Skip to main content
x

ሙዚቃና ዳንኪራ ያጀበው የባንግላዴሽ ገጽታ

ባንግላዴሽ ሁሉን ያቀፈች አገር ናት ይሏታል፡፡ ከሃይማኖት አንፃር እስልምና፣ ቡድሂዝም፣ ሂንዱዝምና ክርስትና በአንድነት የሚኖሩበት በርካታ ነገዶችና ጎሳዎችንም በጉያዋ ያቀፈች ናት፡፡ ከተለያዩ ነገዶቿና ሃይማኖቶቿ ጋር ተያይዘው የሚፈልቁ ባህሎች ትውፊቶችና ልማዶችም ባለፀጋ ናት፡፡

የአፍሪካ ምርጥ አልበም ክብርን ከሦስት ሽልማቶች ጋር የተቀዳጀችው ቤቲ ጂ

በጋና መዲና አክራ በተከናወነው የመላ አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት (አፍሪማ) ኢትዮጵያዊቷ ድምፃዊት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) በሦስት ዘርፎች አሸንፋለች፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ኅዳር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ምሽት ለአምስተኛ ጊዜ በተደረገው የአፍሪካ ማድረክ ለክብር ከበቁት መካከል ቤቲ ጂ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ አልበም እንዲሁም የምሥራቅ አፍሪካ ምርጥ ሴት አርቲስት በመሰኘት ገዝፋ ታይታለች፡፡

የማሲንቆው አውራ ድምፃዊ ለገሠ አብዲ (1931-2011)

በኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃ ታሪክ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት የባህል ሙዚቃ መሣሪያ ተጨዋቾች መካከል አንዱ ነው፡፡ ከግማሽ ምዕት ዓመት በላይ የተቆራኛትን ማሲንቆን በኦሮምኛ ዜማ ሲያጫውታት ኅብረተሰቡንም ሲያጫውት ኖሯል፡፡ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ድምጻዊው ለገሠ የለገሰውን የማሲንቆ ጨዋታ ሲደመሙበት ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡

አዝማሪነትን ለመታደግ ያለመው ፍለጋ ፌስቲቫል

‹‹አዝማሪና ሙያው ማለት ልክ ባህላዊ ባንድ ማለት ነው፤ ድምፃዊውም እሱ ራሱ ነው፤ ደራሲውም እሱ ራሱ ነው፤ ተጫዋቹም እሱ ራሱ ነው፡፡ መሣሪያውንም የሚጫወተው እሱ ራሱ ስለሆነ እንደ አንድ ባንድ ማለት ነው፤›› ብለው አዝማሪነትን በአንድ ወቅት የገለጹት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓባይ የባህልና ልማት ጥናት ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ሙሉ ቀን አንዷለም (ዶ/ር) ናቸው፡፡

የወላይትኛ ድምፃዊ ኮይሻ ሴታ (1963-2010)

ድምፃዊው ኮይሻ ሴታ በ1980ዎቹ አጋማሽ የወላይትኛ ባህላዊ ሙዚቃ በማስተዋወቅ ረገድ ተጠቃሽ ነበር፡፡ በ1984 ዓ.ም. ባሳተመው የወላይትኛ አልበሙ ከሚገኙት ዘፈኖቹ “ኤ አዬ ኤሲስ አቦ…ቡሌ ጋሼ ወላ ሎሜ አያ›› ተደናቂነትን እንዳተረፈበት ይወሳል፡፡

የኢትዮጵያና የኢራን ጥበባዊ ትስስር

የምሽቱ መርሐ ግብር የተጀመረው በመሶብ ባንድ ባህላዊ ሙዚቃዎች ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የተገኙትን ታዳሚዎች በሙዚቃዎቻቸው ዘና አድርገዋል፡፡ ባንዱ በተለይም ግጥም በጃዝ በሚቀርብባቸው የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች በባህላዊ ሙዚቃ የግጥም ሥራዎችን በማጀብ ይታወቃል፡፡ በክራር፣ በመሰንቆ፣ በዋሽንትና በከበሮ ውህድ ግጥሞቻቸውን ያስደመጡ ጸሐፍትም በርካታ ናቸው፡፡

ሙዚቃ ለሰላም

‹‹ሚውዚክ ፎር ፒስ›› (ሙዚቃ ለሰላም) የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የተካሄደው የአፍሪካን አርቲስትስ ፒስ ኢንሽዬቲቭ (ኤኤፒአይ) ፎረምን ተከትሎ ነበር፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ያሉ አርቲስቶችና የመብት ተሟጋቾች ስብስብ የሆነው ኤኤፒአይ፣ የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤን አስታኮ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ የውይይቱ ቀዳሚ ትኩረት ሙስናን በመዋጋት ረገድ አፍሪካውያን አርቲስቶች ምን ሚና አላቸው? የሚለው ነበር፡፡ በውይይቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ ድምፃውያን፣ ገጣሚዎች፣ ዲዛይነሮች፣ ፊልም ሠሪዎችና ሌሎችም የጥበብ ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡ ጥር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የተጀመረው ውይይት የተገባደደው ጥር 19 በተካሄደው የሙዚቃ ኮንሰርት ነው፡፡

የሞርጋን ቤተሰብ በልደት ዋዜማ

‹‹ሙዚቃ በየምንሔድበት አገር እናቀርባለን፡፡ ወደ ኢትዮጵያ በዚህ የበዓል ወቅት መምጣት ግን ሙዚቃ ከማቅረብም በላይ ነው፡፡ ለገና በዓል በኢትዮጵያ መገኘታችን ታላቅ ደስታ ሰጥቶናል፤›› በማለት ነበር የሞርጋን ሔሪቴጅ ባንድ ወንድማማቾች የተናገሩት፡፡ በልደት በዓል ዋዜማ በኤቪ ክለብ ሙዚቃዎቻቸውን ለማስደመጥ ከናይሮቢ፣ ኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡

ታላቁ ሩጫን የተከተለው ኮንሰርት

‹‹አፍሪካስ ሀፒየስት ፊት፤ ዘ ግሬት ኢትዮጵያን ራን›› (Africa’s Happiest Feet: The Great Ethiopian Run) በሚል ከሁለት ዓመት በፊት ዘ ጋርዲያን ያስነበበው ጽሑፍ ስለ ታላቁ ሩጫ ያወሳል፡፡ ‹‹ታላቁ ሩጫ የአፍሪካ ትልቁ አስደሳች ሩጫ ነው፡፡ ደማቅና የሞቀ እንደመሆኑ መዲናዋ አዲስ አበባን ለመጎብኘት የተመቸ ነው፤›› በማለት ነበር የተገለጸው፡፡