Skip to main content
x

የአዲስ አበባ ካቢኔ የልማት ድርጅቶችን ለግሉ ዘርፍ ክፍት ለማድረግ ወሰነ

የፌዴራል መንግሥት ባፀደቀው የግልና የመንግሥት አጋርነት አዋጅ ቁጥር 1076/2010 መሠረት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሥሩ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና በቦርድ የሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶችን ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ ለማልማት የሚያስችል ውሳኔ አሳለፈ፡፡

መንግሥት ጣልቃ ካልገባ በስተቀር አዲስ አበባ በውኃ እጥረት እንደምትመታ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አወቀ ኃይለ ማርያም (ኢንጂነር)፣ በአገሪቱ የሚገኙ ባንኮች ለውኃ ፕሮጀክቶች የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ተገቢውን ትኩረት በመንፈጋቸው ከአንድ ዓመት በኋላ ከተማው ከፍተኛ የውኃ እጥረት ሊያጋጥመው እንደሚችል አስጠነቀቁ፡፡

የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን 95 ባለሙያዎች ለመቅጠር ላወጣው ማስታወቂያ 13 ሺሕ ተወዳዳሪዎች አመለከቱ

በአዲስ አበባ ከተማን ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት አስተማማኝ ለማድረግ በርካታ ፕሮጀክቶችን በማካሄድ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ 95 ባለሙያዎችን ለመቅጠር ላወጣው ማስታወቂያ 13 ሺሕ ተወዳዳሪዎች አመለከቱ፡፡

የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ንብረት ወደ መጋዘን አሽሽተዋል የተባሉ ተከሳሽ በእስራት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው

ከአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በአቃቂ ቃሊቲ ዕቃ ማከማቻ መጋዘን ውስጥ ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን ንብረቶች በአንድ አይሱዙ በመጫን በመጋዘን ውስጥ መደበቃቸው የተረጋገጠባቸው ተከሳሽ፣ በአንድ ዓመት ከአራት ወራት እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ፡፡ ቅጣት የተጣለባቸው ተከሳሽ አቶ አብዮት ከድር የሚባሉ ሲሆን፣ ያጓጓዙትን ንብረት በመጋዘናቸው ውስጥ ደብቀዋል ተብለው እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው አቶ ጥላሁን ታደሰ ደግሞ፣ የ100 ሺሕ ብር ዋስ አስይዘው በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

ከ8.2 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ስምንት ተከሳሾች በነፃ ተሰናበቱ

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለሕዝብ ውኃ ለማቅረብ በውጭ ምንዛሪ ያስገባቸውን ከ8.2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው 120 ዓይነት የቧንቧ ዕቃዎች፣ በሕገወጥ መንገድ በመውሰድ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው ተከሰው ከነበሩት አሥር ተጠርጣሪዎች ውስጥ ስምንቱ በነፃ ተሰናበቱ፡፡

የመሠረተ ልማት ተቋማት በቅንጅት ለመገንባት ቢስማሙም መቀናጀት ተስኖአቸዋል

ተጠያቂው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ይቀርብበታል ተብሏል በኢትዮጵያ የሚገኙ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ተቋማት በአዲስ አበባ ያሏቸውን ፕሮጀክቶች ተናበው ለማካሄድ ቢስማሙም፣ ቅንጅቱ የተሟላ ባለመሆኑ ስምምነታቸው ፈተና ገጥሞታል፡፡ ተቀናጅተው እየሠሩ ባለመሆኑ ለሚደርሰው ጉዳት ተጠያቂ የሚሆኑ ኃላፊዎች፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በሚሰበስቡት ስብሰባ ሪፖርት ይቀርብባቸዋል ተብሏል፡፡

ለአዲስ አበባና ለኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች የመጠጥ ውኃ ለማቅረብ ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከተማዋና በአዲስ አበባ ዙሪያ ለሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ ለማቅረብ፣ የነደፈውን ግዙፍ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ዓለም አቀፍ ጨረታ አወጣ፡፡

ዕጣ የወጣባቸው የ40/60 የጋራ ቤቶች ግንባታ አለመጠናቀቁና የውኃ ችግር ሊፈታ አለመቻሉ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ከአምስት ዓመታት የግንባታ ጊዜ ቆይታ በኋላ በ2009 ዓ.ም. መገባደጃ ላይ በዕጣ ካስተላለፋቸው የ40/60 የጋራ መኖርያ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ውስጥ፣ በክራውን የሚገኙ ሕንፃዎች ግንባታ ሊጠናቀቅ አለመቻሉና የውኃ ቆጣሪ ሊገባ እንዳልቻለ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ የመሠረተ ልማት ተቋማት በቅንጅት እንዲሠሩ የሚያደርግ ደንብ እየተዘጋጀ ነው

የአገሪቱ የመሠረተ ልማት ተቋማት በአዲስ አበባ ከተማ የሚያካሂዱትን የዘፈቀደ ግንባታ እንዲያስቆም ኃላፊነት የተሰጠው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሠረተ ልማት ቅንጅት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የመሠረተ ልማት ተቋማቱን አቀናጅቶ የሚመራበትን ደንብ እያዘጋጀ መሆኑ ታወቀ፡፡