Skip to main content
x

የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪና የሐዋሳ ከንቲባ ሥልጣናቸውን ለቀቁ

በቅርቡ በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ በነበረው ግጭት ምክንያት የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዱላና የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡ ከሦስት ሳምንታት በፊት በተከሰተው ግጭት አሥር ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው 80 ሰዎች የተጎዱ ሲሆን፣ 3500 ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

ካሁን ቀደም በሐዋሳው ጥቃት በወላይታ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው በማለት ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡ ሰዎች በተቀሰቀሰ ሁከት ምክንያት፣ አምስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሥልጣናቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት በአዲስ ሊተኩ ነው

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ምክትል ሊቀመንበር በመሆን የተመረጡት አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን አቶ ደሴ ዳልኬን እንደሚተኩ ታወቀ፡፡

አቶ ማቴዎስ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩትን አቶ ሲራጅ ፈጌሳን ተክተው ማክሰኞ ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. የተመረጡ ሲሆን፣ የድርጅቱ ጽሕፈት ቤትም ከአዲስ አበባ ወደ ክልሉ መዲና ሐዋሳ እንዲዛወር ተወስኗል፡፡

የደኢሕዴን ጽሕፈት ቤት ወደ ደቡብ ከተዛወረ አፈ ጉባዔዋ ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ ተጠቆመ

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ጽሕፈት ቤት ወደ ክልሉ ከተዛወረ፣ ሰኞ ሰኔ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. የንቅናቄው ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ከኃላፊነታቸው ተነስተው ወደ ደቡብ ክልል እንደሚሄዱ ተጠቆመ፡፡

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከፓርቲ ሊቀመንበርነታቸው ለቀቁ

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባደረገው ስብሰባ፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር በመሆን ከየካቲት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡

አቶ ሽፈራው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትርና የደኢሕዴን ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ተክተው ነበር ወደ ሊቀመንበርነት የመጡት፡፡

አቶ ሽፈራው በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በተዋቀረው አዲሱ ካቢኔ የግብርናና የእንስሳት ሀብት ልማት ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

የብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ከኃላፊነታቸው ተነሱ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣንን ከአራት ዓመታት በላይ በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ዘርዓይ አስገዶም ከኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡ አቶ ዘርዓይ በምን ምክንያት ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ባይታወቅም፣ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተሹመው የነበሩት አቶ ሰለሞን ተስፋዬ፣ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡

ኢሕአዴግ ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ሦስተኛው ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ምክር ቤት ከማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ባደረገው ስብሰባ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሊቀመንበር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ፡፡ ማክሰኞ መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ከምሽቱ አምስት ሰዓት ከምክር ቤቱ የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው፣ ዶ/ር ዓብይ በምክር ቤቱ በተደረገ ምርጫ ተመርጠዋል፡፡

ኢሕአዴግ ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ሦስተኛው ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ምክር ቤት ከማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ባደረገው ስብሰባ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሊቀመንበር የሆኑትን ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ፡፡

የኢሕአዴግ አራቱም ብሔራዊ ድርጅቶች ሊቃነ መናብርት ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ይወዳደራሉ

አራቱ የኢሕአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶች ሊቃነ መናብርት ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚወዳደሩ ታወቀ፡፡ አራቱ የኢሕአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶች ማለትም የሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት)፣ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) እና የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ሊቃነ መናብርት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት በሚደረገው ውድድር እንደሚሳተፉ ሪፖርተር ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ተተኪውን ጠቅላይ ሚኒስትር መቀበያ ዋዜማ ላይ

የኢሕአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶች አዳዲስ ሊቃ መናብርትን በመምረጥ ስብሰባቸውን አጠናቀዋል፡፡ ሰሞኑን የደኢሕዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ምትክ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን በመምረጥ ሊቀመንበር አድርጓል፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡