀንስም የኑሮ ልዩነት እየጨመረ መምጣቱን የመንግሥት ጥናት ይፋ አደረገ

ሐረሪ ድሬዳዋና አዲስ አበባ ከአገሪቱ ዝቅተኛ የድህነት መጠን የታየባቸው ሆነዋል ባለፈው ዓመት በተካሔደ የድህነት ትንተና ጥናት መሠረት በ2008 ዓ.ም. በአገሪቱ የነበረው አጠቃላይ የድህነት መጠን 23.5 በመቶ (ከ94 ሚሊዮን ሕዝብ ውስጥ በድህነት ውስጥ የሚገኘው) እንደነበር በማሳየት ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረው የ29.6 በመቶ ይልቅ የስድስት በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡