Skip to main content
x

የሕፃናት አድን ተቋም መሪው ጆን ግራሀም ኅልፈት

በኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በላይ ያገለገሉት ጆን ግራሀም አረፉ፡፡ ዘጠኝ ዓመታት በዩኤስ ኤይድ፣ 11 ዓመታትን ደግሞ በሴቭ ዘ ቺልድረን ኢትዮጵያ አገልግለዋል፡፡ ጆን ግራሀም ከኢትዮጵያ ጋር አብረው መሥራት የጀመሩት ግን ከ1977ቱ ረሃብ ጀምሮ ነው፡፡ በወቅቱ የድንበር ዘለል ግዳጅ የማስፈጸም ሥራ ይሠሩ የነበረ ሲሆን፣ ከኦክስፋም ካናዳ ጋር በመተባበር በትግራይና በኤርትራ ሠርተዋል፡፡

ልሂቅ ፕሮፌሰር ዓቢይ ፎርድ  (1927- 2010)

በ1920ዎቹ ዓመታት በማርክስ ጋርቬይ መሪነት ተራማጅ አስተሳሰብ ያራምድ በነበረው የሐርለም ፓን አፍሪካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ከነበሩት አንዱ ራባይ አርኖልድ ጆሹዋ ፎርድ ይጠቀሳሉ፡፡ በማርከስ ጋርቬይ የተመሠረተው ዩኒቨርሳል ኔግሮ ማኅበርም የሙዚቃ ዳይሬክተር ሆነው ከማገልገላቸው ባሻገር ‹‹ወደ አፍሪካ እንመለስ›› በተሰኘው ንቅናቄ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ሲከበር የሙዚቃ ሥራቸውን አቅርበዋል፡፡

የወላይትኛ ድምፃዊ ኮይሻ ሴታ (1963-2010)

ድምፃዊው ኮይሻ ሴታ በ1980ዎቹ አጋማሽ የወላይትኛ ባህላዊ ሙዚቃ በማስተዋወቅ ረገድ ተጠቃሽ ነበር፡፡ በ1984 ዓ.ም. ባሳተመው የወላይትኛ አልበሙ ከሚገኙት ዘፈኖቹ “ኤ አዬ ኤሲስ አቦ…ቡሌ ጋሼ ወላ ሎሜ አያ›› ተደናቂነትን እንዳተረፈበት ይወሳል፡፡

የትምህርት ፕሮፌሰር ሚኒስትርና ዲፕሎማት ኃይለ ገብርኤል ዳኜ (1923-2010)

‹‹ባህልና ትምህርት ሁለት የሚደጋገፉ የሰውን ልጅ ሕይወት የሚወስኑ የማኅበረሰባችን አውታር ክስተቶች ናቸው፡፡ ባህል የማኅበረሰቡን አባላት በአስተሳሰብ እምነት፣ ምኞት ፍላጎት አኗኗር ወዘተ. ይወስናል፡፡ ያስተሳስራል፡፡ ዕውቀት፣ ጣዕም፣ ውበት፣ ብልህነት፣ ክህሎት፣ የመሳሰሉት ከባህል ይመነጫሉ፡፡ ትምህርት ግን ለባህል እንደመሣርያ ሆኖ፣ ባህልን ለአዲሱ ትውልድ በተግባርና በቀለም አማካይነት ያስተላልፋል፡፡

የታሪክና የቴዎሎጊያ ፕሮፌሰር ምክረሥላሴ ገብረአማኑኤል (1923 - 2010)

ከአራት ሺሕ ዓመታት የሚያልፈው የኢትዮጵያ ሥነ ጽሕፈት ታሪክ ከድንጋይ ላይ ጽሑፍ ወደ ብራና ላይ ጽሑፍ የተሸጋገረው ቅዱሳት መጻሕፍትን በዘመነ አክሱም ከመጀመርያው እስከ አራተኛው ምታመት መካከል ባሉት ዐረፍተ ዘመናት ውስጥ በመተርጐም ነው፡፡ መጻሕፍቱ ከግሪክና ከሶርያ ከሌሎችም ቋንቋዎች ወደ ግዕዝ ቋንቋ በመተርጐማቸው እስካሁን አገልግሎት እየሰጡ ናቸው፡፡

ዲዛይነር አምሳለ አበራ (1946-2010)

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አሜሪካዊት አምሳለ አበራ ስመጥር ዲዛይነር ናት፡፡ በተለይ ከሦስት አሠርታት በፊት ጀምሮ በኒውዮርክ ከተማ የሙሽራ ልብስ ዲዛይን ሥራ በመጀመር የሠርግና የራት ልብሶች በማዘጋጀት ትታወቃለች፡፡

ልሂቁ ሐኪም ፕሮፌሰር እደማርያም ጸጋ (1929 - 2010)

በኢትዮጵያ የዘመናዊ ሕክምና ታሪክ ሉዓላዊ ሥፍራ ከሚሰጣቸው ጠበብት ሐኪሞች አንዱ ነበሩ፡፡ የማከም ጸጋ፣ የማስተማር ክሂል የተጎናፀፉት ፕሮፌሰር እደማርያም ጸጋ ስኬታማ ሙያዊ ሕይወታቸውን በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በኋላ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተባለው በ1960ዎቹና 1980ዎቹ በሕክምና ትምህርት ቤት የውስጥ ደዌ ሕክምና ክፍለ ትምህርት ውስጥ አሳልፈዋል፡፡

ካፒቴን ዓለማየሁ አበበ የመጀመርያው አፍሪካዊ ጄት አብራሪ (1916-2010)

በሃያኛው ክፍለ ዘመን የመጀመርያው ሩብ ኢትዮጵያ ከውጭው ዓለም ጋር በአየር ትራንስፖርት ለመገናኛት በር ከፋች አጋጣሚ የተፈጠረበት ነበር፡፡ በንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ ምኒልክ ዘመን፣ በልዑል አልጋ ወራሽ ንጉሥ ተፈሪ መኰንን አማካይነት በ1921 ዓ.ም. የመጀመርያው አውሮፕላን አዲስ አበባ መድረሱ ይወሳል፡፡ ከአውሮፕላን ጋር የተያያዘው ታሪክ እመርታ ማሳየት የጀመረው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታኅሳስ 12 ቀን 1938 ዓ.ም. ከተመሠረተ በኋላ የመጀመርያውን በረራ መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ.ም. ወደ ካይሮ በአስመራ በኩል አድርጓል፡፡